Ahadu TV :የድርድሩ ሂደት እና ቀጣይ ጉዳዮች | አሐዱ መድረክ - ክፍል 1 -3
በተደሞ ይደመጥ የፖለቲከኞች ሙግት ነው። #እኔም አቶ ሙሉብርኃን ኃይሌን አመሰግናለሁኝ። ዕውነትን መያዝ የሁሉም መሠረት ነው። (የትግራይ ዴሞክራሲዬ ፓርቲ።) አቶ አብርኃም ደስታ የፈጠረች ባዕት እናንተን ደግሞ ሰጥታናለች። ይጨርስላችሁ ከዕውነት ጋር ለመዝለቅ። አቶ ሙሉብርኃን ኃይሌ የታሪክ፣ የዕውነት ምስክርነት ሰጥተዋል። ዶር ደሳለኝ ጫኔም ምስጋና አቅርቧል። እኔም ያልኩት። ወልቃይት እና ራያን ብቻ ሳይሆን በጉልበት ህወኃት የወሰደው አገርንም፣ ኢትዮጵያንም በጉልበት ወስዷል የሚል ዕድምታ አቅርበዋል። ይህ ነው የሃቅ ድልድይ የቅርታ መሠረት፣ የማግሥት ሃብል፣ የትውልድ አብሮነት ተክሊል ሊሆን የሚችል። ሰው፣ መንግሥታት፣ ተቋማት አይደሉም እርቅም ምህረትም። ዕርቅም የዕውነት ነው። የዕውነት ፈጣሪው ደግሞ እግዚአብሔር አላህ ነው። እኔ በስምምነቱ ዙሪያ ድንጋጌ ስላለው የህግ ባለሙያወችን ይጠይቃል። እንግሊዘኛ ዬሚያው ይተረጉመዋል። ትርጉም ግን ባለሙያ አለው። ህግጋትም ባለሙያ አላቸው። አማርኛ ቋንቋን አዘመኝ፣ አሰልጥኜ መናገርም እችላለሁ። ይህ ማለት ግን በአማርኛ ቋንቋ ዬሚፃፋ ህግጋትን እተረጉማለሁ ማለት አይደለም። ስለሆነም በጅምሩም፣ በፍፃሜውም በተደሞ ዬባለሙያወችን ወገናዊ ትንተና አዳምጣለሁኝ። በተለይ ዬቅኖችን። ሙግት ሲሆንም እንዲህ አዳምጣለሁኝ። አስተያዬት አልሰጥም። አልጽፍበትም። ማድመጥ ብቻ። ይህን ውይይት ከቻላችሁ አዳምጡት። ሁልጊዜ እንደምለው ዜሮ ላይ ሆናችሁ። ቅጥንብሩ በጠፋው የኃል አሰላለፍ አቅም አታባክኖ። ዛሬ ሰብሰብ ብሎ አንድ ጎራ መስሎ የምታዩት ነገ ይበተናል። ዬአሁኑማ የጉድ ነው። ቅጥ አንባሩ ጠፍቶታል። ፆታ የለሽ፣ ቀለም ዬለሽ ሆኗል። ግን ዕውነት፣ መርህ፣ ፋክት እነሱን ተዛመዱ። ተኩስ በአስቸኳይ ይቁም ሲሉ ዬነበሩት ሌላ ...