ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ እገታዎች እንዲቆሙ የአሜሪካው አምባሳደር ጥሪ አቀረቡ BBC

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cqe671150d2o

 

"በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ እገታዎች እንዲቆሙ የአሜሪካው አምባሳደር ጥሪ አቀረቡ"

አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ

"የፎቶው ባለመብት, @USEmbassyAddisየምስሉ መግለጫ, አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ ለማግኘት እየተፈጸሙ ያሉ የሰላማዊ ሰዎች እና የተማሪዎች እገታዎች መቆም አለባቸው ሲሉ የአሜሪካው አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጥሪ አቀረቡ።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚፈጸሙ እገታዎች ሰበብ ስጋት እንደተፈጠረ በተደጋጋሚ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወቃል።በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ኧርቪን ማሲንጋ በኤምባሲያቸው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ እንዳሰፈሩት ባለፈው ሳምንት ከ100 በላይ ተማሪዎች እና መንገደኞች ገንዘብ ለማግኘት ሲባል መታገታቸውን ገልጸዋል።ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እና ከባሕር ዳር ተነስተው በሦስት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎች እና መንገደኞች ባለፈው ረቡዕ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም. በታጣቂዎች መታገታቸውን ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።እገታው የተፈጸመው ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 155 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ መሆኑን የዐይን እማኞች እና የታጋች ቤተአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋየፎቶው ባለመብት, ሰቦች ለቢቢሲ ገልጸው ነበር።

ገርበ ጉራቻ አካባቢ 100 የሚጠጉ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታገቱ

በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች አሳሳቢ ሆነው ቀጥለዋል፡ ኢሰመኮ

ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች በዱባይ ቤት መግዛትን እየመረጡ ያሉት ለምንድን ነው?

አምባሳደር ማሲንጋ እንዳሉት “በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በቅርቡ እና በተደጋጋሚ የሚፈጸሙት እገታዎች እየተካሄዱ ያሉት ግጭቶች ምን ያህል ወንጀለኞችን እንዳደፋፈሩ እና የሕግ የበላይነትን እንዳዳከሙ ያሳያሉ” ብለዋል። ስለዚህም የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት እየተፈጸሙ ያሉት የሰላማዊ ሰዎች እና የተማሪዎች እገታዎች ሊቆሙ ይገባል በማለት አሳስበዋል።

 በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እያጋጠሙ ባሉት እገታዎች ሰበብ የታጋች ቤተሰቦች የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠየቃሉ። 

ቤተሰቦች ገንዘብ ለማሰባሰብ ለልመና አደባባይ እስከ መውጣት መድረሳቸው በተደጋጋሚ ታይቷል። በእነዚህ እገታዎች ገንዘብ የከፈሉ እንዲሁም መክፈል ካልቻሉ ሰዎች መካከል ደግሞ የተወሰኑት የተለቀቁ ቢሆንም በርካቶች ደብዛቸው መጥፋቱን ቤተሰቦች ይናገራሉ። 

በአጋቾች የተገደሉ በርካታ ሰዎች ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ዕጣ ፈንታቸው አልታወቀም። ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን እገታ በተመለከተ ከኦሮሚያ ክልልም ሆነ ከፌደራል መንግሥቱ የተባለ ነገር የለም። የመንግሥት ኃይሎች ከታጣቂዎች ጋር ግጭት ውስጥ በሚገኙባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ዕገታዎችን የሚፈጽሙት ታጣቂዎች መሆናቸው በስፋት ይነገራል።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።