ትንሽ ስለጤናችን። #ግራዋ ለነስር ቀጥ እንደሚያደርግ ስለመሆኑ እኔም #ምስክር ነኝ።
#ትንሽ ስለጤናችን። #ግራዋ ለነስር ቀጥ እንደሚያደርግ ስለመሆኑ እኔም #ምስክር ነኝ። ለሆድም ለመጋኛ ይጠቅማል። ቁርጠቴ ሲነሳ በጣታቸው ለክተው ቤተሰቦቼ ይግቱኝ ነበር። ታዳጊ ወጣት ሳለሁኝ። የስለት ልጅ ስለነበርኩ ጤናው የዚያን ያህል ነበረና። የሆነ ሆኖ እኛ ደሃ ያልሆን ማን ደሃ ይሁነው። ወርቅ አፍሰን ወርቅ ለመሸመት ለመለመንም እንጀግናለን። ስንት ጥበብ በጥበብ የተቃኜች አገርን ፀጋ በረከት ተሰጥኦ፦ ማክበር ተስኖን እንሆ ከድህነት ወለል በታች ሥር። ቢያንስ የቀደምቶችን የጤና በረከቶች እስኪ አክብረን እንጠቀምባቸው። ከዚህ የባህል መዳህኒቶች ቅዱስ ነው የሚባሉት። የተፈጥሮ የሚባሉ ፈርማሲወች፤ ሃኪሞችም አሉ። ኢትዮጵያ እንዳለ አሁን አሁን ባደምጥም ይህን ያክል ዕውቅና ግን ያገኜ አይመስለኝም። ሥርጉትሻ 13/3/2025 ፌስቡክ ላይ ያገኜሁትን መረጃ እንሆ። "ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀትGeneral knowledge ethiohakim reotpSnodst01808 2m11ah48f3,ffct9a2f8035021agc98rM3h9t342i3" · ግራዋ «ሳይንሳዊ ስሙ ቨርኖኒያ አሚግዳኒና (Vernonia amygdalina) ይባላል፡፡ ለጽዳት፣ ለምግብነት፣ ለአጥር፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለሰው እና ለእንስሳት መድኃኒት እና ለሌሎችም ብዙ ነገሮች ይጠቅማል፡፡ አገራችንን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካ አገራት በተለያየ መጠሪያ ይታወቃል፡፡ ለምግብነት በምዕራቡ የምድር ወገበ አካባቢ ያሉ የአፍሪካ አገራት ቀንበጡን ግራዋ ለሾርባ ወይም ለወጥ ይጠቀሙታል፡፡ በምዕራብ ታንዛኒያ ውስጥ በታንጋኒካ ሐይቅ ምሥራቃዊ ክፍል ነዋሪ የሆኑት እነ ቶንግዌ (Tongwe) ለመድኃኒትነት በውሃ ዘፍዝፈው በቀዝቃዞው ለወባ፣ ለአንጀት ...