እንኳን ደስ አለህ አዴፓ¡ „ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፵፱ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 18.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ · እ ፍታ። የኔዎቹ እንዴት ናችሁ፤ ብዙ ሰው ሹመቱ የራሳቸው ነው እኛን ምን አገባን የሚሉ አሉ አሁን እኮ መንግሥት አለ ብለን ስለምናምን እንጂ እኔ አዲትም ቀን በሹመቶቻቸው ዙሪያ ጽፌም አላውቅም፤ ፓርላማም ጉባኤውን በትጋት እማዳምጠው ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ነው። ሌአለው ቀርቶ እዚህ ሲዊዘርላንድ ማን አንባሳደር እንደሆነ፤ አንባሲው ቢሮው አድራሻው የት እንደሚገኝ ሁሉ አላውቀውም፤ ምን ይዶለኛል፤ ምንስ ያገበኛል፤ እኔ ዜጋ አይደለሁምና። አሁን አስተያዬት የምንሰጠው የ እኔ ከማለት ነው እንጂ ይህን ራሱን አይተን አይተን እናቆመዋለን። እኔ በተለይ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት ብቻ ሳይሆን ከስሜን አሜሪካ መልስ ጠ/ ሚሩን የማስወገድ አደጋም ተደርጓል ብዬ አስባለሁኝ፤ ምክንያቱም አብዩን አሜኑን እጅግ አቅርቤ አዬ ስለነበር ፈጣሪ መልዕክት ልኮልኛል ብዬ አምናለሁኝ። ያ ሳይሳካ ሲቀርም እገዳ ማዕቀብ፤ ቅደመ ሁኔታ ተቀምጧል ብዬ ስለማስብ አሁን እዬሆነ ያለው ነገር ብዙም አልደነገጥበትም። እኛ ነው እየሠራን ያለነው እያለን ...