ልጥፎች

ከማርች 29, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው????

ምስል
  መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው???? …… "አቤቱ ፀሎቴንም ስማ ልመናዬንም ቸል አትበል።" (መዝሙር ፶፬ ቁጥር ፩)     • በጭካኔ በሰለጠኑ፤ • በበቀል በተነከሩ፤ • በቂም በበቀሉ፤ • በጥላቻ በተዘፈዘፉ፥ • በበታችነት ስሜት ወፈፍ ባሉ፥ • በህሊና አቅም ማነስ በሚባትቱ፤ • በአንጃ ግራንጃ ግንዛቤ ዬሚውተረተሩ፤ • በተለጠጠ ፍላጎት አገር ያህል ቁምነገር በከንቱነት ዬሚመሩ ዘመነኞችን ለመታገል _ መበሳጨት _ መጣደፍ _ መንቦጅቦጅ _ ሱሪ በአንገት አያዋጣም። • ብዙ ነገር ዬተፈጠርንበትን ባዕት፤ ዬዘር ሐረግ፤ ዬአልረገጥም ጽኑ አቋም እና አሻምነት ባይመቻችሁ እንኳን በጣም በርቀት ዬሚታዩ ዕሳቤወችን እህ ----- ብሎ ማድመጥ ይገባ ነበር ቤተ ሰለሞን ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አላችሁ። ግን ዓለማችን ዬጆሮ ገብያ አልከፈተች። በስልተ ቢስ እሰጣ ገባ፤ በግርግር ፖለቲካ፤ ወዳጅ እና ተቀናቃኝን ባለዬ ዬዝንቅ ጉዞ ባዶ እጅ እዚህ አደረሰ። • ዛሬን ለማዬት ተስኖ አዳዲስ አዛይ ዕሳቤወችን እዬፈጠሩ ዬናዷችሁን አክ ብላችሁ ዕውነት - ሃቀኝነት - መርህ እና ዬትግል ታማኝነት ዬት ላይ እንዳለ መዝኖ መወሰን ይጠይቃል። አሁንም ለግብር ዬሚጠራው ማን እንደሆን አስተውላለሁ። በማን መሪነት? ምን አለን? ማን አለን? ነገስ ለማን - ልዕልና ይታሰብበት። ብቻውን ዬቆመው ዬአማራ ህዝብም ይሰብበት። • ወደ ባህርዳር ጉዞ ዬሚታገትበት ዘመን ሊመጣ እንደሚችል እሰቡት። መታገት ዓይነቱ ብዙ ነው። ሁሉም እስረኛ እንደሆነ ይሰማኛል። ለዚህ ደግሞ መንገዱ ዬእስራኤሎች ጽናት እና ጥበብ ይመስለኛል። መሪ ማውጣትም ይለመድ። ፋክሩ ይቁም። እማዬው ነገር ስላለ። #የጣቶቼ ፍቅረኛ የጠይሟ ዕንቁዬ ዬባርች። ታላቅ እህቴም

በለተ ሰንበት ኢትዮጵያ ሽፍታ እጅ መውደቋ ጆሮ አልባው እኛዊነት ስገልፀው ውሃ ያዘለ ተራራ ዬተሸከምኩ ያህል ከበደኝ። መታሰር በስለት ዬሚገኝ ዘመን ላይ።

