#በደል #ይረሳል ወይንስ #ይለመዳል?
"እንሆ በማትረቡበት በሃሰት ቃል ታምናላችሁ።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፰።)
#ምዕራፍ ፲፱።
አሁን ደግሞ #ድገሙኝ // ሰልሱኝ የሚል የዘመነ ህውሃት ናፍቆተኝነት ዲል ብሎ
ስለመጣ፤ ሥልጣን ላይ እያለ የነበረውን የጭካኔ ሁነቱን ትቼ፤ በብልፄው እና በህወሃት
መካከል ልምራህ፤ አልመራም ፍጥጫ በተከፈተው ጦርነት ትግራይም፤ የአማራ
ክልልም፤ የአፋር ክልልም አሳራቸውን አይተዋል።
ጉዳቱ የገዘፈ ቢሆንም ትግራይ ላይ ጦርነቱ ለአጭር ጊዜ ነበር ቆይታው። አማራ ላይ ግን
አሁንም አልቆመም። ስንት ዓመት #በጦርነት? አንድም ሰዓት ይሁን አንድም ቀን ከባድ ነው
አይደለም ለዓመታት።
#ጭና መቃብሩ ቤት ውስጥም እንደ ነበረ የወቅቱ ዘገባ ያመለክት ነበር።
በጭና የሰው ልጅ ህልፈት፤ ሰማዕትነት ነዋሪው ተመልሶ ወደ ቀዩ ለመኖር የነበረው ፈተና ከባድ
እንደ ነበር በወቅቱ ከቦታው ድረስ ሄደው የዘገቡ ጋዜጠኞች መስክረዋል።
እኛ ሥጋ ለባሾች ከእልፈታችን በኋላ በተገቢው ጊዜ፤ የተገባው ነገር ካልተከወነ መከራው #ዝልቅ
ነው። ጭና የገጠመው ይህ ነበር። ፍርስርስ እኮ ነው የእኛ ነገር።
በየለቱ የምንሰማቸው ስቃዮች ምንጫቸው ከጭካኔ ሃሳብ ቤተኛው #ከህወሃት የጭካኔ ገበታ የተቀዱ ናቸው።
እሱ በአምሳያው ከቀረፃቸው አካሎች የሚቀዳው ያው ጭካኔ እና አረመኔነት ነው።
#የሆነ ሆኖ።
"በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት" ሆኖ ያ የህወሃት ግራጫማ ዘመን የሚናፍቃቸው ሰብዕናወች መኖራቸው
ብዙም አይደንቅም። ትውልዱ የዘመነ ህውሃት ነውና። መብትም ነው "ጭካኔን ማበረታታት፤ ይሁን ጭካኔ
አክብሮ መነሳት እንዲሁም ሌላ የጭካኔ መከራን መናፈቅ።" ብቻ ለእኔ ግን #ሰቅጣጭ ጉዳይ ነው።
ህወሃት ከተፈጠረበት ቀን አንድ ጀምሮ የፈጸመው ኢ - ሰብአዊ፤ ኢ - ተፈጥሯዊ ድርጊት ሁሉ ካለይቅርታ፤
ካለ ካሳ ይለፍ ተቆላምጦ እንዲህ ማግኜቱን እያዳመጥኩኝ ነው። #መሃከነ።
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች በደል ይረሳል ወይንስ ይለመዳል ያልኩትም ለዚህ ነው። ጎንደሮች
ባለ ቅኔ ናቸው። "ያልተነካ ግልግል ያውቃል ይላሉ።"
ሁሉ ጸጥ ብሎ ይማር፤ ይዳር፤ ይኳል በነበረበት ጊዜ ሁሉ ብዙ መከራ በህወሃት ምክንያት ያዬ ትውልድ
የትኛውንም #የአፍቅሮተ ህወሃት ናፍቆት ማስጠጋት አይቻልም። በፍጹም።
በደልን የሚያውቀው የተበደለው ነው። አሁን አሁን ሳስበው የአንድ በዕት ህዝብ በዚህን ያህል ጥልቀት
መገለሉ፤ ላሳለፈው የስቃይ ዘመን ሁሉ ተደሳቾች እንዳሉ እያስተዋልኩ ነው።
በማስተዋሌ ውስጥ ክፋ ሃሳብ በምን ያህል ጥልቀት እና ስፋት የሰውን ልጅ መቆጣጠር እንደቻለም
ተገንዝቤያለሁኝ። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
31/07/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ለዕውነት ወጌሻ ወይንም ጋራጅ አያስፈልገውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