ልጥፎች

ከኤፕሪል 14, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#እባካችሁ #ተለመኑን።

ምስል
  #እባካችሁ #ተለመኑን ።    ቃለ ምልልስ የምትሰጡ አታጋዮች ቢያንስ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ወገኖቻችሁ ትንሽ እሰቡ። ምን ይሁኑላችሁ? ታስረዋል እኮ? ዕድሜ ልክ ይፈረድባቸውን? ወይንስ የሞት ፍርድ ወይንስ ይሰውሩላችሁ ምን ይሆን ፍላጎታችሁ? ሌላ በስልክ የምታገኟቸውም ቢሆኑ አጋጣሚን ልትቆጣጠሩት ስለማትችሉ ነገ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አታውቁም እና ሥም ከመስጠት ታቀቡ። እባካችሁ ተለመኑን። እባካችሁ።   ከታሠሩ፤ ከተሰው በኋላ ማን አስታውሷቸው ያውቃልና? ቀንቷቸው ሲፈቱ ደግሞ እናንተው ቀዳሚ አዛኝ ሆናችሁ ትገኛላችሁ። ጋዜጠኛ ይጠይቃል። መብቱ ነው። ተጠያቂ ጥያቄው ይለፈኝ ማለትም ይችላል። መመለስ ግድ አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም። ከጀማሪ ታጋይ እንኳን አይጠበቅም በሁሉም ዘርፍሁሉም ካለው ሲሆን ያማል። አሁን እኮ እሳት ረመጥ ነው ያለው አገርቤት። በስልክ የሚሰጡ ትዕዛዞችም ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ነው። እግዚአብሄር አምላክ የፈጠረልንን ማስተዋል አብዝቶ በልቦናችን ያስርጽው አሜን።   ስለ እስረኞቻችን ትንሽ ርህራሄ ይኑር። ቤተሰብ፤ ትዳር ልጅ ከሁሉምእናት አለች ያቺ መከረኛ። ሌላው ሁሉም በአቅሙ፤ በችሎታው፤ በፀጋው ብቻ ቢሳተፍ መልካም ይመስለኛል።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ስህተት የለበትም። የሌለበትን፤ ያልነበረበትን አወቃቀር እና ሂደት ለማወቅ ነው ጥረት ያደረገው ከሚያውቀው መረጃ ጋር አቀናጅቶ ለተነሳበት ዓላማ መስመር ውስጥ ለማስገባት። መታሰብ ያለበት ግንጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊም ሆኑ ምክትል ጠቅላይ ሚር ተመስገን ጡሩነህ ሙያቸው ስለላ መሆኑን ነው። ይህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ክስተት ነው። ክስተቱ በተለምዶ ዘይቤ ሊታይ አይገባም። እጅግ ጥንቃቄ ይጠይቃል

አንተስ እንዴት ሆነህ ይሆን? ድንግልዬ አብራህ ትሁን። አሜን።

ምስል
  አንተስ እንዴት ሆነህ ይሆን? ድንግልዬ አብራህ ትሁን። አሜን። እናትህስ እንደምን ሆነው ይሆን? ድንግልዬ ትርዳቸው። አሜን። ውቦቼ ደህና ዋሉ፤ ደህና እደሩልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 14/04/2024  

#ክስተት #ለዘመን #ለራዕይም። #በተደሞ #ይመርመር። የመዳኛም #የፊደል #ገበታ ሊሆን ይችላል። ሰክኖ መመርመር። ይህ አዲስ ውሃ ያልነካው የተጋድሎ #ካሪክለም ነው። በአደብ ይመርመር።

ምስል
  #ክስተት #ለዘመን #ለራዕይም ። #በተደሞ #ይመርመር ። የመዳኛም #የፊደል #ገበታ ሊሆን ይችላል። ሰክኖ መመርመር። ይህ አዲስ ውሃ ያልነካው የተጋድሎ #ካሪክለም ነው። በአደብ ይመርመር።      "የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።" (ምሳሌ ፳ ቁጥር ፲፭)     ወጣትነቱን፤ መኖሩን፦ ዜግነቱን፦ ርዕሰ መዲናውን፦ ተስፋውን፤ ራዕዩን፤ ሐሴቱን፤ ምኞቱን፤ ትውፊት ትሩፋቱን፤ ወግና ባህሉን በሥርዓት እንዳይፈጽም፤ በባዕቱ በባድማውም መቀመጫ ያጣ ትውልድ እንዲህ ይቆርጣል። በእኔ የወጣትነት ዘመን የት ይደርሳሉ የተባልን ወጣቶች እንዲህና እንዲያ ሆነን ቀረን። ገና በጥዋቱ ነበር ቀዬወን ሰላም እንዳያሳጡ በ100 ቀናት ተግባራቸው ውስጥ ለጠሚር አብይህ አህመድ አሊ የገለጽኩት፤ ሂደት ላይም እያሉ በስፋት ዘርዝሬ ጽፌላቸው ነበር። ተማላ ሳሉ። እሳቸው አምቀው በያዙት የአስምሌሽን፤ የስውር ዲስክርምኔሽን የወረራ እና የመስፋፋት አብዝቶ የመጫን እና አማራነትን የመጠዬፍ ተግባራቸው ተጉ። ጆኖሳይድን አንቅረው በተፋው አገር ራውንዳ ሂዶ ከማስመሰል እሳቸው የጀመሩትን የትውልድ ምንጠራ ማስቆም ቀዳሚው ተግባር ነበር። ግን አልሆነም። የቆረጠ ትውልድ፤ መኖሩን የናቀ ትውልድ እንዲህ ሰማዕትነትን ፈቅዶ በሐሴት ያልፋል። ያውም በመንበረ መንግሥቱ መቀመጫ በአፍሪካ መዲና በአዲስ አበባ። የሚገርም ሰፊ የምርምር ተግባር የሚጠይቅ በጥሞና እና በተደሞ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ ፊደል ያስቆጠረ፤ አናባቢም ተነባቢም ክስተት እንሆ በምድራችን ተፈፀመ። አስፈሪም አጽናኝም፤ ፈታሽም አራሚም፤ ጎባጣ ሃሳብን አቃንቶ በሰከነ፡ በተረጋጋ መንፈስ ምንሽን ነው እማ ብሎ በማስተዋል ሊመረመር የሚገባው ክስተት። ይህ የጀግንነት ተግባር ተብሎ ሊታለፍ አይገባም። ለበቀል ብርንዶነትም