ልጥፎች

ከሜይ, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የአገር መሪን የሥልጣን ጊዜ ስለመገደብ የእኔ ዕይታ። "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ።"

  #የአገር መሪን የሥልጣን ጊዜ ስለመገደብ የእኔ ዕይታ።    "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ።"   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   ብዙ ተቃዋሚወች ይሁኑ ተፎካካሪወች ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን አቅልሎ የማዬት የወል ባህሪ አይባቸዋለሁ። ልምድ እንደሌላቸውም ሲናገሩ አድምጫለሁኝ።    በቂ ልምድ አላቸው። ሚሊተሪ ላይ ሠርተዋል፤ በተመድ ፕሮጀክት ተሳትፈዋል፤ ከኢንሳ መስራችነትም አሉበት በዛው ተቋም መሪነቱም ታክሎ ልምድ ይገበይበታል፤ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በሚር ደረጃ መርተዋል፤ የኢህአዴግ የፓርላማ አባል ነበሩ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ሠርተዋል። ይህ በቂ ነው።    የኢትዮጵያ መሪ ከሆኑ በኋላ እሳቸው የሚያምኑበትን መስመር ተግተው ነው የሚሠሩት። ቢሮክራሲው ላይ የሉበትም መስክ ላይ፤ ፕሮጀክት ተኮር ጉዳዮችን ይወጥናሉ፤ ይፈጽማሉም። ዳሽ የሆነው ሰብአዊነት ላይ ነው የማጽናናት፤ አይዟችሁ የማለት፤ በተከፋት ቀዬ በህዝባቸው ውስጥ ተገኝተው ጥግ የመሆን አቅም አለመኖር። እስር ላይ ያለው የማይገፋ ተራራ። ሌላው ዳሽ የሆነው የቢሮ አስተዳደራዊ ሥራም ነው። በተጨማሪም የሌሎችን መከፋት #አቅለው ማዬታቸው፤ ለመፍትሄው አለመትጋታቸው ዳሽ ነው።    ጠቅላይ ሚር መለስ ዜናዊ የትኛው ተቋም ላይ ሠርተዋል? ከጫካ ህይወት ቤተ- መንግሥት። በቃ! ዕውነቱ ይሄ ነው። ያለውን #ዕውነት #ማስከፋት አያስፈልግም። ከዚህም ሌላ መሪነት ፈቃደ እግዚአብሄር፤ ቅብዓ ስለመኖሩም ማመን ያስፈልጋል።    የሆነ ሆኖ አገራዊ ምክክሩ ለምን እንዳስፈለገ፤ ከዛ በፊት ለሙከራ አቋቁመው ያፈረሷቸው ኮሚሽኖች ሁሉ በመደዴ ታስበው የተከ...

በነገረ ሐራ መሬት የነገ #ስጋቴን ብገልጽስ? #ነገን ሰላማዊ ተከታይ ስለማድረግ።

  በነገረ ሐራ መሬት የነገ #ስጋቴን ብገልጽስ?   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   #ጠብታ ።   በብልጽግና መንግሥት የተፈቀደለት ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በአፋር እንዳለ ሳድምጥ ቆይቻለሁኝ። ለሽምቅ ኃይሉ የፖለቲካ ክንፍ እንደተደራጀለትም ይገባኝ ነበር። ግን የእኔን የመረዳት መጠን መሬት ላይ ካለው የራሱ አካል ማረጋገጫ እስኪሰጥበት ድረስ ጸጥ ብዬ መጠበቅ ነበረብኝ።   ሰሞኑን በአርተስ የዜና ዕውጃ ከስምረት ፖለቲካል ፓርቲ በተገኜ መረጃ መሰረት የኃራው ታጣቂ ሸማቂ ኃይል ክንፋ እንደሆነ ዜናው ያትታል። እኔም አውቄው ስለነበር አላስደነገጠኝም። እንዲህ ገልፆ መናገር መልካም ነገር ነው።   #ጥቃትን መቅደም እና መቀደም።   በጣም ከሚያሳዝኑኝ የዓለም ማህበረሰብ ውስጥ ሊባኖናውያን አንዱ ናቸው። ሊባነን መንግሥት አላቸው። መንግሥታቸው ግን ለህልውናቸው ቀጣይነት የደህንነት ዋስትና የመስጠት አቅም የለውም።   አቅሙ ያለው ከመንግሥት ውጭ የሆነው #ሂዝቦላ ነው። የሂዝቦላ የፖለቲካ ክንፍ የሊባኖስ ማዕከላዊ መንግሥት ሳይሆን አገረ #ኢራን ናት። የኢዝቦላ ተቋማት ሁሉ በሊባኖሳውያን ውስጥነት ታዳሚወች ናቸው። ወጩ የሚሸፈንለት በኢራን መንግሥት ነው። የሂዝቡላ የፖለቲካ ያው ሃይማኖታዊ ነው፤ የታጣቂ ኃይል መሪ የኢራን መንግሥት ፖለቲካ ነው።   ሂዝቦላ ለሚወስደው እርምጃ ዋጋ የሚከፍለው ደግሞ መከረኛው የሊባኖስ ህዝብ ነው። ይህ ወጣ ገብ ሁነት የተፈጠረው ከጥንስሱ የሊባኖስ መንግስት የራሱን የፖለቲካ፤ የሚሊተሪ ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ባለመቻሉ ነው። የዘገዬ እና ፍዝ አቋም ያለውም ነው። አሁን የሊባኖስ ንጹኃን የሚከፍሉት ዋጋ ተመን ሊወጣለት የማይችል ነው። ከሊባኖ...

