ልጥፎች

ከጁላይ 8, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

«አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ማን ናቸው?»

ምስል
  «አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ማን ናቸው ?»   6 ሀምሌ 2024 «ሰር ኪር ስታርመር የሌበር ፓርቲን በመምራት በምርጫ አሸናፊ ሆነው የዩናይትድ ኪንግደም ( ዩኬ ) አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። ሰር ኪር የጠንካራ ግራ ዘመም ፖለቲከኛው ጄሬሚ ኮርቢንን ከአራት ዓመት በፊት በመተካት የሌበር መሪ ሆኑ። ፓርቲውንም ከግራ ዘመም ወደ መሃል ሜዳ በመመለስ ተመራጭ ለማድረግ ሠርተዋል። የሌበር ፓርቲ ለ 14 ዓመታት ከሥልጣን ርቆ ነበር። ሰር ኪር ጥሩ ስም ከገነበቡት የጠበቃነት ሥራቸው በኋላ ዕድሜያቸው በ 50 ዎቹ ውስጥ በነበረበት ወቅት ነበር የፓርላማ አባል የሆኑት። በፊትም ቢሆን ግን ለፖለቲካ ፍላጎት ነበራቸው። ወጣት እያሉ አክራሪ ግራ ዘመም ነበሩ። ሕይወት ከፖለቲካ በፊት እአአ በ 1962 በለንደን ተወለዱ። ወላጆቻቸው አራት ልጆች ነበሯቸው። ያደጉት ደግሞ ደቡብ ምሥራቅ እንግሊዝ ውስጥ በመትገኘው ሰሪ ነው። ብዙውን ጊዜ ከሠራተኛ መደብ ከሆነ ቤተሰብ እንደተገኙ ይጠቅሳሉ። አባታቸው ፋብሪካ ውስጥ ይሠሩ ነበር። እናታቸው ደግሞ ነርስ ነበሩ። ቤተሰባቸው ጠንካራ የሌበር ፓርቲ ደጋፊዎች ነበሩ። ሰር ኪር ስማቸውን ያገኙት የፓርቲው የመጀመሪያ መሪ ከነበሩት ስኮትላንዳዊው ኪር ሃርዲ ነው። የቤተሰብ ሕይወታቸው በብዙ ፈተና የተሞላ ነበር። “ ቀዝቃዛ እና ከሰው የማይቀላቀል ዓይነት ሰው ነበር ” ይላሉ ሰር ኪር ስለአባታቸው ሲናገሩ። እናታቸው ...