ልጥፎች

ከጁላይ 31, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጨረቃ ክንፍ አውጥታ ሰማይ ላይ ብትበር፤ ጸሐይ በሠረገላ ወደ ምድር በሚያስፈራ ግርማ ብትመጣ፤ የሰማይ ታምራት እና ገድላት በምድራችን ላይ ቢገለጥ፤ ህወኃት ኢትዮጵያን የመምራት #ዕድል ፈጽሞ አይኖረውም።

  ጨረቃ ክንፍ አውጥታ ሰማይ ላይ ብትበር፤ ጸሐይ በሠረገላ ወደ ምድር በሚያስፈራ ግርማ ብትመጣ፤ የሰማይ ታምራት እና ገድላት በምድራችን ላይ ቢገለጥ፤ ህወኃት ኢትዮጵያን የመምራት #ዕድል ፈጽሞ አይኖረውም።    "እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች፤ ዓይን እያላችሁ የማታዩ፤ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ፤ ህዝብ ሆይ! ይህን ስሙ። በዕውን እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን?" (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፳፩ - ፳፪)   #ምዕራፍ ፲፱።   #ጠብታ ።   ተዘርዝረው የማያልቁ የሰው ልጅ የጭካኔ ዓይነትን ተቀብሏል ህዝብ በህወሃት። ያ የግፍ፤ ያ የስቃይ፤ ያ መተንፈሻ ያልነበረበትን የጭካኔ ዘመን መላ የኢትዮጵያ ህዝብ በወረፋ ቢደርሰውም በስሜን ጎንደር የደረሰው፤ በአዛውንት #ተጋሩ ዕውነት መስካሪነት የተፈጸመው አሰቃቂ ሰቆቃ ዕንባን ሰማይ አዳመጠ። መለሰም።    ህወሃት ፈቅዶ እራሱም ድምጽ ሰጥቶ ሁለት ድምጽ ብቻ አግኝቶ ሥልጣነ - መንበሩን ሲለቅ፤ ከዚህ በላይ ዲስፕሊን የለም በማለት ውሃ በቀጠነ ህወሃትን አጀንዳ ያደረጉ ሚዲያወች ይሁን ግለሰቦች ሲሞግቱት እኔ እንደ ቋሚ ሞጋችነቴ ጸጥ ብዬ ነበር እምመለከተው።   የህወሃት እና የብልፄ ጦርነት ዱብ - ዱብ ሲልም፤ #ተው ከማለት ውጪ አንዳችም ቃል ብዕሬ አውጥታ እንድትናገር አልፈቀድኩም። እንዲያውም "መጤ፤ ጸጉረ ልውጥ" በሚሉ አገላለፆች ቅሬታዬን ጽፌያለሁኝ። የተገባ አልነበረም። ይቅርታም በይፋ ሊጠየቅበትም ይገባል። ለይቅርታ ቅድመ ሁኔታም ቀጠሮም ስለማያስፈልገው። ሰው በአገሩ፤ በባዕቱ - "መጤ፤ ጸጉረ ልውጥ" ፈጽሞ ሊባል አይገባምና።   በጦርነቱም ወቅት ጉዳቱን ከዓለም ዓቀፍ ሚዲያወች ብቻ የማገኜውን የግራ ቀኙን ሰብአዊነት...

#በደል #ይረሳል ወይንስ #ይለመዳል?

