ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………
ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ……… "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ጠብታ ። ወርኃ የካቲት የታቦቴ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን በስጋ የተለዬን ስለሆነ እያዘከርነው ቢሆን። ለ17 ዓመታት በዘለቀው በእምዬ ሲዊዘርላንድ በራዲዮ #ሎራ 97.5 መካከለኛ ሞገድ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ በቀን ቅዱስ ከ15.00 -16.00 ጸጋዬ ራዲዮ በድንቁ አማርኛ ቋንቋ በሚተላለፈው መሰናዶ በአግባቡ በዬአመቱ ተከብሮ ይዘከራል። የራዲዮ ፕሮግራሙ የተመሰረተበት ዓላማም ግብም ይኽው ነውና። ለታላቅ ባለውለታ የቅኔ አባት መታሰቢያው ክብሩን፤ ልዕልናውን፤ የአማርኛ ቋንቋን የሥልጣኔ ትውፊቱን ማስቀጠል ነውና የትውልዱ ድርሻ። #ውሽክታ ። አቶ ጃዋር መሃመድ ስለ አዲስ አበባ ሰሞኑን ያለው ቁምነገር አለ። ከዛ ያጎረፈ ሃሳቡ በፍፁም የተለዬ አዲስ አበባን የገነባትን #ጉራጌን አትዝለሉ ሲል ለኦሮሞ እና ለአማራ የአዲስ አበባ አቀንቃኞች መልዕክቱን ሳደምጥ #ቁጥር አንድ ውሽክ አልኩ። በነገራችን ላይ የጨመቱ ጉራጌ፤ ጋሞ፤ ወላይታ፤ አማሮ፤ አፋር ወዘተ ማህበረሰቦች ኢትዮጵያ ስለሰጣት ፈጣሪን አላህን ልታመሰግን ይገባታል። ቁጥር ሁለቱ ውሽክታ ደግሞ በአገረ ጀርመን ላይ "እኛ መንግሥት መገልበጥ ሰልችቶናል" ሲል ውሽክ ብዬ ነበር። ኧረ በሞቴ አይሰልችህና ሞክረው በማለት መልሱንም ጥፌያለሁ። ሊንኩም ተቀምጧል። ሰሞኑን ደግሞ በኦነግ ዓርማ በተንቆጠቆጠው አዳራሽ በአሜሪካ ኦሪንገን ላይ ተሰብሳቢወች በጀርባ በሚታዩበት የጃዋሪዝም ጉባኤ ላይ በኦሮምኛ ተናግሮ የተተረጎመውን " ማለዳ " በሚባል ዩቱብ ቻናል፤ "መንግሥት መገልበጥ ከሰለቸን ተሃድሶ ይባል፤ ተጠግኖ ተጠግ...