ቤተሰባዊ መሪነት ፍቅር በፍቅር ከስደተኛ ወገኖቹ ጋር። ተመስገን!
ቤተሰባዊ መሪነት። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን የቃናለታል፤“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አሁን ያገኘሁት ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጀርመን ርዕሰ መዲናው በርሊን ላይ የጠበቋቸውን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸውን በፍቅር ተቀብለዋል። ያው ጠ/ሚር አይመስሉም ልክ አብሮ አደግ ጓደኛ ነው የሚመስሉት። መቼም የጀርመን መንግሥት ሳይገረመው አያቀርም። ዕድሜ ልክ በመቃወም የኖረ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ዛሬ ከሙሴው ጋር እንዲህ በፍቅር እቅፍቅፍ ብሎ ሲሳም ሲታዩ እጅግ ያስደስታል። አብሶ ሥርጉትሻ ሐሴቷ ዝቀሽ ነው። አላሳፈሩኝም። ባይበላም ባይጠጣም ጥሩ ነገር ነው እንዲህ ቤተሰባዊ መሆን። አብሶ ስደተኛ ብዙ ነገር አጥቶ ስለሚኖር መቼም ይህ የሰማይ ስጦታ ነው። ተመስገን። እኔ ከስሜን አሜሪካውም ደመቅ ዓውድ ይልቅ ይህ በለጠብኝ አቀራረቡ እና ውስጣዊ እቅቅፉ ይሄ ላቀብኝ፤ የፈንሳዩንም አይቸዋለሁኝ የበርሊኑ ግን እኔ እንጃ ልክ የአገር ቤት ቤተሰባዊ ጠረን አለው። ያው ከተደጋጋሚ ሞት እና አፈናም ወጥተው ነው ለ ዓይነ ሥጋ የተበቃው። እንደ ገና የመፈጠርም ያህል ነው። ብዙ የተከደኑ ነገሮች እዮር የሚያውቃቸው አሉና። ብቻ ተመስገን ነው። እስኪ ይጨርስለዎት! የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።