  #በደል #ይረሳል ወይንስ #ይለመዳል ?   "እንሆ በማትረቡበት በሃሰት ቃል ታምናላችሁ።" (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፰።)   #ምዕራፍ ፲፱።   ይህን እርስ #በደል ይረሳል ወይንስ ይለመዳልን። በዘሃበሻ እና በሳተናው ድህረ ገጽ ላይ በዘመነ ህውሃት ጽፌበት ነበር።   አሁን ደግሞ #ድገሙኝ // ሰልሱኝ የሚል የዘመነ ህውሃት ናፍቆተኝነት ዲል ብሎ ስለመጣ፤ ሥልጣን ላይ እያለ የነበረውን የጭካኔ ሁነቱን ትቼ፤ በብልፄው እና በህወሃት መካከል ልምራህ፤ አልመራም ፍጥጫ በተከፈተው ጦርነት ትግራይም፤ የአማራ ክልልም፤ የአፋር ክልልም አሳራቸውን አይተዋል።    ጉዳቱ የገዘፈ ቢሆንም ትግራይ ላይ ጦርነቱ ለአጭር ጊዜ ነበር ቆይታው። አማራ ላይ ግን አሁንም አልቆመም። ስንት ዓመት #በጦርነት ? አንድም ሰዓት ይሁን አንድም ቀን ከባድ ነው አይደለም ለዓመታት።    የሆነ ሆኖ #ሰቆቃው ማይካድራ /// የሬቻ ጭፍጨፋ ዕጣ ፈንታ ነው የደረሰው። #አፋርም አልቀረለትም #ጭና መቃብሩ ቤት ውስጥም እንደ ነበረ የወቅቱ ዘገባ ያመለክት ነበር።   በጭና የሰው ልጅ ህልፈት፤ ሰማዕትነት ነዋሪው ተመልሶ ወደ ቀዩ ለመኖር የነበረው ፈተና ከባድ እንደ ነበር በወቅቱ ከቦታው ድረስ ሄደው የዘገቡ ጋዜጠኞች መስክረዋል።   እኛ ሥጋ ለባሾች ከእልፈታችን በኋላ በተገቢው ጊዜ፤ የተገባው ነገር ካልተከወነ መከራው #ዝልቅ ነው። ጭና የገጠመው ይህ ነበር። ፍርስርስ እኮ ነው የእኛ ነገር።    ወሎ የተረፈው ነገር አልነበረም። 20 የመርሳ ወጣቶች #የመዳህኒት መፈተኛወች እንደሆኑ ሁሉ ሰፊ ዘገባ ነበር።    የእናቶች፤ የእህቶች አስገድዶ የመድፈር ሂደት እጅግ ...

«ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ « እርዕሱ የፋና ነው።

  «ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ « እርዕሱ የፋና ነው። "መግለጫ" እንደምን እንዳሉት አላውቅም።   «ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ «    https://www.youtube.com/watch?v=PMCa8vhxxdU https://www.youtube.com/watch?v=MmXBskHA3aM https://www.youtube.com/watch?v=WTWVJ-NtdLs   #ማብራሪያ ፤ #ወቅታዊ መረጃ ቢባል የተሻለ ይመስለኛል። መግለጫ የውሳኔ ሃሳብን የሚይዝ ነው። ይህ ግን የሚዲያ ማብራሪያ ነው። ኮሚሽኑ ምን ላይ እንዳለ፤ ቀጣይ አቅጣጫው ምን ሊመስል እንደሚችል የሚብራራበት ነው።   የሆነ ሆኖ ተያያዥነት እንዲኖረውም ከሶስት ቀን በፊት፤ እንዲሁም ከስድስት ቀን በፊት የነበረውንም ሊንክ አክላለሁኝ።   #ገርሞኛል ።   የገረመኝ ግን የተወሰነ አትኩሮቱ አቅጣጫው በምክክር ኮሚሽኑ ላይ መሆኑ፤ ጠቅላይ ሚር አብይ ደግሞ በመሃል በቃለ ምልልስ ብቅ ብለዋል። ለአንድ ወር #መጠሞን ፤ #መጨመት እንደምን ፈቃድ ለአጤ #አትኩሮት ሊሰጥ አልቻለም።   ያው እንደ ተለመደው አንዱ አመክንዮ ሳይቋጭ ደግሞ ወደ ሌላው የመንፈስ #ብክነት …… በዚህ መሃል ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ብቅ ብሎ እንዲህም እንዲያም ያው ያስኮናል።   #የተሰባሰበ ፤ #የተማከለ የመንፈስ አቅም፤ የአትኩሮት አቅም በራሱ የውስጥ #ሰላም ይሻል። ግን ………?   #ክወና ።   የሆነ ሆኖ የአገር ጉዳይ #የትንፋሽ ነውና ማን ይከውነው ማን፤ ይህን መሰል ግዙፍ አገራዊ ጉባኤ በአትኩሮት መከታተል የተገባ ይመስለኛል። አገሬን ያለ፤ በዕቴን ያለ፤ መከፋቷን ውስጡ ያደረገ፤ በተለይ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ...

