„ጋዜጠኝነትን እንደ መንገድ እንጂ እንደ ግብ አላዬውም።“ (ጋዜጠኛ ሙኒራ አብደልመናን አውል)
„አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል፤ በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል? በቅንነት የሚሄድ ጽድቅንም የሚያደርግ በልቡም ዕውነት የሚናገር“ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 14 ቁጥር 1 ) ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና የሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ ጋዜጠኝነትን እንደ መንገድ እንጂ እንደ ግብ አላዬውም።“ (ጋዜጠኛ ሙኒራ አብደልመናን አውል) · መነሻ ምርኩዜ። https://www.youtube.com/watch?v=mm3mFckIO_8&t=68s Ethiopia: EthioTube አፈርሳታ - Lidetu Ayalew : ልደቱ አያሌው | February, 2021 104,436 views • Premiered Feb 13, 2021 · ምክሬ። እናት የመጀመሪያዋ ትምህርት ቤት ናት እላለሁኝ። እናትም የመኖር መቅድመ የፊደል ገበታ ናት እላለሁም። እናት የመጀመሪያዋ ዬህይወት ጎዳና ናት እላለሁኝ። እናት የመጀመሪያዋ ሉዓላዊ መምህር ናት የሚል ፍልስፍናም አለኝ። ትክክለኝነቱን ሁሉም ከእናት ማህጸን ስለተፈጠረ መመዘን እና መወሰን የእያንዳንዱ የሥርጉትሻ ብራና ቅን ታዳሚ መብት ይሆናል። እናቴ እብዬ ሆዴ በማህበራዊ ግንኙነቴ ውስጥ ከምትለግሰኝ ምክር አንዱን ላጋራ። „መጀመሪያ ስታይው የምትደነግጭለት፤ ከራስ ጸጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ውርር ካደረገሽ ያ ሰው፤ ያቺ ሴት የአንቺ የውስጥሽ የምትሆን ናት እና አትለፊው፤ አትለፊያት“ ትለኝ ነበር...