ልጥፎች

ከዲሴምበር 23, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ" BBC እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው።

    እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው። ክፋ ሃሳብን ያነገቡ ሰብእናወች ዓለማችን የጥፋት እና የመከራ በማድረግ ፈሪ ትውልድ ይሻሉ። የጭካኔው ዓይነት ይዘገንናል። ይህን ጭካኔ የሚገታ ወይንም የሚመክት ተቋም አለማችን ምን አላት? የሚያስፈራኝም ይሄ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c23vezjzgzdo   "ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ"   23 ታህሳስ 2024, 07:49 EAT "በኒው ዮርክ አንዲት ሴት ባቡር ጣቢያ ውስጥ በእሣት ተቃጥላ መገደሏን ተከትሎ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል። የፖሊስ ኮሚሽነር ጄሲካ ቲስክ እሑድ ዕለት የተፈፀመውን ጥቃት "አንድ ሰው ሌላ ሰው ላይ ከሚፈፅማቸው እጅግ ዘግናኝ ወንጀለኞች መካከል አንዱ" ሲሉ ገልፀውታል። ኮሚሽነሯ እንደገለፁት የተገደለችው ግለሰብ 'ስቴሺነሪ ኤፍ' ከተባለው ጣቢያ ወደ ብሩክሊን እያቀናች ሳለ ነው አንድ ሰው መጥቶ በእሣት መለኮሻ (ላይተር) ልብሷን ያቀጣጠለው። ግለሰቧ እዚያው ባቡር ጣቢያ ውስጥ ስትሞት ተጠርጣሪው በተማሪዎች ጥቆማ መሠረት ሌላ ባቡር ሲሳፈር በቁጥጥር ሥር ውሏል። ፖሊስ እንዳለው ስሟ ያልተጠቀሰው ሴት እሑድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ጥዋት 1፡30 ገደማ ነው ባቡር ስትሳፈር አንድ ሰው የተጠጋት። ከጥቃቱ በፊት በሁለቱ መካከል ምንም ዓይነት ንግግር አልነበረም ያለው ፖሊስ ሁለቱ ሰዎች ይተዋወቃሉ ብሎ እንደማያምን አስታውቋል። በባቡር ጣቢያ ያሉ የፖሊስ መኮንኖች እሣቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብ ከሥፍራው ሮጦ ማምለጡ ተሰምቷል። "በባቡር ጣቢያው በላይኛው ክፍል ላይ የነበሩት ፖሊሶች በሽታ እና በጭስ አማካይነት እሣት መነ...

"በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ" BBC እኔ ደግሞ ... የዚህ ሥርአት #በቀለኝነት እኮ #የዲያቢሎስ ዓይነት ነው።

    የዚህ ሥርአት #በቀለኝነት እኮ #የዲያቢሎስ ዓይነት ነው። በእጃቸው ያሉ እስረኞችን እንዲህ እንዲሰቃዩ ማድረግ #አረማዊነት ነው። ሃይማኖት አለኝ የሚል ስርዓት በእነኝህ የአማራ ሊቃናት ላይ የወሰደው፤ በመውሰድ ላይ ያለው በቀላዊ እርምጃ ነገን #ያከስለዋል ። ዛሬንም #ቃሬዛ ላይ ያውለዋል። ከዚህ ቀደምም የአማራ ባንክ ትጉህ ሰራተኛ በቁሙ እስር ቤት ገብቶ አስከሬኑን ነው ተረከቡ የተባለው። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና አሁንም የሚፈለገው ይህ ነው።    በየትኛውም ሁኔታ የሚደረጉ የህልውና ተጋድሎወች በብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርጉበት የሚገባውም በዚህ መሰል አመክንዮ ላይ ያስተዋለ የፖለቲካ አቅም መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። በድንገቴ ግጥግጦሽ ስልጣኑን የተረከበው ማህበረ ኦነግ በአዲስ ዘይቤ መምጣቱ አይቀሬ ነው። የአማራ ቅን ህዝብ አቅሙን ቆጥቦ በስርዓት አቅሙን የማስተዳደር ግዴታ አለበት። የአማራ ህዝብ #መታመኑን ከእነ ሙሉ አቅሙ አስረክቦ ነው "ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቁሞ ማውረድ ይቸግራል" እንደሚባለው የሆነው።    የአማራ ህዝብ አመድ አፋሽ ነው። ሙሉ ድምፁን ሰጥቶ በወዘተረፈ የበቀል ዓይነት ሙሉ ስድስት አመት ተቀጠቀጠ። እንዴት ህመም ላይ ባለ ሰብዕና ይጨከናል? አንዴት? ለምንስ????    ይህ አስተምህሮ ነገንም በማስተዋል ማደራጀት እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው። እየዳሁ ያሉ አመክንዮወችን አያለሁኝ። ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቁ። በዳግም "በኢትዮጵያ ሱሴ" መደናገር እንዳይኖር ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ማህበረ ኦነግ መንፈሳቸው የሚቀዳው ከአንድ ነውና። አይደለም የይዘት የቅርጽ ልዩነት የላቸውምና። አህቲ ናቸው። እየገዙም የማይጠግቡ። እየገዙም የማይረኩ። ይሉኝታየሚባል ያልሰራላቸው።   ...