ነፃ የወጣ ኢትዮጵያዊ #የአዕምሮ ነፃነት!

 

ነፃ የወጣ ኢትዮጵያዊ #የአዕምሮ ነፃነት!
 

 
• ሃሳብ ነፃ የወጣ ነፃ የአዕምሮ ነፃነት ነው። ነፃ የወጣ ስል የአዕምሮ ነፃነቱ የትውስት ሰብዕናን፤
• የትውስት ፍልስፍናን፤
የትውስት አቅምን፤
• በትውስት አዕምሮ የተፈጠረ ንድፈ ሃሳባዊ ቀመርን በፍጹም ሁኔታ የተጸዬፈ ነው።
በአካልም በመንፈሰም የዬትኛውንም ሐገር ፍልስፍና ወይንም የኤኮኖሚ አቅም፤ ወይንም የዲፕሎማሲ ጫና አልሞ የተነሳ አይደለም የራስ አቅም ይህ ራሱን ችሎ በራሱ ጊዜ ነፃነቱን አውጆ የተነሳው ሃሳብ በቀጥታ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ወዳጅ የሆነውን ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነት ኢትዮጵያዊ ቀለም ሰጥቶ የተነሳ ከሆነ ስለሰው ግድ የሚላቸው፤ ስለተፈጥሮ ግድ የሚላቸው ባለ አዕምሮችን ቀልብ ሲስብ ፕሮፓጋንዲስት ወይንም ቀስቃሽ ወይንም በፕሬስ ውደሳ ተቀባይነቱ ጥገኛ አይሆኑም። ጥራት ያላቸው ማስተዋሎች ብቻ ይደግፉታል። ያ ደግሞ ለግብ ያበቃል።
ዛሬ ሁሉንም በጋራ የሚያገናኘው አንድ ተፈጥሯዊ መርህ አለ #ሰብዕዊነት። ከብዙ ቅን መንፈሶች ጋር የተሰራው ሃዲድም በዚህ መስመር ነው።
• አንደኛ … በራስ ወገን የታሰብ ከሆነ፤
• ሁለተኛ … አቅሙ ስፋቱና መጠኑ ባለጥሪት ከሆነ፤
• ሦስተኛ … ከማንም እና ከምንም ከዬትኛውም ሐገር የውለታ ጥገኝነት የሌለበት ከሆነ።
• አራተኛ … ሁሉንም በአኩልነት በእቅፉ ለማድረግ ከልቡ ከፈቀደ፤
• አምስተኛ … ተረስተው፤ ተዘንግተው የኖርትን ሁሉ ፍቅርን በገፍ ከሰጠ።
• ስድስተኛ … ነገስ ለሚለው አደራውን ለመወጣት ያለው የህሊናው መሳናዷዊ አቅሙ ሙሉዑ ከሆነ፤
• ሰባተኛ ሲጠልፉ ሲያነቅዙ ለኖሩት ጠለፋ ካልተመቼ፤
ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያን ከነክብሯ፤ ከነግርማ ሞገሷ የእኔ ብሎ ከሚስጢሯ ከተነሳ ለቅኖች ቅደመ ሁኔታ ሳያሰኛቸው በመንፈሱ ተስፋን እንዲሰንቁ ያደርጋቸዋል።
• መውጫ።
ጊዜ እና ቦታ፤ ሁኔታ እና ዕድል የሚነሱትም የሚያሳጡትም አለ። … ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ሲሞላም ይፈሳል ሲከርም ይበጣሳል። እጬጌው ሂደትን ጠብቀኝ ማለት አይቻልም፤ አብሮ መጓዝ ብቻ ነው ምርጫው።
በስተቀር መንጠባጠቡ በመፈጥፈጥ ይሆናል። ሰማይን ንጋት እንዳይሰጥ የሚያደርግ ወይንም ጸሐይ ብርሃን እንዳትሰጥ የሚያደርግ የተፈጥሮ ህግ የለም።
ህግ ጣሹ በህግ ጥሰቱ ውስጥ ራሱን ጥሶ ግብዕቱን ይፈጽማል።
በዚህ አሰልቺ በሆነ ደንዛዛ አቅም - ጊዜ - ማቃጠሉ ቅራኔውን ቢያባብሰው እንጂ ሊፈታው አይችልም። ጨው ለራስህ ብትል … ይብቃኝ እነ እንቅልፍ ማህበረ ኦነጋውያን ከተለመደው የሄሮድስ መለስ አንቀልባ ጋር አንጎላቹ … ፍዝ።
ትንሽ ስለነገ ስላልተፈጠሩት የትግራይ ህፃናት የማታስቡ የግዴለሾች ናችሁ እላቸው ነበር ህወሃቶችን፤ ይህን አመክንዮን እኔ በጽሞና ያስገንዝብኳችሁን ስላልፈጸማቸውሁ ድቀት እና አመድ ማፈስ ለዛ ህዝብ እንሆ ሆነ።
ነገም የኦሮሞ ህዝብ ዕጣ ክፍሉ ይኸው ይሆናል። እርግጥ ነው አዲስ እሸት ዕሳቤ ይዘው የተነሱ ሞጋች ሰብዕናዎች አያለሁኝ ከኦሮሞ ማህበረሰብ። ይህ በጣም ወቅታዊ ልባም እርምጃ ነው። አብይዝም ሌንጮዊዝም አይወክለኝም ብሎ ደፍሮ የወጣ ብቃት፤ ልቅናውን ለመግለጽ አቅም እስኪያንስ ድረስ ምስባክ ክሰተት የሆነ አንበሶች እያዬሁ ነው።
ኢትዮጵያን ያመሷት ህዝቃዬሊዝም፤ ጃዋርይዝም፤ ለማይዝም፤ በቀለይዚም፤ ጉዲናይዚም፤ አራራሳይዝም ሁሉ ከማይችለው ፈተና ውስጥ ላይ ነው የሚገኙት። ቅባዕውም፤ ርጋታውም፤ ክህሎቱም የኢትዮጵያዊነቱም ህብራዊ ቀለሙም፤ የርህርህናው ዲካም የሰማዬ ሰማያት ነው።
ይህን መሰል የሰማይ ሽልማት በዘመነ ተጋሩ አይደለም በማለዳ በበሰበሰበት ሰዓት እንኳን አላዬሁም ነበር። ይህ የስጦታ አቅምም ቢሆኑ ባለው ነገር ላይ በቁንጣ ቁንጢ ንትርክ ጊዜያቸውን ካቃጠሉ መዳኛው ከባድ ነው።
በፍጥነት የተደራጀ ሊሠሩ፤ ሊሆኑ የሚገባቸው የተግባር ማሳዎች ሊኖሩ ይገባል።
• በምን?
• እንዴት?
• የት? መልስ መሰጠት ግድ ይላል … በዞግ ሶሻሊዝም በገዳ የጨለማ ጉዞ ብቻ ሳይሆን ገደልም ላይ ነው ያለችው ኢትዮጵያ። እናት ኢትዮጵያ አሳቻ መንገድ ላይ ናት። አብሮ ከመከስከስ ባስተዋል ፍጥነትን መጥለፍ።
• ማስታወሻ።
ይህ ፎቶዬ የልጅነቴ ነው። በዚህ ዕድሜ ትልቅ ኃላፊነት ነበረኝ። በዚህ ኃላፊነቴ ውስጥ የነበረኝ ስክነት ይገርመኛል። ማትራሰ ነፍቼ ቢሮዬ ነበር እማድረው። እጅግ ለሰማይ እና ለምድር የከበዱ ሊቀ - ሊቃናት ለኔ ፖለቲካ ሰብዕና ደክመዋል። ለፍተዋል። ብርቅ ነበርኩኝ። ሥራ አገሬ ነው። ትናንትም ዛሬም። ከወጣትነቴ ጋር ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮ በሰጠኝ ጸጋ ደስታን በማራቅ ግዴታን መወጣት በሚል ተላለፈን። ወጣትነት እና ጉልምስና ምን ያህል ይመጣጠኑ ይሆን? ጹሑፉን ለኩት እና በይኑት ቅኖቹ አዱኛዎቼ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ለዘንካታ አድማጭነታቸሁ ፍቅርን በአክብሮትን ልሸልም።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
25.03.2023 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ ከደልዳዋ ደርባበዋ ቪንቲዬ)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።