ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።


እንኳን ደህና መጡልኝ።

የችግር መነሻውን ማወቅ
መፍትሄ ለማግኘት ይረዳል።
„ከቁጣ እራቅ። መዓትንም ተው።
እንዳትበድል። አትቅና።“

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09.04.2019
ከእመ ዝምታ ከሲዊዘርላንድ።



ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ከመንግሥት የተሰጠ አንድ መግለጫ አዳመጥኩኝ። ችግሩ ማህበራዊ ሚዲያም አልፈጠረው፤ ህወሃትም አልፈጠረው። ህዝቡም አልፈጠረው።

የፈጠረው ኦንግን አቅም ሰጥቶ ፍላጎትን ለማሳካት ተመስጥሮ የተያዘ የራስገመና ነው። ሽብር የተፈቀደለት ዘመን እኮ ነው። በአደባባይ። ይህን ራስን መርምሮ ነገ ሊያስከትል የሚችለውን ነገር በማስተዋል ገርቶ ወጥ የሆነ አቋም መድረስ ይገባል።

የሚሆነው ነገር ሁሉ ህወሃት በሻብያ እርዳታ ደርግን አስወግጃለሁኝ እና እኔ በበላይነት አውራ ሆኜ እምራለሁ ብሉ ተሳካለት ወደ 27 ዓመት ሙሉ። አሁን ደግሞ ኦነግን አቅም ሰጥቶ ኦህዴድ አውራ ሆኖ እንዲዘልቅ የማድረግ ተግባር ነው ያለው። አንድ ትልቅ ተደራዳሪ አድርጎ የማውጣት ክንውን ነው ያለው።

አቅመ ቢሱ ኦነግ፤ አጀን አልቦሹ ኦነግ በአውሮፕላን ሰተት ብሎ ገብቶ ትጥቁም፤ ስንቁም፤ አልባሳቱም ሳይጓደልበት ተሰናድቶለት በተጠናከረ የመንፈስ ልዕልና የሁሉም ገዢ ሆኖ እንዲወጣ ነው ዓመት ሙሉ የተሠራበት። 

በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ራሷን የሚፈርስ ባላንጣዋ እንሆ ሁለመና ተግብሮለት በድል ላይ ይገኛል። ስንቱ ስንትን ነገር ገብሮ ባዶ ሜዳ ላይ ፈሰሰ ዕድሜ አብይወለማ ሌጋሲ … ዕውነቱ ይሄ ነው። 

ያ ሁሉ የተጋድሎ ዘመን በነፍስ ወከፍ በቡድን ጊዜ፤ ገንዘብ መዋለ መንፈስ ፈሶ አሁን ሁለመናውን ለኦነግ ዓላማ ተሸለመ። ማስተዋል የጎደለው ድጋፍ ነበር ያደረግነው ሁላችንም። ማመን ራስን ብቻ መሆን ነበረበት። ቢያንስ አሁን ስለምን አቅም መዋጣት እንዳለበት ልብ ይኑረን። 

ይህ እንዲሆን የተፈለገበት ምክንያት ኦህዴድ ስልጣን ሲይዝ ካለ ጦር ነበር። በድምጽ ዕድሜ ለብእዴን የራሱን እጩ አግልሎ ከእጩነት ሙሉ ድምጹን ሸልሞ ነው የተከወነው። አሁን የልቤ ብለው አንደ ጆሮ ጉትቻ ጠ/ሚር አብይ ሆኑ ርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ ይዘው የሚዞሩት ደግሞ ማን እንደሆን እናያለን። 

በሌላ በኩል በሎቢም ፈጣሪ በሚያውቀው እኛው እራሳችን ራሳችን እንዲህ እንደ ጨው ለሚያሟሟው ስውር የሴራ ድር ፈቅደን ገብረናል። መታመን ጠፋ። ቃል ተበላ። ተስፋም አነከሰ፤ ... ክፉ ሆኖ ከሚገኝ ትርፍ መልካም ሆኖ የሚመጣ ኪሳራ ይሻለኛል ለእኔ። 

ይህም ሆኖ እኔ ብቻ ነኝ የተጋድሎው አንበሳ ለሚለው ኦዴፓ ይህ ምቾት ሊሰጠው አልቻለም። ስለዚህ ምቾት ለማግኘት ሌላ ክንድ፤ ሌላ ደጅን ማደራጀት ነበረበት፤ "እራሳችን ጥረን ግረን 7 ዓመት ሙሉ ውስጥ ለውስጥ ታግለን ያመጠናው ነው" አዲስ ትርክት ስምረቱ አነግን ጉልበታም አድርጎ በማውጣት አስገድዶ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ማስቀዬስ ነው ስልቱም፤ ጥበቡም ትልሙም። 

ይህን ለማስረገጥ ጉልበታም አቅም እራሳቸው ፈጥረው ተደራዳሪ አድርጎ ማውጣት ተፈለገ። የሆነው የሚሆነው ይኸው ነው። 

አሁን የሰሞኑ የጉለሌው መንግሥት ከጫካው ተጋድሎ ጋር ተለዬ እወጃ ሌላ ሚስጢር የለውም እንዳለ ሁሉም ተዘፍቆበታል። ተጠያቂነት ይምጣ ቢባል ማን ከማን ይለያል? ዳንቴሉ ሊተረተር ነው። ስለዚህ ራስንም ለማዳን የጉለሌው መንግሥት ከጫካው ጋር ግንኙነት እንደሌለው መግለጫ ወጣለት …

እንዳይጠየቅ፤ እንዳሻው እንዲቀጥል ይደረግ እና ነገ በምርጫ ውድድርም ካለምንም እንከን እና ተጠያቂነት እኩል ከቸች ይላል … ስውሩ የቀጠል ወታደራዊ እርምጃ ደግሞ ይቀጥላል … በለመደው መስክ ያርዳል፤ ያቃጥላል፤ ያርዳል፤ ይፈጃል። ተፈቅዶለታል። ያው ለጊዜው በሚቻልበት ክልል ነው። ምርጫ ዋዜማው ሲመጣ ግን ተራፊም አይኖርም። አዲስ አባባ ላይ አዳዲስ ነገሮች መጀመራቸው እዬተነገረ ነው ... 

በታሪክ እንዲህ ዓይነት ዘመን ኢትዮጵያን ለሚፈታተን፤ ሉዕላዊነቷን አደጋ ለሚጥል ጉዳይ ይህን መሰል የታመቀ የሴራ ሂደት አገር አስተናግዳ አታውቅም።  በአደባባይ እኮ ነው ሁሉም ሲሆን የሚታዬው።

በራሷ መንግሥት በራሷ መንፈስ ሉዕላዊነቷን የሚፈተሽ አቅም ቤቱ አውዱ ባዕቱ ቧ ተብሎ ተከፍቶ ወሸኔ እዬተባለለት፤ እዬተደለቀለት እንዲህ ይለፍ ተሰጥቶት አያውቅም።  ሃፍረት ውርዴት ምን ይባል?

በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት ሞገድ የሚባል አንድ መጸሐፍ አለ እሱን አንብቡት። ራስ ያደራጁት ቀውስን እንደገና ራስ ከሳሽ ሆኖ ኢትዮጵያ እና ነፍሷቿ በሽብር ሌትተቀን ይናጣሉ … ሽብሩ፤ ጫናው፤ መከራው እንዲቀጥል የሚፈለግበት ዋናው ምክንያት ተራራ የሚያክለውን ጥያቄ ተሽከሞ ወደ ኮርበታ ለማምጣት ነው።

ከመገንጠል አዲስ አበባ የኦሮምያ ሆኖ እንዲቀጥል ወደሚል ጭብጥ ለማምጣት ነው ይህ ሁሉ ጥምጥም ጉዞ። ቃሉ ሰሞኑን ደርቷል። „ ኢትዮጵያ አንድነት ኩታ ወዘተ ወዘተ …“ እኔ ያቅለሸልሸኛል።

