ከግራጫማ ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው።
ከግራጫማ ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው። „የሽንገላ ከንፈሮችን ሁሉ እግዚአብሄር ያጠፋቸዋል“ መዝሙር ፲፩ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 11.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መ ቅድመ ዕለት። የአብይ አቅም፤ ክህሎት፤ መክሊት፤ ሰብዕና ስኬታማ ትልም፤ ነጋዊነት፤ አዲስአዊነት፤ እኛዊነት፤ አቃፊነት፤ ሰብዕዊነት፤ ክህሎታዊነት፤ ሰብሳቢነት፤ አቅራቢነት፤ አደራጅነት፤ ታጋሽነት፤ አያያዥነት፤ ቅኔነት፤ አድማጭነት ከሳበረገጋቸው ሰዎች አንዱ አቶ ጃዋር መሃመድ ነው። ትናንትም ዛሬም የሚያብንነው ይኸው ነው። ይህ ባላስበነው ወቅት እና ሁኔታ ከች ያለው ብልህነት የእሱን ደረጃ ቁልቁል ያስገባም ነው። የአሱን ተደማጭነት ወደ አልነበረ ያሸጋገረም ነው። የጠ/ሚር አብይ አቅም ልክ እንደ ፏፏቴ ነው። ሲሰጥ አይነግር የሚባል መክሊት ነው ያላቸው። ይህን ደፍሬ እምናገረው እኔ ከ2016 ጀምሮ ስላጠናኋዋቸው ነው። የግራ ሴራ ፖለቲካ ነው ለማደናቀፍ እዬተፈታተናቸው ያለው እንጂ ሰላም ቢሆን ስንት ታምር ባዬን ነበር ከዚህም በላይ። ግን እንቅፋቱ በዛ። በተጨማሪም በሁለቱ ሊሂቃን ማህከል በዶር ለማ መገርሳ እና በዶር አብይ አህመድ ያለው የተከደነ የክህሎት ሲሳይ ጃዋርውያን እና መሰሎቻቸውን ቢያሰበረግጋቸው ይገባል። ማወዳደር የሚቻለው ተቀራራቢ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ማነጻጸርም የማይደፈር ነውና።ለዛውም ከእኛ ተፈጥረው እንጂ ስካንዳንቢያ አገሮች ቢፈጠሩ ኖሮ ስንት መጸሐፍ በታተመላቸው ነበር። አብዝቼ ለሁለቱ እምጸልዬው ንፋስ እንዳያስገቡ እንዲህ በቅናዊ አሃታዊነታቸው እንዲቀጥሉ ነው። ...