#በኖኽ #መርከቡ የአባይ ብሥራታዊ ዕጹብ ብራንድ ትልም ፍፃሜ እንኳን ደስ አለሽ ልዕልት ኢትዮጵያ! በልጆችሽ የተግባር ልዕልና #ልዩው #ብራንድሽ ለወግ በቃልሽ! !#እሰይ! ዛሬ ለእኔ ዕንቁ #ብሄራዊ ቀኔ ነው።
#በኖኽ #መርከቡ የአባይ ብሥራታዊ ዕጹብ ብራንድ ትልም ፍፃሜ እንኳን ደስ አለሽ ልዕልት ኢትዮጵያ! በልጆችሽ የተግባር ልዕልና #ልዩው #ብራንድሽ ለወግ በቃልሽ! ! #እሰይ ! ዛሬ ለእኔ ዕንቁ #ብሄራዊ ቀኔ ነው። "አድርገህልኛል እና አመሰግንሃለሁ።" ዘለግ ያለ ጹሁፍ ነው። ለቅጽበታውያን ሳይሆን የተረጋጋ፤ የጨመተ መንፈስ ለተመረቀላቸው፤ የትውልድ ጉዳይ ህሊናቸው ለሆነ ቅኖቼ የተፃፈ ማስታወሻ ነው። አመሰግናለሁኝ ጊዚያቸውን ለእኔ ለሚሸልሙ አዱኛወቼ። #መርኃች ሆነ መሪያችን የዕውነት ተፈጥሮ ይሆን ዘንድ እንፍቀድ። ትሁታዊ ልመናዬ። ይህ ከደስታ በላይ ሐሤት ነው። ከምድር እስከ አርያም ፍጹም የሆነ ልዩ ቅዱስ መንፈስን የሚመግብ። የሰው ልጅ አለሁ፤ እየኖርኩ ነው ማለት የሚችለው ዕውነትን #የማይፈራ ሲሆን ብቻ ነው። ዕውነት ለቤት እና ለዱር እንሰሳት - አልተፈጠረም። ዕውነት ለጋራ ሸንተረሩ - አልተፈጠረም፤ ዕውነት ለወንዝ ፏፏቴ - አልተፈጠረም። ዕውነት ለዝናብ - አልተፈጠረም። ዕውነት ለወጀብም - አልተፈጠረም። ዕውነትበዕውነትነት የተፈጠረው የሰው ልጅ እንዲኖርበት ነው። ዕውነት የሆነውን ዕውነት፤ ሃሰት የሆነውን ደግሞ ሃሰት ማለት ይገባል። በዘመናችን ታላቅ የተግባር ተጋሎ ለስኬት ሲበቃ የእኔ ማለት ይገባል። ሊቀ ትጉኃንን ለማመስገን ቆጥቋጣ ልንሆን አይገባም። #ኢትዮጵያዊነት ሜዳ በቀል አይደለም! ኢትዮጵያዊነት የእዳሪ ግኝትም አይደለም። የዊዝደም እንጂ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መሥራችነቷ፦ ኢትዮጵያ የዓለም አንድነት ከመሠረቱ ቀዳሚ አገሮች መመደቧ፤ ኢትዮጵያ የቀጥታ ቅኝ ግዛትን፤ የእጅ አዙር ቅኝ ተገዥነትን...