ልጥፎች

ከሜይ 21, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እንኩሮ (የወግ ገበታ)

ምስል

እንኩሮ (የወግ ገበታ)

ምስል
  እንኳን ደህና መጡልኝ   እንኩሮ። ። „እኔም ተመለስሁ ከፀሐይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዬሁ   እነሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፏቸው እጅ ሃይል ነበር፣ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።“ መጽሐፈ መክብብ ፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 21.05.2019 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        እ ፍታ። እንዴት ናችሁ ቅኖቹ የአገሬ ልጆች? ሰሞኑን ወጀቡ፣ ብርዱ፣ መከፋቱ ሁሉም ተዳምረው ቪንቲን ጨገግ አድርጓታል። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? የዕለቱ እርሴ እንኩሮ ይላል። እርስ ሰጥቼ መጻፍ አይሆንልኝም። እንደ እርእስ መስጠት አድካሚ ሥራ የለብኝም። ጹሑፍ ከጨርስኩኝ በኋዋላ ነበር እርእስ የምሰጠው። ዛሬ ግን አደላድዬ ለ እሱ ዘውድ ከደፋሁ በኋዋላ ነው አህዱ ያልኩት፤ ይሳካልኝ ይሆን? አይታወቅም እንፈታተን … አንላቀቅም ዛሬ … አልኳችሁ ድሮ ድሮ ታላቅ እህቴ ነበር የምትሰጥልኝ አገር ቤት እያለሁኝ። አሁን ግን ብቻ መጋፈጥ ነው። ፈተና! እኛ አ ነኮ ር ነው ወይንስ እሱ አነኮ ረ ን ወይንም እኛ እና እሱ ተዳብለን ተነኳኰርን? ወይንም እንደ ዘመኑ ቋንቋ እንደ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሥናዊ አገላለጽ „ተደምረን አነኮርነው“ ወይንስ እንደ ቀደመው እንደ አቶ ልደቱ አያሌው ስሪት በሦስተኛ መንገድ ተነኳኰርን ይሆን? አይታወቅም። ብቻ መንገዳችን ጠፍቶብን ያለው በአነኳኰራችን ላይ በደረሰው የምህንድስና የሰልት አፈጣጠም አደጋ ይመስለኛል። ሽሚያ ላይ መሆናችን ደግሞ ነው የሚገርመው። ስለምን ወደ ቅንጅት ተመለስን ይባላል? ያን ድል እንደግመዋለን የሚሉ ነፍሶች እስካሉ ድረስ ግድ ያላል ምልሰት ማድረግ … ደግሞ ታሪክ ነው የትውልድ