ልጥፎች

ከሜይ 29, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ውቦቼ እንዴት ናችሁ ፈውስ ይህውላችሁ። "በቀላሉ ክብደት መቀነስ! ከሀኪም በላይ ሰውነትን ማድመጥ! ከአለም ሲስተም ማምለጥ || ገነት አህፈሮም | Many..."

ምስል

ኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥም ያስፈልጋታል፨ አጽናኝ ፖለቲካ ትሻለችና፨

ምስል

ውቦች ቅን ቀን ይስጣችሁ። አሜን።

 ውቦች ቅን ቀን ይስጣችሁ። አሜን። ቸር ዋሉ። አሜን ሥርጉትሻ።

#ኦኦ! "እኛ BRICS ነን።" #በለው! #ፌንጣዊ የዴፕሎማሲ አያያዝ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም።

ምስል
  #ኦኦ ! "እኛ BRICS ነን።" #በለው ! #ፌንጣዊ የዴፕሎማሲ አያያዝ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም።   ወዳጅወነት ፓርክ የሠራ" መደመር" መርሄ፤ ርዕዮቴ ብሎ ሠርክ መጽሐፍ ሲያትም ውሎ የሚያድር አገዛዝ ደጋፊ ስሎጋን "እኛ ብሪክስ ነን" አትፎግሩን ዓይነት ጨዋታ አምጥተዋል። ። ግን አብይዝም አንስት ዩቱበር የለውምን??? ለጨዋታ ያህል። #ህም ። ለወዳጅነት ልክ ያስፈልገው ይሆን? ግን የወዳጅነትስ - ከወገብ በላይ እና በታችስ ያሰኜው ይሆን?? ኦ! መዳህኒዓለም አባቴ ደግሞ ልደግመው ነው ለርግማን "መደመር" ልበለው ይሆን? እሱስ ምን እንበለው። ሦስት መጸሐፍ ነው መሰል የታተመው። ዛሬ ዛሬ እንደ "ኢትዮጵያ ሱሴ" #አድራሻ ቢስ ሆኗል። +|ጥሎብህ። የሆነ ሆኖ ኮንፊደንስ ከልክ በላይ ሲሆን #ዕብጠትን ፤ ኮንፊደንስ ከልኩ በታች ሲሆን #መኮስመንን ያመጣል። ኮንፊደንስ ጤናውን የሚያገኜው በልኩ ለልኩ ሲሆን። የተንቧለለም፤ የተጣበቀ ወይንም የተኮረኮደ ወይንም ጥብቆ አያስፈልገም። ለልኩ ልክ። "የዛሬ ዓመት ረጂወቻችንንም በእናመሰግናለን እናስናብታለን። በምግብ እራሳችን እንችላለን" ዓይነትም ጣዕም ያላት የፋንታዚ ወግ ጠሚ አብይ አህመድ ገልጠዋል። እንደ አፈወት ብያለሁ። የሆነ ሆኖ "ብርክሲም" ብትሆኑ ወዳጅነት ከሌላው ጋርም ያስፈልጋል። አላያችሁም የቻይናው መሪ በአገረ አሜሪካ ሲንቦላኩ፤ እዛም እንደተማሩ አዳምጫለሁኝ። የአሜሪካ ወዝም አለባቸው ማለት ነው። ለጠቅላዩም ቤተሰቦቻቸውን አስጠልሎ ነበር የአብርኃሙ ዕልፍኝ አሜሪካ። ብቻ ……… የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ ወዘተ ፖሊሲው አሳቻ የሆነ አገዛዝ መሪውም አሳቻ ናቸው። የልብ አያደርስም። በአባይ ጉዳይ #ተዘ

ትውልድን #ከሞገድ ላይ ካለው ምኞቱ አውርዶ በፋክት፤ በመርህ እንዲሞግት ብቃት ይሰጣል።

 እንዴት አደርን? ጉንፋን እንዴት ይለቅ ይሆን? 365 ቀናት እኔ እና ጉንፋን ጉልቻ ላይ? የሆነ ሆኖ "ዛሬ ዕለቱ" ሰከን ብሏል? ሸጋ ነው። ምን ልላችሁ ነበር? እ። ፕ/ ዶር ተሾመ አበበ በመረጃ የተደገፈ ሙያዊ መግለጫ አንከር ሚዲያ ላይ ሰጥተዋል። ማስታወሻ ተይዞ የሚማሩት ገለጣ ነው። ድክመታችን፤ ፈተናችን እንዲህ ሙያዊ ትንተና ሲያገኝ #ትውልድን #ከሞገድ ላይ ካለው ምኞቱ አውርዶ በፋክት፤ በመርህ እንዲሞግት ብቃት ይሰጣል። የሚደንቅ ነው ትጥቅ አስፈች ዕይታወችን ሁሉ በረጋ አቀራረብ ሞግተዋል። "በኢኮኖሚ ውድቀት ሥርዓት ይፈርሳል" የሚለውን ዕድምታ "ትጥቅ አስፈች" ብለውታል። ግን በከረረ አገላለጥ አይደለም። በእናታዊ አገላለጥ። በጣም ጠቃሚ መምህር የሆነ ገለጣ ነው። ከዚህ ቀደምም የሰጡት ሁሉ ሰኃ የማይወጣለት ነው። የልጅ መሳይ ብርቱ አቅሙ እሱ ልተንትነው፤ ልበትነው አይልም #አብዛኛውን #ጉዳይ ከባለሙያ ጋር ይወያያል። ይህቺን ሲያደርግ አያመልጠኝም አዳምጠዋለሁ። የቤተ እግዚአብሄር ከሆነም ለተሰጣቸው ዕድሉን ሰጥቶ ያወያያል። ማለፊያ ነው። ይፈቀድልኝ አይፈቀድልኝ ስለማላውቅ ሼር አላደረኩትም። ሄዳችሁ ግን እንድታዳምጡት በትሁት ብዕሬ አሳስባለሁ። ሥርጉትሻ2024/05/29