በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚ/ር ፈጽሞ አያምርም።
በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚ/ር ፈጽሞ አያምርም። „እሳት በረድ ረሃብ ቸነፈር ይህ ሁሉ ሊበቀሉበት ተፈጠረ“ መጽሐፈ ሲራክ ፴፱ ቁጥር ፳፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute© Selassie 24.03.2019 ከእመ ዝምታ ከሲዊዝ። https://www.youtube.com/watch?v=aGQfuWK7MD4 ጠ / ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ ወግ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረጉት ንግግር ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት አንድ ንግግር ነበራቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ። አሁን አሁን ሌላ ሰው ሌላ ሰው እዬመሰሉኝ ነው። ምን ነካቸው የምለው እኔ ብቻ አልሆንም ብዬ አስባለሁኝ። ከእኛም አልፎ የመንፈስ ወርቅ ለህሊናቸው ያነጠፈላቸው ሉላዊው ዓለምም በትዝብት ሳይመለከታቸው አይቀርም ብዬ አስባለሁኝ። ለነገሩ አንድ ጠንከር ያለ ጥራዝም ወጥቷለኝ። እሳቸውን ለመወቅስ ለመተቸት ማሰቡ በራሱ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ቢያውቁት ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር። ዳሩ በእኛ ውስጥ ስለሌሉ ጭንቁና ችግሩን የተረዱት አይመስልም። እጅግ ነው የሚቸግረን አንድ ብሄራዊ መሪ ለመተቸት። በሁለት ምክንያት። አንደኛው ባህላችን ሲሆን፤ አብሶ እንደ እኔ ወግ አጥባቂ ክፍለ ሀገር ላደገ ሰው ፈተና ነው። ሁለተኛው ደግሞ እኔ በሳቸው አክቲቢዝም ላይ ተግቻለሁኝ። እንዲያውም እንደ እኔ በሳቸው ላይ በ አዎኢንታዊነት የጻፈም አለ ብዬ አላስብም። እኔ ብቻ አይደለሁም የሳተናው ድህረ ገጽም እጅግ ትጋት ነበረው። በጣም ቅን በሆነ የተስፋ ጥበቃ መልካሙን ሁሉ ተመኝተናል። ተቀናቃኝ ሃሳቦችን ሞግተናል። ቅራኔ ውስጥ ገብተናል። ው...