ልጥፎች

ከሜይ 10, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ዛሬን #ለመስኪ! #ብዙዬ #የብዕር "አንጋቿ" ውዴ ክብርት መስከረም አበራ እናትም ነሽ። #ታድለሽ!

  #ብዙዬ #የብዕር "አንጋቿ" ውዴ ክብርት መስከረም አበራ እናትም ነሽ። #ታድለሽ !   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   እናት መሆን የቻልሽው መስኪ እንኳን ለድንቁ፤ ለውቡ፤ ለበረከት ቀኑ የዓለም ዓቀፍ እናቶች ቀን ደረስሽልኝ። አንቺ ብዙ ነሽ። በቋሚነት በትንታጓ ብዕርሽ እደነቅም ነበር። የዘሐበሻ እና የሳተናው #ቋሚ #አምደኛ ሁለታችንም በነበርንበት ጊዜ ሁሉ ጽናትሽ ይደንቀኝ ነበር። አገር ቤት ሆኖ ያን መሰል የሃሳብ ሙግት አቅምሽ ይደንቀኝ ስለነበር አንድ ቀን ኢሜል ፃፍኩልሽ። ፈጣሪ አምላክ #ቸርሽን ያሰማኝ ዘንድ እለምነዋለሁኝ። የማይገኜው ዕፁብ የእናትነት ጸጋ ፈጣሪ ስለሰጠሽ ይመስገን። አሜን።   የማከብራችሁ የአገሬ፤ የዓለም እናቶች ሆይ!   እንኳን ለብርኃነ - ለዓለም ዓቀፋ ክቡር ቀን ለእናቶች በዓል #ደረሳችሁልን ። እናንተ ኃላፊነት እና ግዴታችሁን ባትወጡ እኮ ምድር ወና ትሆን ነበር። ስለሆነም ለሰጣችሁን የትውልድ #በረከት ልዩ ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረስ።   #እናታዊነት የደግነት መንክርነት ነው።   እናትነት የእናትን ተግባር መወጣት ስለሆነ፤ በልጆች ጉዳይ ኃላፊነት የወሰዳችሁ የረባ ዕውቅና ተሰጥቷችሁ የማያውቀው #አባቶች ፤ #ታላቅ እህት እና ወንድሞች፤ #የበጎ አድራጎት ያቋቋቋማችሁ #ደጋጎች ፤ #በማደጎ - በማር ልጅ ