ልጥፎች

ከዲሴምበር 13, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እራሱ „ተጋድሎ“ ዬሚለው ሥያሜ ቃለ ወንጌል ነው። ዛሬን የሰጠን ትናንት ነው።

ምስል
ዬስጋት ቋት - ጦሮ!   „አቤቱ፦ ምህረትም የአንተ ነው፤ አንተ እንደ ሥራው ለእያንዳዱ ፍዳውን ትሰጣለህ።“ ( መዝ. ምዕራፍ ፷፩ ቁጥር ፩፫) ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 04.12.2016 ( ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ።) v ጠ ብታ። ውዶቼ ይህም የአማራ የህልውና የመንነት ተጋድሎ ወጀብ በበዛበት ወቅት የጻፍኩት ነው። ሳተናው/ ኢትዮ ሪጅስተር አትሞልኝ ነበር። መርቁት። ጀግና እሱ እንጂ ሌላ አልነበረም። ጀግንነት በገንዘብ ሳይሆን በድርጊት ነው የሚቀልመው። የቃላት ግድፈትን ብቻ ነው እማርመው እና የሚገርሙኝ አገላለፆችን አቀልማቸዋለሁኝ። የእኔ የእኔ የማይመስሉኝ ግን የቀደሙ አገላለፆች አሉበት። እኔን እራሴ እዬገረመኝ ነው ሳነበው … ጹሑፉ በዛን ዘመን መንፈስ እና በተነሳሁበት የአማራነት ማንነት ቃለ ምልልስ ውስጥ ነው መታዬት የሚገባው እሺ ውዶቼ። ግን ታሪክም ስለሆነ ቀንበጥሻ  አርኬቧ ላይ ልታስቀምጠው ወዳለች። እንዲህ ነበር የተጀመረው … v እ ንዲህ … ዓለም እራሷን ፈጣሪ አደራጅቶ ነው ዬፈጠራት። በአህጉር - በአገር - በዬብስ፤ በውቅያኖስ፤ በሰማይ አሳምሮ ነው ዬሠራት። ዬሰው ልጅ ደግሞ ሥጦታውን፤ ዘመኑ በፈቀደለት እውነት፤ ለእሱ በሚያመች መልኩ ስልት ቀይሶ፤ ህግ ሰርቶ፤ ዬአፈጻጸም መመሪያ አሰናድቶ ተጠቃሚ ሲሆን ቆይቷል። በዓለም ከድርጅት ውጪ ዬሆነ ነገር ዬለም። ስለሆነም ዓላማና ግብ ያለው ዬሰው ልጅ ዬኑሮው ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ድርጅት ነው ማለት ያስችላል። v መደራጀት ማለት ምን ማለት ነው? ግባእቱስ? በቀላል አገላለጽ ብቻ ነው ዛሬ እምገልጸው። ምክንያቱም ዬተነሳሁበትን አጀንዳ  እንዳይጫንብኝ ስለምሻ። መደራጀት ማለ