ልጥፎች

ከሜይ 21, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጤና ባለሙያወች #የራሳቸው #ጉዳይ ነው በህብረት ያስነሳቸው። ሌላ ገፊ ኃይል ያላቸው አይመስለኝም።

ምስል
  የጤና ባለሙያወች #የራሳቸው #ጉዳይ ነው በህብረት ያስነሳቸው። ሌላ ገፊ ኃይል ያላቸው አይመስለኝም።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       በዘመነ አብይዝም የ፯ ዓመታት የአገዛዝ ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ ያልታዬ የፈተና፤ ያልተሞከረ የቀውስ፤ ያልተመለከትነው የሴራ ድንኳን የለም። 100 ቀናት ሳይሞላ ገና በልጅነት ዕድሜው ከሰኔ 16 ጀመሮ በመላ ኢትዮጵያ ያልታዬ የፈተና ቡፌ የለም። ደቡብ ምን ያህል ህዝብ ነው የተፈናቀለው። የገዴወ፤ የጋሞ ህዝብ ምን ዋጋ ከፈለ። ቡራዩ ለገዳዲ አዲስ አበባ ፦ ብቻ ፈተና ኢትዮጵያን ፈተናት።   ቀውሱ በመንግሥትም ታቅዶ፤ መንግሥት ውስጥ ባሉትም ተመስጥሮ እንዲሁም በፊት በምን አቅሙ እል የነበረው #ህወሃት መራሽ ሴራም በሚችለው ሁሉ በቀውስ አምራችነት ላይ ተሳትፎ እንደ ነበር ዛሬ ባለው የህውሃት የትርምስ ማሳቸው ለመገንዘብ ችያለሁኝ። ከዚህ ጋር ተያይዞም የህወሃት ሆነ የኢህዴግ #ተስፈኞችም ተመሳሳይ ትጋት እንደ ነበራቸው ቢዘገይም ምልክቶቹ ዛሬ ይፋ ናቸው። በምን መሥፈርት ህወሃት እንደሚናፍቅ ባይገባኝም።    የሆነ ሆኖ በህወሃት እና በብልጽግና #ልግዛህ እና #አልገዛም ጦርነት፤ በብልጽግና እና በአማራ ትጥቅ ፍቱ፤ አንፈታም የነፍጥ ተጋድሎ፤ በኦነግ የጫካው እና በብልጽግና፤ በኦነግ መንፈስ እና በአማራ ህዝብ የደረሰው ሰቆቃ ውስጥ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያወች #ቤተ - ሳይለንት ማጆሪቲው ውስጥ ነበሩ። እርግጥ መጀመሪያ ላይ ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸው የጋራ ቆይታ ጥያቄያቸውን ከሞላ ጎደል ማንሳታቸውን አስታውሳለሁ። ይህም #በራሳቸው #ጉዳይ ላይ ብቻ ነበር።   የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያወች በየትኛውም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ የሙያ...

"የሐኪሞቹ መሠረታዊ የሆነው የመብት ጥያቄ ምላሽ ይሻል!" (ነጭ ቁጣ - Witte Woede) የአቶ ያሬድ ኃይለማርያም ዕይታ

  "የሐኪሞቹ መሠረታዊ የሆነው የመብት ጥያቄ ምላሽ ይሻል!" (ነጭ ቁጣ - Witte Woede)   ትናንት ከሃሳብ ገበታ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ዘግቤ ነበር። ድርጅታቸውም መግለጫ እንዳወጣ ሲገልጡ ሰምቻለሁኝ። አንድ ሃኪም ደም የሚሰጥ ላጣ በሽተኛ ደም መስጠቱን፤ ሌላ ሃኪም ከአባቱ የመጨረሻ መራራ ስንብት ይልቅ የበሽተኛው ቀዶ ጥገና በልጦበት በዛ ላይ እንዳተኮረ በዕውነት የተየሠረተ መረጃ ሲሰጡ ሰምቻለሁኝ። ዛሬ ከአቶ መላኩ በላይ ፔጅ ያገኜሁትን እንሆ። የጨመቱ፤ በንግግራቸውም ጥንቁቅ፤ ቋሚ የሆነ የሰባዊ መብት ትጋት ያላቸው በመሆኑ የማከብራቸው ናቸው።    ተቋማቸው ታግዶ ሁሉ ነበር። የዓለም የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ከታሠረ ሦስት ዓመታት እንዳሳለፈ ሲናገሩ ሰምቻለሁኝ። የሠራተኛም አደራጅ ስለነበርኩ ውስጤ ቁስል ነው ያለው። ሠራተኞች የህብረት ድምጽ ማሰሚያ ቀናቸው ሲታሠር እሰቡት። ወይ አብይዝም????? መጨረሻውን ያዬው ሰው። #ዕድሉን ሁሉ እጥፍጥፍ፥ #ኩፍትርትር እያደራረገ የት ሊደርስ ይሆን???? የአቶ ያሬድ ኃይለማርያም ዕይታ …………   "በሕክምና ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች በድፍን ጦቢያ ላይ ያጠላውን የፍርሃት ድባብ ገፈው 'ኽረ እየተራብን ነው፣ ብዙ አመታትን ተምረን አገር እያገለገልን እኛ ግን ተረስተናል፣ ደሞዛችን የኑሮን ውድነት እንድንቋቋም አቅም የሚፈጥር አይደለም፣ በቀን አንድ ጊዜ መብላት አቅቶናል' በሚል ለአመታት ውስጥ ለውስጥ ሲያጉረመርሙበት የቆየውን ብሶት ዛሬ አደባባይ ይዘው መውጣታቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። መብትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠየቅ ስልጡንነት ነው።    መንግስት ትኩረት ከነፈጋቸው ዘርፎች መካከልና የመጨረሻው የትኩረት ተርታ ላይ የሚቀመጡት ትምህንትና ጤና ናቸ...