ምስል
  በለተ ሰንበት ኢትዮጵያ ሽፍታ እጅ መውደቋ ጆሮ አልባው እኛዊነት ስገልፀው ውሃ ያዘለ ተራራ ዬተሸከምኩ ያህል ከበደኝ። መታሰር በስለት ዬሚገኝ ዘመን ላይ።   በለተ ሰንበት ኢትዮጵያ ሽፍታ እጅ መውደቋ ጆሮ አልባው እኛዊነት ስገልፀው ውሃ ያዘለ ተራራ ዬተሸከምኩ ያህል ከበደኝ። መታሰር በስለት ዬሚገኝ ዘመን ላይ።       በለተ ሰንበት ኢትዮጵያ ሽፍታ እጅ መውደቋ ጆሮ አልባው እኛዊነት ስገልፀው ውሃ ያዘለ ተራራ ዬተሸከምኩ ያህል ከበደኝ። መታሰር በስለት ዬሚገኝ ዘመን ላይ። #መታሰር መመረቅ ነው ልል ዳር ዳር እያለኝ ነው። #ወይ ሩህሩኋ እናት አገሬ ከምኑ ጋሬጣ ጣለሽ። እነኛ ታፍነው፤ ታግተው ዬተወሰዱት ልጆቻችን፤ ወንድም እና እህቶቻችን ምን ያህል ገኃነም ውስጥ እንደ አሉ በጥልቀት አዬሁት። ዬታሰሩት ይፈቱልኝ። እናቶች ይሳቁልኝ። ልጆች ይቧርቁልኝ። ሚስቶች መሰናዶ ያሟልኝ ዬቅንጦት ያህል ነው። ሆኖ ተሰማኝ። ቃለ ምልልሱን እያዳመጥኩ ፊቴ ዳመና ዋጠው። እኔ ከማለዳው ቢገባኝም ስንት አቅም እንደባከነ አሰላሁት። #ረመጥ ። https://www.youtube.com/watch?v=yk3Kzm17aPU «ጥብቅ ሚስጥር! ኦነግ ሸኔ የብልጽግና አንዱ ክንፍ ነው! // በጋራ የሚሰሩት ኦፕሬሽን ሲጋለጥ! | Oromia | Onege Shene | Ethiopia» እኔ ፀፀት ዬለብኝም እራሴን አቅቤ እዚህም ክንፋ ስላለ ዕውነቱን እዬተማገድኩ በእርጋታ ገልጫለሁኝ። እቅሙ ሁሉ እኛን ለማጥፋት መዋል ለበትም እያልኩኝ። አሁንም ከዛው ላይ ነን ግን ሙት መሬታችን ታቅፈን። #ፎቶው የራሴ ቅንብር ነው። የኢትዮጵያ ቀኖች ዕንባ እዬለቀሙ፤ ሞት እዬዘገኑ ከሚለው አውዲዮ ጋር ፖስት ተደርጓል። ዋናው ዕሳቤ የወንጀሎች ሁሉ ሞደሬተር ዬኖቤሉ የሰላም አባት ሎሬት አብይ አህመድ ናቸው ነ

ድካምን እርቃን ላለማስቀረት #ዬቋንጃ ጉዞ ይቁም።

ምስል
  ድካምን እርቃን ላለማስቀረት #ዬቋንጃ ጉዞ ይቁም። ትዕዛዝ አይደለም ዕይታ ቅናዊ በተለይ ለአማራ ሳተና ወጣቶች። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ፤ በቅዱሳንህም ዘንድ መልካም ነውና፤ ሥምህን ተስፋ አደርጋለሁ።" (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፱)     • ዬውቂ ደብልቂ ቅልቅል አደብ ይግዛ። • ዬግርግር ሩጫ ተግ ይበል። • ዬጥድፊያ ግልቢያም ይጨምት። #መሪነት ሩቅ ማዬት እንጂ ቅርብ አዳሪነት ማለት አይደለም። • አንደበቶች ይገሩ። ዬ፶ (50) ዓመቱን ዝልቦ መከራ ዬተሸከመው ዬአማራ ህዝብ መሪው መከራው፤ • ማኒፌስቶው ውዚደሙ ይሆን። • ያገኜ ዬሚነዳው አይሆን። #ዬመሪነት ጥበብ ተከታታይነትን ይጠይቃል። ይህ ማለት ሙሉ ዬወጣት፥ ሙሉ ዬጎልማሳ፤ ሙሉ ዬባለግራጫማ ሰብዕና ጠቅልሎ አመራሩ ሊይዝ አይገባም። ተወራራሽነት ያስፈልጋል። ወጣቶች ዬወስፋት ማሳረፊያ እራፊ ተመክሮ ሳይሆን ጎታ መር ተመክሮን ከግራጫማው ሰብዕና ዝቅ ብሎ ለምኖ መማር ይኖርባቸዋል።።ጎልማሳውም እንዲሁ። ሙጥጥ ያለ ዬመሪነት ሂደት ድርቅ ዬመታው ይሆናል። ዘመን እና ዘመንንም ከመቃብር እንዳይቋቋሙ ያማምላል። ይህ ደግሞ ለትውልድ ታሪካዊ ዬልቅና ጉዞ ግድፈት ነው። ዬአሁኑ ኦነግ መራሽ አሳር ይህ ነው። ሲነሪቲ አንጡራ ጠላቱ ነው። እዬተከታተለ እዬመነጠረው ነው። ትናንትን እንደ ደመኛ የሚይም ጉድጓድ ነው። ዬአማራ ወጣቶች ከዚህ ከተላጠ፤ ከተጋጋጠ፤ ከተሞነጫጨረ፣ ከተፋፋቀ ፍግ ሂደት ጋር እንዳይወዳጁ አበክሬ ላስገነዝባቸው እወዳለሁኝ። ለአማራ ዬተስፋ ጉዞ ታዳጊወች፣ ወጣቶች፤ ጎልማሶች #ዬላስታ አለታቸው ዬቀደምት ትውፊት፤ ታሪክ፤ ትሩፋት፤ ገድል፤ ዬጉዞ ተመክሮ ጥልቁ ዊዝደማቸው ሊሆን ይገባል። አትራፊነት ፈንታዚን ማምለክ ሳይሆን በራስነት ውስጥነት መመሰጥ፣ መወስን በህይወቱ ውስጥ

ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።

ምስል
  ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ። "ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ። በእሽታ መንፈስ ደግፈኝ።" (መዝሙር ፶ ቁ ፲፪)   (1) ያለን ነገር ማወቅ። (2) ያለን ነገር ማጥናት። (3) ያለን ነገር መመዘን። (4) በአለ ነገር መነሳት። (5) በአለ ነገር ላይ መደራጀት። (6) ዬአለን ነገር ለመምራት በአለን ነገር ውስጥ ያለውን ዲስፕሊን ጠንቅቆ ማወቅ። (7) በአለን ውስጥ ያሉ መልካም ነገሮችን ከደም ጋር ማዋህድ። ( ብስጭትን - ገረጭራጫነትን - ሞረድ አንጀትን ዬክፋት አውራ ጎዳናወችን አክ ማለት። አለን ለሚባለው ሁሉ ቀና ጎዳና ቀያሽ ነው። ለዚህ ደግሞ እራስን መግዛት ይጠይቃል። በአንድም በሌላማ ዬውርጅብኝ ናዳ ዬሚወርድባቸው ሰብዕናወች በዬዘመኑ አሉ። እነሱን ዬራስ ለማድረግ አለን ዬምንለውን በጥንቃቄ ይዘን … • ተደማጭ፤ • አሸናፊ ማድረግ ካልተቻለ ዬወቀሳ ተርቲም ዛሬን አያተርፍም፣ ለነገም ጭጎጎት ነው። እዮባዊቷ ቅድስታችን ከዬትኛውም ተቋም በላይ ዬዘመኑ ዓውራ እንድትከስም ዬተፈረደባት አሳረኛ ናት። • አጥኑት ዊዝደሟን። • ሁሉን ረብ አድርጋ በከፍታ ላይ ትገኛለች። • ሁሉን ነገር ታውቃለች። መሪዋ መንፈሥ ቅዱስ ነውና። • ስለሆነም ተፍተፍ ዬለም። • ባጉም ባጉምም አይታሰብም። • ግልቢያም ትውር አይልም። • ዬቂም ብቅልም ዬላትም። • ያላት አርምሞ፤ ተደሞ፤ ጥሞና ፆም ጠሎት፥ ስግደት፤ ሱባዔ፤ ምስጋና፤ ዝማሬ፤ ቅዳሤ፤ ማህሌት ወዘተ … እዮባዊቷን አለችን ማለት ይገባል፤ ነገረ ፍጥረቷ ቫወል ነው። • እኛ እናሰግርሽ እንደ በቅሎ እንጋላብሽ ግን ቀኖናዋም፤ ዶግማዋም አይደለም። • እዮባዊቷ ዬፖለቲካ ድርጅት አይደለችም። • ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ለአገር ሰላም ብቻ ዬሚውል እንጂ ዛሬ ተሰርቶ ነገ ለሚፈርስ ግጥምጥም ጤዛ ዬፖለቲካ

ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል።

ምስል
  ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል። • ጨካኞች በሽተኛ ናቸው። እንደ ሙሉ ሰው ሊታዩ አይገባም። • ጨካኞች ያልሰለጠኑ ናቸው። ሥልጣኔ ኢንተግሪቲ ነውና። • ጭካኔ ዬአስተሳሰብ ድህነት ነው ወደ ኋላ አብራራዋለሁኝ። • ጭካኔ ዬድንጋይ ዘመን ህዳሴ ነው። ጭካኔ ሰብዕናን ገድሎ ጫካዊነትን ማነፅ ነው። • ጨካኝ ሱፍ እና ገበርዲን ከረባት እና ቀሚስ አደለም ሰብእናዊ ቀለም ነው። • ጨካኞች አመክንዮ ስለመፈጠሩ አያውቁም፣ እርካታቸው አመክንዮን መስቀል ነውና። • ጨካኝነትን ለፋክክር ዬሚያቀርቡ ልሙጥ ሰብዕና ያላቸው ናቸው እና። እንሰሳነት ስለማያስቀና።     #ኋላቀርነት ። በኢኮኖሚ ሳይንቲስቶች ኋላቀርነት በኢኮኖሚ ዕድገት አለመመጣጠን ይሉታል። እኔ ደግሞ በአስተሳሰብ ዘሃ ዬህሊና ድህነት እለዋለሁኝ። ልቆ አይፈጠርም የሰው ልጅ። ቅዱሳን አሉ በቅብዓ ዬሚሰጡ። ነገር ግን ዬሰው ልጅ ዲግሪውን ቁብ አድርጎ አይፈጠረም። ሂደት ትምህርት ቤት ነው። መኖር ትምህርት ቤት ነው። ቤተሰብ ትምህርት ቤት ነው። የአኗኗር ዘይቤ ትምህርት ቤት ነው። ተፈጥሮ ትምህርት ቤት ነው። ቀደመው ዬታነፁ፤ ዬተገነቡ ቅርስ እና ውርሶች ትምህርት ቤት ነው። ታሪክ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤት ዬግድ ዩንቨርስቲ መግባት ብቻ አይሆንም። ዕድሉን ያገኙ ሁለገቡን ተምረውበት ክህሎቱን በሥልጠና ያዘምኑታል። ይህ ለታደሉት ነው። ላልታደሉት ደግሞ ትውስቱም፤ ውራጁም ብርቃቸው ነው። አሁን ለፋንታዚው ልዑል ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የውሃ ዳንስ፤ የፓርክ ግንባታ፤ የኩሬ ውሃ ዋና ብርቅ እና ድንቃቸው ነው። ይህ ግን አንዱን ቤተ ጊዮርጊስ የሚሰጠውን ሚስጢር አቻ ሊሆነው አይችልም። ግብግቡ ዬጭካኔው ውርስ የሥልጣኔውን ውርስ ተፃሮ ውድመት ላይ መባጀቱ ነው። ኦነግ መራሹ የኦሮሞ ፖለቲካ ከሊቅ

