ልጥፎች

ከኤፕሪል 9, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የችግር መነሻውን ማወቅ መፍትሄ ለማግኘት ይረዳል። „ከቁጣ እራቅ። መዓትንም ተው። እንዳትበድል። አትቅና።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09.04.2019 ከእመ ዝምታ ከሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ከመንግሥት የተሰጠ አንድ መግለጫ አዳመጥኩኝ። ችግሩ ማህበራዊ ሚዲያም አልፈጠረው፤ ህወሃትም አልፈጠረው። ህዝቡም አልፈጠረው። የፈጠረው ኦንግን አቅም ሰጥቶ ፍላጎትን ለማሳካት ተመስጥሮ የተያዘ የራስገመና ነው። ሽብር የተፈቀደለት ዘመን እኮ ነው። በአደባባይ። ይህን ራስን መርምሮ ነገ ሊያስከትል የሚችለውን ነገር በማስተዋል ገርቶ ወጥ የሆነ አቋም መድረስ ይገባል። የሚሆነው ነገር ሁሉ ህወሃት በሻብያ እርዳታ ደርግን አስወግጃለሁኝ እና እኔ በበላይነት አውራ ሆኜ እምራለሁ ብሉ ተሳካለት ወደ 27 ዓመት ሙሉ። አሁን ደግሞ ኦነግን አቅም ሰጥቶ ኦህዴድ አውራ ሆኖ እንዲዘልቅ የማድረግ ተግባር ነው ያለው። አንድ ትልቅ ተደራዳሪ አድርጎ የማውጣት ክንውን ነው ያለው። አቅመ ቢሱ ኦነግ፤ አጀን አልቦሹ ኦነግ በአውሮፕላን ሰተት ብሎ ገብቶ ትጥቁም፤ ስንቁም፤ አልባሳቱም ሳይጓደልበት ተሰናድቶለት በተጠናከረ የመንፈስ ልዕልና የሁሉም ገዢ ሆኖ እንዲወጣ ነው ዓመት ሙሉ የተሠራበት።  በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ራሷን የሚፈርስ ባላንጣዋ እንሆ ሁለመና ተግብሮለት በድል ላይ ይገኛል። ስንቱ ስንትን ነገር ገብሮ ባዶ ሜዳ ላይ ፈሰሰ ዕድሜ አብይወለማ ሌጋሲ … ዕውነቱ ይሄ ነው።  ያ ሁሉ የተጋድሎ ዘመን በነፍስ ወከፍ በቡድን ጊዜ፤ ገንዘብ መዋለ መንፈስ ፈሶ አሁን ሁለመ...