ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል።

 

ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል።
• ጨካኞች በሽተኛ ናቸው። እንደ ሙሉ ሰው ሊታዩ አይገባም።
• ጨካኞች ያልሰለጠኑ ናቸው። ሥልጣኔ ኢንተግሪቲ ነውና።
• ጭካኔ ዬአስተሳሰብ ድህነት ነው ወደ ኋላ አብራራዋለሁኝ።
ጭካኔ ዬድንጋይ ዘመን ህዳሴ ነው። ጭካኔ ሰብዕናን ገድሎ ጫካዊነትን ማነፅ ነው።
• ጨካኝ ሱፍ እና ገበርዲን ከረባት እና ቀሚስ አደለም ሰብእናዊ ቀለም ነው።
• ጨካኞች አመክንዮ ስለመፈጠሩ አያውቁም፣ እርካታቸው አመክንዮን መስቀል ነውና።
• ጨካኝነትን ለፋክክር ዬሚያቀርቡ ልሙጥ ሰብዕና ያላቸው ናቸው እና። እንሰሳነት ስለማያስቀና።
 

 
በኢኮኖሚ ሳይንቲስቶች ኋላቀርነት በኢኮኖሚ ዕድገት አለመመጣጠን ይሉታል። እኔ ደግሞ በአስተሳሰብ ዘሃ ዬህሊና ድህነት እለዋለሁኝ። ልቆ አይፈጠርም የሰው ልጅ። ቅዱሳን አሉ በቅብዓ ዬሚሰጡ። ነገር ግን ዬሰው ልጅ ዲግሪውን ቁብ አድርጎ አይፈጠረም። ሂደት ትምህርት ቤት ነው። መኖር ትምህርት ቤት ነው። ቤተሰብ ትምህርት ቤት ነው። የአኗኗር ዘይቤ ትምህርት ቤት ነው። ተፈጥሮ ትምህርት ቤት ነው።
ቀደመው ዬታነፁ፤ ዬተገነቡ ቅርስ እና ውርሶች ትምህርት ቤት ነው። ታሪክ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤት ዬግድ ዩንቨርስቲ መግባት ብቻ አይሆንም። ዕድሉን ያገኙ ሁለገቡን ተምረውበት ክህሎቱን በሥልጠና ያዘምኑታል። ይህ ለታደሉት ነው። ላልታደሉት ደግሞ ትውስቱም፤ ውራጁም ብርቃቸው ነው። አሁን ለፋንታዚው ልዑል ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የውሃ ዳንስ፤ የፓርክ ግንባታ፤ የኩሬ ውሃ ዋና ብርቅ እና ድንቃቸው ነው። ይህ ግን አንዱን ቤተ ጊዮርጊስ የሚሰጠውን ሚስጢር አቻ ሊሆነው አይችልም።
ግብግቡ ዬጭካኔው ውርስ የሥልጣኔውን ውርስ ተፃሮ ውድመት ላይ መባጀቱ ነው።
ኦነግ መራሹ የኦሮሞ ፖለቲካ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ ቀደምትነት ህመማቸው ነው። ወራሽነት ውጋታቸው ነው። በብልጫ አገር አበጅተው የቆዩ ማህበረሰባት አንጡራ ጠላታቸው ናቸው። ለምን? የአስተሳሰብ ድህነት ስላለ። እራሱ ቱሪዝም ስለምን እንደተደራጀ ብናኝ ዕውቀት ዬላቸውም። ትናንትን ከሰረዙት፤ ዛሬ ላይ ከጀመሩ ቱሪዝም አያስፈልጋቸውም።
የሰለጠኑ አገሮች እና ህዝቦች ወደ ኢትዮጵያ ዬሚተሙት የውኃ ዳንስ ለማዬት አይደለም። ያማ ሞልት ተርፎ። በዬሠፈራችን ፓርክ አለ። አሁን እኔ በመስኮቴ ፓርክ እያዬሁ ነው እምጽፈው። ግን ዬአክሱምን፤ ዬዘጌን፤ የላሊበላን፤ የፋሲልን፤ የጉዛራን ወዘተ መንፈስ የሰነቀ ያነበበ፤ ዬተረጎመ፤ ያመሳጠረ ቅንጣት ትርታ ዬለውም። እርግጥ ነው ይህ ሥልጣኔ ሲዘምን ዘመናትን ሲቆጥር ቅርስ ውርስ ይሆናል። ለዛሬ ግን ያለንበት ዘመን ውጤት ስለሆነ በቅርስነት አይታይም። አይንፋህ ስልጣኔ ነው።
የእኛወቹ የጭካኔ አንበሎች በሰው ልጅ ብቻ አይደለም ጭካኔያቸው በውርስ ቅርሳችን ላይም በመሆኑ በውጭ ጠላት ከተወረርነው በላይ ሊያመን፤ ሊያሳስበን ይገባል። ሙሉ አምስት አመት ፋታ አልቦሽ በጥድፊያ እያነደዱን ነው። ይህ ዬነበረን ጠልቶ፤ ተጠይፎ የመንቀል ደባ ከውስጥ ተጠንቶ እራሱን በቻለ ንቅናቄ አቅም ፈጥሮ ሊነቃነቅ ይገባል።
መጀመሪያ ግን አህዱ ከራስ ይጀምር። ምንም ነገር ጠልቶ ሳይሆን አክብሮ መጠዬቅን ይጠይቃል። ሌላው በደራሽ ዜና እዬተዋጡ ትናንትን እዬጣሉ ሰበርን ማንጠልጠል እያዋዙ ዬጀመሩት ወረራ አካልነት ይሆናል። ዕውነት ለመናገር ለዘመኑ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልግም። ፈጽሞ።
በራስ አቅም የሰከነ ለፎቶ ሸው እና ለከንቱ ውዳሴ ያልተንበረከ ተግባር በምግባር።
#ፎቶው ውዴ ብያንካ ከሉዘር ሜሴ ያነሳችው ነው።
እግዚአብሄር ይሥጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።