የለውጥ ሃሳብ።

ምስል
  የለውጥ ሃሳብ። • የለውጥ ሃሳብ ሂደትን ማዕቀብ በመጣል ማስቆም ወይንም የታቆረ ማድረግ አይቻልም። በፍጹም። ተፈጥሯዊ ነውና! „በታካች ሰው እርሻ፤ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ። እነሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፤ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል። የድጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“ (መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴፩)     • በር። ለእኔ በማሰብ ልቅና የአስተሳሰብ ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ። የነቃው የህሊና ክፍል አዲስ ሃሳብ ሲያፈልቅ ሃሳቡን የሚቀበል ህሊና፤ አዕምሮ ሊኖረው ይገባል። ይህ አዕምሮ ያፈለቀውን አዲስ ሃሳብ የሚመጥን የሰብዕና አቅም የሚኖረው ከአቅሙ ከራሱ በመመንጨቱ ነው። አዲሱ ልቅና ያለው አስተሳሰብ ሃሳብ የትውስት ወይንም የብድር አይደለም። ስለምን? አዲሱ ዬአስተሳሰብ ልቅና ካለው ከራሱ ህሊና፤ የአዕምሮ የአቅም ፏፏቴ የመነጨ ስለሆነ ዲስፕሊኑን የመሸከም ብቻ ሳይሆን በቅጡ አደራጅቶ የመምራት፤ የማስተዳደር አቅሙ ተመጣጠኝ ነው። .. ብቻም ሳይሆን ሚዛናዊነቱ በራሱ የአዕምሮ የውሃ ልክን የሚያስጠብቅ ተጠባባቂ የሃሳብ ማህበር ዘብም ይኖረዋል። እንደገናም የማህበራዊ ንቃተ ህሊናው የመሸከም ዲስፕሊን አንጻር ማዬት ይጠቅማል። ቀድሞ ነገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና አጀንዳው ሆኖ አያውቅም። መነሻ የሌለው መድረሻ ሲያልም የኖረ ልም። • ምጥነት። የወገቡ ስፋት 35 ሴንቲሜትር የሆነ ልብስ የ52 ሴንቲሜትር ስፋት ያለው ልብስ ቢጠለቅለት መዋኛ ገንዳ ነው የሚሆነው። ወይንም 35 ሴንቲሜትር የወገብ ስፋት ላለው 10 ሴንቲሜትር ስፋት ያለው ልበስ ቢባልም ይሄም በጅ የሚል አይሆንም። አሁን የገዳ ኦሮሙማ እና የምርኩዞቹ አዲሱ ችግርም ይሄው ነው። ቢደረደሩ፤ ቢከመሩ፤ እንደ ተራራ ቢቆለሉ፤ አንደ አነባበሮ ቢነበባሩ

ዬአስተሳሰብ ደራጎንነት እና ጢስ ጢንብሳዊነቱ።

ምስል
  ዬአስተሳሰብ ደራጎንነት እና ጢስ ጢንብሳዊነቱ። "ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።" (መዝሙር ፶ ቁጥር ፲፪)     እነ ማበህረ ደራጎን በሄሮድስ መለስ ዜናዊ አንቀልባ በታቆረ ጥብቆ ህሊና ሊመጥነው በማይችል ቅዠት ውስጥ ሆነው እናያለን። ቅዠታቸውን ለማስቀጠል ያላቸው የአዕምሮ ብቃት አቅሙ አልተመጣጠነም። ያልገባቸው ጉዳይ ይሄ ነው። ስለዚህ ባነሰ ግምት ስድስት ዓይነት ጦርነቶች ተከፍቶባቸዋል።    • አንደኛው፣ … የሻገተው አስተሳብን ለመሳቀጠል ያለ ከራሳቸውም ጋር ራሳቸው ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። • ሁለተኛው፣ … በራሳቸው ማህበርተኛ ወስጥ የተፈጠረ አዲስ ሃሳብ አቅም አለ አስምጧቸዋል። • ሦስተኛው፣… በሃሳብ ልዕልና በሚያምኑ አቅሞች ሙግቶችን የመቋቋም ግብ ግብ ላይ ናቸው። • አራተኛው፣ … በራሱ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ውስጥ የተከደነ የጦርነት ቀጠና ውስጥ የተጠለለ የዲፕሎማሲ ተጋድሎ አለ። • አምስተኛው፣ … ከሁሉም ያልሆነ ግን የመንፈስ አቅሙ ሙሉዑ የሆነ፤ ልኩ ያልታወቀ አቅም ልዩ ኃይል አለ፤ ይሄ „ጸጥተኛ ፤ ጭምታዊ ድምጽ silent majority“ የሚባለው። • ስድስተኛው፣ … የድሮ ዓለምዓቀፍ ወዳጆቻቸው ሂደቱን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም በቅርበት እዬተከታተሉት መሆኑ ሌላው ፈተና ነው።   ለዚህ ሁሉ ፈተና የማህበረ ሌንጮ ህልማቸውን የሚሸከም የአስተሳብ/ የሃሳብ፤ የሰብዕና፤ የአዕምሮ ደረጃው ነገቲብ ላይ ነው። የዛገ ብርት ዝግት እዬጨመረ በሄደ ቁጥር ቀለሙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የመስጠት አቅሙም ያኑ ያህል እዬተፈረፈረ ይሄዳል። ቀብር። በሂደቱ ራሱን መሸከም እያቃተው ለበለጠ ክስመቱ ሆነ ዕድሜ ማጠሩ እራሱን በራሱ ያጣፋል። በዚህ ማህል በተነደለ ቁጥር መወተፊያ የሆነው የለበጣ ግርዶሽ ገመናው የአደባባይ ሲ

አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል።

ምስል
  አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል። "ዬደም ሰወች እና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ አይሞላም።:እኔ ግን አቤቱ እታመንኃለሁኝ።" (መዝሙር ፶፪ ቁጥር ፳፫)     ትግሉ የአልሞትም ባይ ተጋዳይነትን ስለሚጨምር የሚያስከፍለው መስዋዕትነት የከፋ ይሆናል። ግን አዲሱ ሃሳብ በአዲስ አቅማዊ ስልትና ስትራቴጂ በጥበብ ስለሚመራ አሸናፊ መሆኑ አይቀሬ ነው። ይህ ስለተፈራ ነው አብሮነት የተሰረዘው በገዳ ምርጫ ቦርድ። አብሮነትን የገዳ ምርጫ ቦርድ በድፍረት እና በማናህሎኝነት ሲሰርዘው ኢትዮጵያን ሰርዟታል። ኢትዮጵያ መለያ ማልያዋ አብሮነት ነውና። በሌላ በኩል አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል። አሰምሌሽንም ተፈጽሞባቸዋል። ይህ በጣም ረቂቅ አመክንዮ ነው። በእኔ ውስጥ እኔ ስኖር ብቻ ነው ሊታዬኝ የሚችለው። አንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም ሲደረመስ በእኔ ውስጥ ያለው መንፈስም አብሮ መደረመስ ታውጆበታል ማለት ነው። አብሮነት ጆኖሳይደ ሲካሄድበት እኔንም ይጨምራል። • እኔ ተቋሜ ኢትዮጵያ ናት። • ኢትዮጵያ ደግሞ የአብሮነት ማህደር ናት። • አብሮነትን ሥሙ ትውፊቴም ትሩፋቴም ነው። • ትውፊቴን የፖለቲካ አመንዝራዋ የገዳ ልዕልት ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ሲፈጽሙት በእኔንም ላይ ፈረዱ። እሳቸው 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዛገው ገዳቸው ላይ ነው ያሉት። እኛ ደግሞ 21ኛው ምዕተ ዓመት ሰውኛ እኛዊነት ላይ እንገናኛለን። መመጣጠን ያልቻልነውም በዚኸው አመክንዮ ነው። „ጸጥተኛ ድምጽ silent majority“ አባልተኞችም የቀና ቀን ጠባቂዎች ናቸው። ስብጥራቸው ሁሉንም የአቅም አይነት ያሟላ ነው። እነኝህ ከሁሉም ጋር ያልነበሩ ድርጁ መንፈሶች የበቃ የአቅም መቅኖ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው። ለእነኝህም ተቋማቸው ኢትዮጵያ እና

የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አይቻልም። • የዛገው ብረት በማረተ ሃሳብ … ???

