ዙሬያው ትሬኮላታ አልጋውም ረግረግ ውጦታል።

 

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
#ዕዳ ከሜዳ።
በግንቦት 7 የእጅ ሥራ የኤርትራ እና የኦህዴድ ድርድር በሠርግ እና መልስ ተንቆጥቁጦ ባጅቶ ነበር። አሁን ግን ገርባባ እዬሆነ ነው።
አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ዋና ፍላጎታቸውን በማንቆርቆሪያቸው አሰሩንም፣ ጉሹኑም፣ አንቡላውንም ያንዶለዱሉና እሳቸው እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ታጥበው በኢትዮጵያውያን የተለመደው ቀዶ መድፈን፣ ወታትፎ ወቅት ማሳለፍ በሻብያ ይገኛል ብለው አስበው ነበር፣ እንዲህ ዘውታ የለም።
 
እኔ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ዘገባም ሳይመከርበት ሆኗል ብዬ አላስብም። ጫና እንዳለባቸው ለኤርትራ መንግስት ለማሳወቅ እሳቸው የሠሩት ዳንቴል ነው ብዬ አምናለሁ።
 
የተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ የአሜሪካ ጫና እና ከዛ የቀረበው የአማራ ተቋማትን ውንጀላ የአማራን ልዩ ኃይል ለማስወጣ ከግርባው ብአዴን ጋር ስምምነት አለበት፣ የአማራ ህዝብን ጫና አለብኝ እንዲል ግርባው ብአዴን ብዬ በዕለቱ ፅፌ ነበር።
ስለ ኤርትራ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ዘገባ፣ የአሜሪካ ልዑክ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ፣ የተወካዮች ምክር ቤት ድንገቴ ጉባኤ ሁሉም በአንድ ወቅት ነው የተከወነው። ግልቢያውን አስታግሶ ሁሉንም ነገር በስጋት ማዳመጥ ይገባል። 
 
እኔ በኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን እምነት ስላለኝ ነው ይርዱን ብዬ አክብሬ አቤቱታ እማቀርበው። ዘገባው ጥሩ ሆኖ ግን ዘገባው የወጣው በኮሚሽኑ ተነሻሽነት ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል።
 
ይህ ጫና እንዲመጣ ጠቅላዩ ስለፈቀዱ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህን ያደረጉበትም የአሜሪካን ፈቃድ ለመሙላት ችግሩን ከሳቸው አርቀው ለመወርወር ነው ብዬ ነው እማምነው። ብልጠት ብልህነት አይደለም። 
 
ብልጠት ሁሉንም አንድ ቀን ያሳጣኃል። የግንቦት 7 መንገድ ይህ ነበር። ተው ብዬ ፅፌያለሁ። እንዲህ ዘነዘናቸውን ሊቀሩ አስቀድሜ። ከ6/7 ዓመት በፊት። 
 
ዕውነት በትናታም፣ በእንጥሽታም፣ በህቅታም፣ በሳቅም፣ በስላቅም ካሰኜው ገልጦ ያስረክባል። እጅም ያሰጣል። ኤርትራ የሄዱት እጅ ለመስጠት ነው። 
 
አንድ ጊዜ የእስራኤል መንግሥት ሞገታቸው። በጓዳ ተሸሽገው ምልጃ ይዘው ሄደው ተማጠኑ። የሰኔ 15/2011 የአማራ ሊቃናት፣ ልዩ ኃይል ርሸና ጊዜ። ያዳፈኑትን አዳፈኑ። "በኢሱ" ቤት ግን ቀልድ የለም።
የዳመናው ዝናብ እያረሰረሰው የተካሄደው ኦነጋዊዊ ፓርላማ የሙሉ ቀን የዲስኩር ቋት ብዙ ነገር ዘርጥጧል። ብዙ ፍንጭ እረጭቷል። ብዙ እንዘጭም አቦካክቷል።
 
"የኢሱ እና የአብይዝም" የልብ ስንብትንም አውጇል። ቅርቃሩ፣ መጠራቅቁ፣ የሙሽርነት ዘመኑም፣ የጫጉላ ሽርሽሩም ቡላማ ሆኗል። አጋፋሪው ግንቦት 7 በድንጋጤ አመዱ ቡን ሳይል አይቀርም። የልደት አምላክ የት ሄዶ? ገናም ገና …
 

ዙሬያው ትሬኮላታ አልጋውም ረግረግ ውጦታል። ቅጥፈት፣ ክህደት፣ ውሸት አብሮ አይቆምም። ቀድሞ ነው እግሬን አውጭኝ የሚሉት።
መለመላህን ስትቆም ገመና ከታችም ከዋኝም የለም። "ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፣ አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ" የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት በልኩ ራስን ሳያዋርዱ፣ የቡና ተርቲመኛ አሳላፊም ሳይሆኖ መቀራረቡ መልካም ነበር። አገርን፣ ትውፊትን፣ ትሩፋትን ማውረስ ግን ዋልጌነት ነው። የኃላፊነትን ልክም አለማወቅ ነው። 
 
ይህ ሁሉ ምስቅልቅል የአሳቻ ሰብዕና መከራ የፈጠረው ነው። ከእንግዲህ በኋላ የጓዳ ፍቅር እስከ መቃብር ወደ እንጦርጦስ ተልኳል። ቀልድ የለም "በኢሱ" ቤት። መንቦጫረቅም። 
 
ብቻ ኢትዮጵያን ማወቁ ነበር ጠቃሚው ነገር። ታላቋ አገር በዘመነ አብይዝም ማዕረጓን ተገፈፈች። ተፈሪነቷን ተቀማች። ተዘጋች። ተኮደኮደኮደች። ኳራንቲ አስገቧት። አዝናለሁ።
 
ኤርትራ ጎረቤት አገራችን ናት። ተከባብሮ፣ ተቻችሎ መኖር ሲቻል ግን ቁልፋ ተሰጣት። አሳቻነት ያበቀለው አረም በምን ጥበብ ታርሞ በቀደመ ትውፊቷ ልክ ኢትዮጵያን ማስከን እንደሚቻል አንድዬ ይወቀው። "በታቲንካ፣ በታቲንካ" ዕውን ሆነ። ያለ ከልካይ። የዚህ እንኩሮ አጋፋሪ አቤቱ ግንቦት 7 ነው። ሁሉም ተያይዞ እንዘጭ።
ትውልድ ሆይ! የት ነህ? አድራሻህ ጠፋብኝ። 
 
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
ጎዳናዬ መርኽ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።