ይህ ከሆነ ምን ኮንዲሚኒየም ቤት ሥር ያራኩታል። ምን ፈጣሪ ለሰጠው የወንዝ ውሃ ምን እሰጣ እገባ ያስገባል … ስለምንስ በዬቦታው ውጥረት ለማንገስ ይፈለጋል?  ብትክ ፖለቲካ ነው ለእኔ። አላወቁበትም። ሲያረጉም አላዩም። መጀመሪያ ሰው ሆነው ለመቆም ይሞክሩ። 

አንዲት ገናና አገርን እንመራለን ተብሎ ላይ እና ታች በዝንቅ ፍላጎት መታመስ። እርግጥ ነው አሁን አዲስ ስልት አለ እነዚህ ተረስታችሁ ነበር የሚሉትን አካባቢ ወደ ራስ ጉዳይ የማሰለፍ። ፈጣሪ ካልፈቀደው የሚሆን ነገር የለም። በማን ላይ እዬታደመ እንዳለ ይገባናል። ገና በአንድ ዓመት ሰውኛ ጠረን አልቦሹ ጉዞ … ይከርፋል። እኔ እንጃ ያስፈራኛል … ነገረ ኢትዮጵያ ... 

ከዚህ ባሻገር የሌላውን ነፍስ አንደበትን ለመዝጋት ደግሞ ሌላ ጥድፊያ አለ፤ ገመናው ታምቆ እንዲቀር። የስታሁኑ ይበቃል እኮ ቀጥለን እንደሂድበት ቢባል። 

ሌላው የገመና ገበታ ደግሞ ... በጭንቀት ማጣደፍ ነው፤ ማስተባበል፤ መካድ፤ ማለከክ፤ መክሰስ፤ መታበይ፤ ትልቅ ናችሁ በሉን ብሎ ያለልክ መንጠራራት፤ ባለስድስት ክንፍ ነን ስህትት አልሰራነም ብሎ መጠን አልቦሽ መሆን  … እኔ እንጃ እንዴት እንዳቅለሸለሸኝ … እንደገለማኝ …

የሰው ልጅ እንዴት አምስግኑኝ ብሎ ያውጃል? ዜሮ ላይ ተቆሞ እኮ ነው ምንም ሳይታይ ምንም ሳይገኝ ሚሊዮን ፍቅሩን መታመኑን የገበረው … ለዛውም ዓመት ሳይሞላ ውለታው አስፓልታ ላይ በጠራራ ጠሃይ ነፍስ ሲረሽን … ደግሞ አዬን።

ስንት ነፍስ ነው የጠፋው? ስንቱ ነው የተፈናቀለው? ስንቱ ነው ከትምህርት ገበታቸው የተሰረዙት? ስንቱ ሩህ ነው በስጋት ሌት እና ቀን የሚናጠው? የትኛው ክልል ይሆን ጤነኛው ከትግራይ በስተቀር? 

አሁን እኮ ክረምት እዬመጣ ነው ሚሊዮን ህጻናት፤ ነፍሰጡሮች፤ አዛውንታት፤ አዳጎዎች ሜዳን ተጠምነው ነው ያሉት። በዚህ ውስጥ ነው እንግዲህ የከረባት የገበርዲን ትርዒት የኬክ ቆረሳው ደርቶ የባጀው ... 

መከበር በከንፈር እና በጠራ ተግባር ነው። አንደበትን ገርቶ ወጥ ለመሆን መጣርም ይገባል። እንደ ውጫሌው አንቀጽ በ አማርኛ ሌላ በኦሮምኛ ሌላ ድምት አይጥ ገድላ እንደምትጫወተው ጢባ ጢቦሽ ሆነ ነገር አለሙ ሁሉ ... ስንቱ ይካዳል? ለስንቱስ መጣፊያ ቁራጭ ይሰናዳ? 