የጨዋ ህዝብን መንፈስ #ማዋለል ለምን? የመልሰን "#እናጤነዋለን" ቀጠሮው ለመቼ? #መወሰን ያቃተው ነፍስ መኖር አልጀመረም።

  የጨዋ ህዝብን መንፈስ #ማዋለል ለምን? የመልሰን " #እናጤነዋለን " ቀጠሮው ለመቼ? #መወሰን ያቃተው ነፍስ መኖር አልጀመረም።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ። "   #ምዕራፍ ፲፱።   ይገርመኛል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁልጊዜ #በቀጠሮ ። "ቁርጥ ያጠግባል" ይላል ባለ ቅኔው ጎንደሬ። ይህ አሳረኛ ህዝብ እየተገበረ አሳሩን አዬ። ፍቅሩን በንጹህ ልቡ ቢሰጥም፤ መዝኖ ቢያስተዳድርም ስቃዩ ሊያባራ አልቻለም። መሻልን ለማሳዬት ሆኖ መገኜት ነው። ኢትዮጵያን ያህል አገር ለመምራት እራስ ሲታጭ ምን አለኝ ብሎ መነሳትን በእጅጉ ይጠይቃል። አገር ሱቅ በደረቴ አይደለችም።   #እፎካከራለሁ ስትል አቅምህን ነው እምታቀርብ እንጂ አንደበትህን አይደለም። ሙሉ አገርን ለመምራት የሰከነ፤ የሚዘልቅም ራዕይ፤ የተሰናዳ የተግባር ቅደም ተከተል፤ ብቁ መንፈስ እና ተመክሮ ይጠይቃል። ከምትፎካከረው፤ ከምታጣጥለው፤ ከምታቃልለው ይሁን፤ ከምታከብረው የፖለቲካ ድርጅት መሻልህን ህዝብ መስማት ሳይሆን ማዬት ይሻል።   የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን ኢትዮጵያ ፍቅሩንም፤ ክብሩንም፤ ዕውቅናውንም ለሁሉም በገፍ ሰጥቶ አይቷል። ተፈታትሿል። የኢትዮጵያ ህዝብ ስልጡን ህዝብ ነው። ቅኑ እና ቀናው ህዝባችን ምን እንዳለው፤ ምን ደግሞ እንደሌለው ያውቃል። በዝምታው ውስጥ እራስ እግሩ ብልህነት #ተደላድሎ የሰከነበት ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍጹም አድማጭም ነው። ፍጹም ቻይ ህዝብም ነው።    የሚገርመኝ ግን በመንፈሱ ስለምን በተለያዩ በሚዋልሉ፤ በሚያረገርጉ፤ እርስ በርስ በሚጠላለፋ ሃሳቦች፤ መሻቶች እና ፍላጎቶች ይሁኑ አቋሞች ላይ #እንዲቀጣ እንደሚደረግ አላውቅም።    መወሰን ያቃተው ነፍስ መኖርን አልጀመረም። 15 ቀ...