ምስል
  የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አይቻልም። • የዛገው ብረት በማረተ ሃሳብ … ??? "ኃያል ሆይ በክፋት ለምን ትጎዳዳለህ?" "ሁልጊዜስ በመተላለፍ?" (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፩)     የዛገው የጉራጁ ኢህዴግ ኦህዴድ የማረቱ ምርኩዞቹ የዚህን የአዲስ ዘመን መንፈስ ሰላሙን በማወክ ትንፋሹን ማባከን ቀዳሚው መስካቸው ነው። የማያዋቀው ነገር ግን የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አለመቻሉ ነው። አንድ ጊዜ ተፈጥሯል። እንደ ጉርሻ ዋጥ ተደርጎ ጸጥ የሚባልበት አይሆንም። አዲስ ሃሳብ ምጡ እስኪ ወለድ ድረስ ነው። ከተወለደ በኋዋላ ግን በራሱ ጊዜ እድገቱን መቀጠሉ የተፈጥሮ ህጉ ነው። አንድ በህክምና ዶር. የተመረቀ ሰው በዕወቀቱ ላይ የተለዬ ስልጠና እዬወሰደ ያዳብረዋል እንጂ እንደገና ወርዶ 7ኛ ክፍል ላይ ስለተፈጥሮ ሳይንስ ልማር አይልም። ምክንያቱም አቅም ፈጣሪው አዕምሮ ወደላይ ከመዝለቅ በስተቀር ወደ ታች መውረድን ስለማይፈቅድለት። አሁን ያለውን ቡቃያ የለወጥ መሻት በዛገ የምርኩዝ ጋጋታ፤ በወዬበ ኳኳቴ በፈለገው ዓይነት መጠራቅቅ መቋቋም አይችልም የአዳማ ሥርዕዎ መንግሥት። ይህ የለውጥ መንፈስ ከብሄራዊ አልፎ፤ አህጉራዊና ዓለምዓቀፋዊ ጫናም ፈጥሯል። ረቂቅ ነው። የፈጠረው ጫና በፍጹም ሁኔታ ኦህዴድ በሚያስበው መልክ በግርድፍ የሚሾከሾክ የገብስ ቆሎ አይደለም። በፍጹም። ሃሳብ ዬለም ብሎ አይመፃደቅ። • መታዬት። የዛገው ሙጣጭ ሃሳብ አዲሱን የለውጥ መንፈስን መቀበል ብቻ ሳይሆን ከአዲሱ መንፈስ ጋር ለመቀጠል እንኳን በግትርነት የሚሆን አይሆንም። የሚመጥን የአዕምሮ ብቃት፤ የሰብዕና ንጽህና፤ የሥነ - ምግባር ሞራል፤ የሥርዓት መዋቅራዊ ደርጁነት የለውም። ያስፈራውም ይሄው ነው። ቀውስ ባጀቱ የሆነውም ለዚህ

ነፃ የወጣ ኢትዮጵያዊ #የአዕምሮ ነፃነት!