አሁን ይህን የተነኮረ መልከቢስ ቅጠቢስ ፎርመቢስ ሥምየለሽ ገማና ተሸክሞ ያዙኝ ልቀቁኝ የተገባ አይደለም … ፈርሃ እግዚአብሄር የሚባል ነገር አለ ... ይሉኝታው ቢቀር። ክህደት ክብደትን ይቀንሳል ... እውነትን የደፈረ ብቻ ነው ሚዛኑን ጠብቆ መኖር የሚቻለው። 

አይደለም ነገ ዛሬ እጅግ አስፈሪ ነው … ቸሮች ነን ከሆነ ቸርነቱን ካለ፤ ብጽዕናው የልብ ከሆነ …  ፈጣሪ ዋጋውን ይሰጣል፤ ለደጎቹ የዴሞግራፊ ሳይንቲስቶች...   

መምራት ቂጥ ይፈልጋል። ቁጭ ብሎ ለማድመጥ ትልቅ ጆሮን ይጠይቃል፤ ለማደራጀት መቻልን ይጠይቃል፤ ለማቀናጀት ደግሞ ታማኝነትን ይጠይቃል። እስኪ ይህ ያልተሞከረው መስመር ነውና ይሞከር፤

ምስጋና የተስፋ ስንቅ አይደለም። ሙገሳም የራዕይ መባቻ አይደለም። ወንበሩ ተቀምጦ የሚሰራበት ይፈልጋል።

በግራ በቀኝ በማጣደፍ ፋታ ነስቶ ኢትዮጵያን አፍሪካን መናህሪያ አልባ ከማድረግ መቆጠብ ይገባል። ኢትዮጵያዊነት ማለት ይሄው ነው።

ዛሬ ብዙ ሰው ላይታዬው ይችል ይሆናል መራራ ነገር ፊት ለፊት አለ … የተጀመረ እንጂ አለቀ የተባለ፤ መቋጫ አገኜ የተባለ አንዲትም ነገር የለም … አንቲፔን እንደ ፈውስ ነው እዬታዬ ያለው ... ትንሽ ሃሳብ ሲገለጥ ያዙኝ ልቀቁኝ ክላሽኮፕ ጥይጥ ማጉረስ ነው። ዴሞክራሲ እንዲህ አይደለም ... የማይፍለጉትን ሃሳብ ላመደመጥ መሰናዳት ያስፈልጋል። ዜግነት የክት እና የዘወትር የቅልሞሽ ጨዋታ አይደለም። 

በዬቦታው ውጥን ነው፤ ውጥን ደግሞ ጊዜ ኖሮ ክትትልን ይጠይቃል … በመጓዝ ዓመቱ ተጠናቋል። ከእንግዲህ ደግሞ ያ የቤተመንግሥት ወንበር ወጉ ይድረሰው እና ቁጭ ተብሎ ይሰራበት …

በስውር ኢትዮጵያን የሚወጋ ሃይል ጋር መንፈስን አደራጅቶ የምልዕትን መንፈስ በስጋት ማረስም ኩነኔ ነው … ያ እንዳለፈ ሁሉ ይህም ያልፋል። ለመከራኞቹ ኢትዮጵውያን ተስፋው ሁሉ ትቢያ ለለመሰባቸው ምንዱባን ...
 https://www.youtube.com/watch?v=Z62ql_T837g


አቶ ንጉሱ ጥላሁን የሰጡት መግለጫ


ፈጣሪ ከሴረኞች ጋር ሳይሆን ከቅኖች ጋር ነው ያለው። አምላክ አለን! መታመናችን የሚያከብር የፈጠረን አማኑኤል አለ። ታማኝነታችን ዋጋ የሚሰጥ መዳህኒተ ዓለም አለ። 

ወረተ„ከቁጣ እራቅ። መዓትንም ተው።
              እንዳትበድል። አትቅና።“ኛ እና ጊዜኛ ያልሆነ ልዑል አለን ሁሉን ቻይ አዶናይ። 

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።