የህውሃት ለቅሶ ... ግፍ አይሆንም? ጡር ፍሩ!
የስሞታ ክምር አይሆንም እን ደ ተለመደው የልዕልና ብርንዶ ! እንኳን ደህና መጡልኝ። „እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፤ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።“ መዝሙረ ዳዊት ፲፯ ቁጥር ፲፬“ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.01.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። · ግ ርምታ! እንዴት ሰነበታችሁልኝ የእኔ ቅኖቹ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። በዬአቅጣጫው የሚሰማ አቤቱታ አንድ አይነት ነው - እንግሊዞች ሬድሜድ እንደሚሉት። የህውሃት ማንፌስቶ ማህበረተኞች የስሞታ ክምር በተለመደው የጭካኔ ብርንዶ የሰብዕ ቁርጥ አለመቀጠል የሁሉም የወል የለቅሶ ቤት ሆኗል። ሁሉም በአንድም በሌላም ተገፋን፤ ጥፋቱ ሁሉ ተጠቃሎ በአንድ ድርጅት ላይ ሆነ፤ የ27 ዐመቱ ዕዳ በእኛ ላይ ብቻ ተጣለብን፤ እምናመለከው የህውሃት ታቦት ሰሚ አጣ እያሉ እያጣወሩ ነው። ከ2008 ዓመተ ምህረት በፊት ወደ ነበረው መመለስ አለበት እያሉን ነው፤ ወንዝ ወደ ላይ ወይንስ ወደ ታች ይሆን የሚፈሰው?!ለመሆኑ 2010 እራሱን መልሰን ማምጣት እንችል ይሆን? · ብ ቻ እኛ እንዲህ እንላለን… 27 ዓመት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የተሸከመውን በደል ብራናውም ብዕሩም አይችለውም እና ጡሩ ፍሩ እያልን ነው። እነሱ ለ9ወራት ከጨቋኝነት፤ ከገዢነት፤ ከበላይነት መ ወገዳቸ ው የከበዳቸው 27 ዓመት ሙሉ በባይተዋርነት አሳሩን እዬበላ መወለደኑ የጠላውን 100ሚሊዮን ምንዱብ ህዝብስ ምን ይል ይሆን? ብግፍ የፈሰሰው ደም እና ዕናባስ ከቶ ተገኝቶ ቢጠዬቅ ምን ይል ይሆን?...