ኢትዮጵያዊነት አያረጅም! ስለዚህም እድሳት አያስፈልገውም።
እንኳን ደህና መጡልኝ። „ዕውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወይስ ጡት ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ ሥርዓት በሥርዓት ሥርዓት በሥርዓት፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፱ -፲ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእማ - ሲዊዘርላንድ 11.01.2019 "ኢትዮጵያዊነት መታደስ አለበት ኢትዮጵያዊነት እንደገና መሠራት አለበት አዲሲቷ ኢትዮጵያን እንግነባ" የሚሉ ድምጽች ይሰማሉ። መልካም ነው። ከሆነ። ይህ ማለት ኢትዮጵያዊነትን መጠገን በሚለው በአዎንታዊነት የሚታይ ሲሆን በሌላው ዕድምታ ግን አሉታዊ ነው። መታደስ፤ በአውነታዊነት መገንባት ያለበት የእኛው አንጎል ነው። አሉታዊነቱን እንዲህ ልግለጠው … ኢትዮጵያዊነት በእኔ ውስጥ ያለው አርጅቶ አያውቅምና። መወደሱም ራሱ ውስጤም ኑሮዬም ይገልጠዋል። ምን አልባት ኢትዮጵያዊነትን እንደ አንጡራ ጠላት ለሚዩት ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ራሳቸው መታደስ ይኖርባቸዋል። ከማዕቀፉ በወጡ ቁጥር እዬሾለኩ ስለሚቀሩ። ኢትዮጵያዊነት የሚያረጀው አስረጅተውት የኖሩት የብልጠት ፖለቲካ ፍልስፍናቸው ያደረጉ የንፋስ ተጠዋሪ ፖለቲከኞች ናቸው። ወጀቡ በለጋው ቁጥር ኤን ላለማስከፋት ኢትዮጵያዊነት በስርዙ መደራደሪያ አድርጎ በማቅረብ፤ ቢን ለማፍነሽነሽ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ በዚህ እንዲያ በዚያ በማለት አደናግሬን በመከተል። ኢትዮጵያዊነት አያረጅም፤ አይሞትም፤ አይሰበረም፤ አይቀበረም። ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ቀደም እንደምለው እሸት ነው። እያሸ ተ እያፈራ እዬሰበለ የሚሄድ የገነት ፍሬ ነው። ስለሆነም እንደ አሮጌ ቤት ወይንም ህንፃ እድሳት...