ልጥፎች

ከጁን 6, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የእኔ ትእግስት።

ምስል
                    የእኔ ትእግስት ስናፍቅሽ ወይንስ ስመኝሽ                      እሙዬ የትኛው ሥም ይሻልሽ ይሆን?                                      ከሥርጉተ ሥላሴ 05.06.2018 (ከጋዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።)             „እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤ እርሱ ለቅኖች ደህንነትን ያከማቻል፤                 የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናልና። ( መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ከ፮ እስከ ፰ ) ·          በር። አቶ ዛሬ እምር ብሎበት ነበር የዋለው በገበርዲን በከረባት ሽቅርቅር ብሎ ወሸቤም የቆዬ መስሏል። ንግሥቲቱም ፏ ብላ በሠረገላ ተኮፍሳ አገር ምድሩን እያፍነከነከችው ነው። እልፍኟ ኑብኝ ይላል። አልባብ ባልባብ፤ ታዲያንላችሁ ሥርጉትሻ ምኗ ሞኝ። እሷም የአቶ ዛሬን ግምጃ ቤት ለመታደም በልክ በሆነ ዝነጣ ወጣ አለች። ግን ምን አለ ሁልጊዜ እንዲህ ብትሆን ይህቺ የአውሮፓ ቅምጥል። ሰዉ ይስቀላ። ቀሎታል። ደስ ብሎታል። ታውቃላችሁ አይደለም? የሆነ አውሮፓ የሚጫን ደመመን ነገር አለው። ክብድ የሚል። ግን ዛሬ፤ ዛሬማ የእምዬን ያህል አምሮበታል። አድባሩ። ውይ ሳልነግራችሁ እነዛ ጥፍት ብለው የከረሙት ባለክንፎቹ ባንዳቸውን ይዘው ከች ለበጋ እረፍት። በጥዋት የቀሰቀሰኝ የእነሱ የንጋት ማህሌት ነበረ። ተዛንላችሁ ትንሺ ዘወርወር ብዬ መለስ አለኩኝ እና ወዜን አሳርፌ ማለት ነው፤ ያው የዘወትር የሀገር ቤት የዜና ኬወስክ እናቱ ይባል አባቱ ይባል ብቻ የአንጀት አድርሱ አይዋ ዩቱብን ከፈት ሳደርግ የምወድሽን ግኝት። ዛሬ ወግ በወግ ሆንኩኝ አይደለ … ብርሃን ደስ ይላል። በጠሐይ ጥንቢዝ ብሎ መስከር