BBC "የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ይዘት “አሳሳቢ” መሆኑን 14 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስታወቁ"
https://www.bbc.com/amharic/articles/cly04m7gezvo የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ይዘት “አሳሳቢ” መሆኑን 14 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስታወቁ "አስራ አራት የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት እና የሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ማሻሻያ “አካሄድ እና የይዘት ግድፈቶች” እንደሚስተዋሉበት ገለጹ። ድርጅቶቹ ይህን የገለጹት የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅን በተመለከተ በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው። “በአዋጁ ከለላ ተሰጥቷቸው የነበሩ የቁጥጥር እና ሚዛን መጠበቂያዎች በረቂቅ አዋጁ ሊሻሩ የሚችሉ መሆናቸው በእጅጉ ስላሳሰበን ይህንን የአቋም መግለጫ አዘጋጅተናል” ሲሉ መግለጫ ያወጡበትን ምክንያት ጠቅሰዋል። ድርጅቶቹ አክለውም “የአዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይትም ባልተካሔደበት ሁኔታ” ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ማሻሻያ ከተደርገባቸው ሕጎች እና አዋጆች መካከል የመገናኛ ብዙሃን አዋጁ አንዱ ነበር። የአዋጁን መጽደቅ ተከትሎ “ነጻና ገለልተኛ የሚዲያ ምኅዳር ለመገንባት ከፍተኛ ተስፋ” እንደ ነበር ያስታወሱት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ፤ “ለፕሬስ ነጻነትና የተሻለ የሚዲያ ሥራ መሠረት በመሆኑ አዋጁ በስፋት ተቀባይነትን አግኝቶ ቆይቷል” ብለዋል። ተቀባይነት አግኝቶ የቆየው ይህ አዋጅ “ተለዋዋጭ በሆነው የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ” ሳቢያ፤ “የሚዲያ ነፃነትን ከማረጋገጥ አንጻር የሕጉ ተፈጻሚነት በተግባር ችግሮች” እንደገጠሙት ድርጅቶቹ አውስተዋል። በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ፤ “የገለ...