የለውጥ ሃሳብ።

 

የለውጥ ሃሳብ።
• የለውጥ ሃሳብ ሂደትን ማዕቀብ በመጣል ማስቆም ወይንም የታቆረ ማድረግ አይቻልም። በፍጹም። ተፈጥሯዊ ነውና!
„በታካች ሰው እርሻ፤ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን
ቦታ አለፍሁ። እነሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፤
ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል። የድጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“
(መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴፩)
 

 
• በር።
ለእኔ በማሰብ ልቅና የአስተሳሰብ ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ። የነቃው የህሊና ክፍል አዲስ ሃሳብ ሲያፈልቅ ሃሳቡን የሚቀበል ህሊና፤ አዕምሮ ሊኖረው ይገባል። ይህ አዕምሮ ያፈለቀውን አዲስ ሃሳብ የሚመጥን የሰብዕና አቅም የሚኖረው ከአቅሙ ከራሱ በመመንጨቱ ነው።
አዲሱ ልቅና ያለው አስተሳሰብ ሃሳብ የትውስት ወይንም የብድር አይደለም። ስለምን? አዲሱ ዬአስተሳሰብ ልቅና ካለው ከራሱ ህሊና፤ የአዕምሮ የአቅም ፏፏቴ የመነጨ ስለሆነ ዲስፕሊኑን የመሸከም ብቻ ሳይሆን በቅጡ አደራጅቶ የመምራት፤ የማስተዳደር አቅሙ ተመጣጠኝ ነው።
.. ብቻም ሳይሆን ሚዛናዊነቱ በራሱ የአዕምሮ የውሃ ልክን የሚያስጠብቅ ተጠባባቂ የሃሳብ ማህበር ዘብም ይኖረዋል።
እንደገናም የማህበራዊ ንቃተ ህሊናው የመሸከም ዲስፕሊን አንጻር ማዬት ይጠቅማል። ቀድሞ ነገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና አጀንዳው ሆኖ አያውቅም። መነሻ የሌለው መድረሻ ሲያልም የኖረ ልም።
• ምጥነት።
የወገቡ ስፋት 35 ሴንቲሜትር የሆነ ልብስ የ52 ሴንቲሜትር ስፋት ያለው ልብስ ቢጠለቅለት መዋኛ ገንዳ ነው የሚሆነው። ወይንም 35 ሴንቲሜትር የወገብ ስፋት ላለው 10 ሴንቲሜትር ስፋት ያለው ልበስ ቢባልም ይሄም በጅ የሚል አይሆንም። አሁን የገዳ ኦሮሙማ እና የምርኩዞቹ አዲሱ ችግርም ይሄው ነው።
ቢደረደሩ፤ ቢከመሩ፤ እንደ ተራራ ቢቆለሉ፤ አንደ አነባበሮ ቢነበባሩ ለጥ ብሎ በተኛው የዛገ ሃሳብ ውስጥ ከመዝገጥ በስተቀር ዘለግ ብለው የመታዬት አቅምም ወርድም የላቸውም። አዲሱን ሃሳብ የአዕምሮ ደረጃ የሚመጥን አዕምሮ የላቸውም። አንድ ሰው ቁመቱ የሚያድገው አስከ ተፈቀደለት ድረስ ነው። ያማ ባይሆን ሰማይ ጠቀስ ይሆን ነበር የሁላችንም ቁመት።
አሁን የእነሱ ገዳኢዝም በጎሳዊ ቀመር ፍልስፍና እደግ ተመንደግ እዬተባለ ነው። ግን ያረጠ ነው የ50በ60 ህልም። የነርብ ሲስተሙ ከዚህ በላይ መሄድ አይችልም። አቅም የለውም። ዘመኑን መሸከም አይችልም። ወይ ይፈነዳል ወይ እንደ በለመደበት ለሽ ብሎ ይተኛል።
ይሄ ስለተባለ ሳይሆን የዕድገት ሂደት ነባራዊ ሁኔታዎችና ተፈጥሯዊነት የሚያስገደዱት ረቂቅ ህግ አለ። ይህን የእድገት ህግ በሰው እጅ አንቦልቡሎ ወይንም ጠፍጥፎ ማስኬድ አይቻልም። አዲስ ሃሳብ በራሱ አዕምሮ እድገት የሚፈጠር ብቻ ነውና።
ስለዚህ የአማራ ፖለቲካ ብናኝ ትምህርት ከማይገኝበት ልሙጥ ፖለቲካ ጋር ፋክክር፤፦ግብግብ ሳያስፈልገው የራሱን የነጠረ አመክንዮ አስክኖ፤ አብስሎ፤ አጥርቶ በትውስት አማካሪ፤፦በውራጅ ምንድስና ሰናጅነት ሳይሆን ራህቡን የሚያውቀው እሱ ነውና እራህቡን የሚፈውስበትን ጎዳና በሰውኛ እና በተፈጥሮኛ ዘይቤ እና ውስጥነት ሰክኖ ሊነድፍ፤ ደንጎ ሊሆንበት ይገባል። ጉዞውን ታካችም፤ አታካችም ማድረግ ግፍ ነው። የደከመን ሰወች አለን። ተጨማሪ ጉዳዮችን ለማስተናገድ የሚቸግረን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።






  •  
    Shared with Public
    ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል።
    • ጨካኞች በሽተኛ ናቸው። እንደ ሙሉ ሰው ሊታዩ

    አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    አብይ ኬኛ መቅድም።