ምስል
  ነፃ የወጣ ኢትዮጵያዊ #የአዕምሮ ነፃነት!     • ሃሳብ ነፃ የወጣ ነፃ የአዕምሮ ነፃነት ነው። ነፃ የወጣ ስል የአዕምሮ ነፃነቱ የትውስት ሰብዕናን፤ • የትውስት ፍልስፍናን፤ • የትውስት አቅምን፤ • በትውስት አዕምሮ የተፈጠረ ንድፈ ሃሳባዊ ቀመርን በፍጹም ሁኔታ የተጸዬፈ ነው። በአካልም በመንፈሰም የዬትኛውንም ሐገር ፍልስፍና ወይንም የኤኮኖሚ አቅም፤ ወይንም የዲፕሎማሲ ጫና አልሞ የተነሳ አይደለም የራስ አቅም ይህ ራሱን ችሎ በራሱ ጊዜ ነፃነቱን አውጆ የተነሳው ሃሳብ በቀጥታ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ወዳጅ የሆነውን ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነት ኢትዮጵያዊ ቀለም ሰጥቶ የተነሳ ከሆነ ስለሰው ግድ የሚላቸው፤ ስለተፈጥሮ ግድ የሚላቸው ባለ አዕምሮችን ቀልብ ሲስብ ፕሮፓጋንዲስት ወይንም ቀስቃሽ ወይንም በፕሬስ ውደሳ ተቀባይነቱ ጥገኛ አይሆኑም። ጥራት ያላቸው ማስተዋሎች ብቻ ይደግፉታል። ያ ደግሞ ለግብ ያበቃል። ዛሬ ሁሉንም በጋራ የሚያገናኘው አንድ ተፈጥሯዊ መርህ አለ #ሰብዕዊነት ። ከብዙ ቅን መንፈሶች ጋር የተሰራው ሃዲድም በዚህ መስመር ነው። • አንደኛ … በራስ ወገን የታሰብ ከሆነ፤ • ሁለተኛ … አቅሙ ስፋቱና መጠኑ ባለጥሪት ከሆነ፤ • ሦስተኛ … ከማንም እና ከምንም ከዬትኛውም ሐገር የውለታ ጥገኝነት የሌለበት ከሆነ። • አራተኛ … ሁሉንም በአኩልነት በእቅፉ ለማድረግ ከልቡ ከፈቀደ፤ • አምስተኛ … ተረስተው፤ ተዘንግተው የኖርትን ሁሉ ፍቅርን በገፍ ከሰጠ። • ስድስተኛ … ነገስ ለሚለው አደራውን ለመወጣት ያለው የህሊናው መሳናዷዊ አቅሙ ሙሉዑ ከሆነ፤ • ሰባተኛ ሲጠልፉ ሲያነቅዙ ለኖሩት ጠለፋ ካልተመቼ፤ ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያን ከነክብሯ፤ ከነግርማ ሞገሷ የእኔ ብሎ ከሚስጢሯ ከተነሳ ለቅኖች ቅደመ ሁኔታ ሳያሰኛቸው በመንፈሱ ተስፋን እንዲሰንቁ ያደርጋቸዋል። •

በ"ኦሮሚያ" ክልል እየተካሄደ ባለው የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ የህግ ትንተና: ለተጠያቂነት የቀረበ ጥያቄ ዋንኛው ማጠቃለያ

ምስል
  በ"ኦሮሚያ" ክልል እየተካሄደ ባለው የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ የህግ ትንተና: ለተጠያቂነት የቀረበ ጥያቄ ዋንኛው ማጠቃለያ     በ1960ዎቹ የዩንቨርስቲ ወጣት ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ የመንግስት ቋንቋ መሆኑን የጎሳ አማራን በኢትዮጵያ የበላይነት ስላሳሳቱ፣ አማሮች በኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ንግግሮች እና ግድያዎች በጋራ እየፈጸሙ ነው። በ1990ዎቹ የተቋቋመው የአፓርታይድ አይነት የብሄር ፌደሬሽን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የበላይነት ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በአማራ ተወላጆች ላይ የነበረው ጥላቻ በብዙ የኢትዮጵያ ክልሎች በአማራ ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ እልቂት እንዲፈጠር አድርጓል። እ.ኤ.አ. በ2018 በአማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ግድያ እና መፈናቀል እና መንደር ማቃጠል አስገራሚ ለውጥ የጀመረው አብይ አህመድ አሊ የተባሉ የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ በኋላ ነው። በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጸምበት ከ2018 ጀምሮ የኦሮሚያ ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ እልቂት ሲካሄድበት ቆይቷል።   መኢአድ እነዚህን በአማራዎች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ መዝግቦ የጀመረው የመርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ በማቋቋም ነው። የዚህ ዘገባ አላማ በአለም አቀፍ የወንጀል ህግ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተካሄደ ያለውን ስልታዊ ጭፍጨፋ ወንጀል ለማሳየት በአአ እና በሌሎች ከተሰበሰቡ መረጃዎች በመነሳት ነው። የዚህ ዘገባ የመጀመሪያ ክፍል (ክፍል አንድ) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን ስልታዊ ጭፍጨፋ መንስኤ እና ምንነት ለመወያየት ያለመ የዘር ማጥፋት አስር ደረጃዎችን ወይም “የ