#መድህን።

ምስል
  #መድህን ።   "ከመምህራን ዘንድ ምክርን ፈልግ፤ #የምትረባህንም ምክር #አታቃልል ።"         #ምዕራፍ ፲፱።   መድህን #መዳኛ ፤ #መፈወሻ ማለት ነው። ቃለ ወንጌልም ነው። ህመማችን ዝልቅ መፍትሄችን ሩቅ ሆኖ ትውልድ ሲገበርበት ኖረ። ዘመን #ይፍታህ ለማለት ፍቱን መዳህኒቱ ለእኔ ይህ የቀደመው፤ የኢትዮጵያ ካርታ ብቻ ይመስለኛል።    #ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ወንዞችን፤ ተራሮችን መለያ፤ መወሰኛ አድርገው አቨው እና እመው ወደ ሠሩልን አቅጣጫ ብንመለስ ዛሬ እንዲህ ህሊናችን እምስምስ ከሚልበት ትርምስ ወጥቶ ዘመን ሰጥ ሥልጣኔወች ጋር ማተኮር በተቻለ።   በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ የምክክር የጉባኤ አባላት ከሚወያዩበት በህረ ጉዳይ ይህ ነውና መድከም ካልቀረ #የሰመረ ጣፋጭ ውሳኔ ላይ ቢደረስ መልካም ይሆናል።    " #የድሮ ናፋቂ " ይባላል ሰላምን መኖርን የሚለግሥ ከሆነ ስለምን አይናፈቅም።   #አንድ ዶላር እና አንድ የኢትዮጵያ ብር እኩል የሆነበት ዘመን፤ በግ ተገዝቶ ቆዳው ተሽጦ ሥጋው ነፃ የሆነበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም? #ለትምህርት ወደ ውጪ የተላከው ሁሉ ስደትን አሻም ብሎ ወደ አገሩ የሚመለስበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም? #አንድ ኩንታል ጤፍ በጥቂት የብር ኖቶች ይገዛ የነበረበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም? #ሰው መሆን ብቻ ቁምነገር የሆነበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም? #የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከክብሩ ወርዶ የማይነድበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም? #ዜጋ በባዕቱ የማይሳደድበት፤ ሥልጣኔው የማይነቀፍበት ወይንም የማይነቀልበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም? ወዘተ ……… ወዘተ ……… ………ወዘተ ………   ቸር አስበ...

#ለምህረት ይሁን #ለይቅርታ #ቅድመ ሁኔታም ይሁን #ቀጠሮ አያስፈልገውም።

ምስል
  #ለምህረት ይሁን #ለይቅርታ #ቅድመ ሁኔታም ይሁን #ቀጠሮ አያስፈልገውም።   "እግዚአብሄርም እንዲህ ይላል፦ ----- በመንገድ ላይ ቁሙ፤ ተመልከቱም ፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ፥ በእርሷም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ - አንሄድባትም አሉ።" (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፲፮።)       #ምዕራፍ ፲፱።   የሰው ልጅ ፍጥረተ - ነገሩ ከታወቀው ከሥጋ፤ ከአጥንት፤ ከመንፈስ፤ በሃይማኖት እራሱን የቻለ የአፈጣጠር ሚስጢራት አሉ። አቨው ይሂዱበት፤ እኔ በገሃዳዊው ዓለም መኖርን በማኖር ሂደት ያሉ ቅይጥ ሁነቶች ላይ ብቻ ነው አትኩሮቴ።   ብቻ የሰው ልጅ ከተፈጠረባት #ትንፋሽ ባላነሰ ይቅርታም፤ ምህረትም፤ እርቅም፤ ትህትናም፤ አድማጭነትም፤ መታመንም፤ መሰጠትም፤ አክብሮት፤ መቀበልም፤ ቅንነትም፤ ትህትናም፤ ደግነትም፤ ሐሤትም፤ አብሮነትም፤ ትዕግስትም፤ ማፍቀርም፤ መፈቀርም፤ መውደድም፤ መቻቻልም፤ መወደድም፤ እሽታም፤ ምርቃትም፤ ሃቅ፤ ምስጋናም፤ ስጦታም፤ ዕውቀትም፤ መክሊትም፤ ጥሪም ወዘተ ከተፈጠረበት ቅብዓ ንጥረ ነገሮች ጋር ተነጣጥለው ሳይሆን እሱነቱ ከተዋቀረበት አካላቱ፤ ሚስጢራቱ ጋር #ተዋህደው ተፈጥረውለታል።   የሰው ልጅ - ከወደደ፤ የሰው ልጅ - ከፈቀደ፤ የሰው ልጅ መቻሉን ካስቻለ #ተመርቆ በተፈጠረበት ልክ መሆን ይችላል። #ከልካይ የለበትም። እንደ እኔ ፅኑ እምነት የሰውልጅ ተባርኮ፤ ጸድቆ፤ ጹሞ ነው የተፈጠር ብዬ አምናለሁኝ።   ውዷ ዓለማችን ግን የተፈጠርንበትን የምርቃት ንጥረ ነገር የምታስቀጥልበት #ቋሚ ተቋም የላትም። ስለሆነም የሰው ልጅ #መሰጠት #ብክነት ገጠመው ብዬ አስባለሁኝ።...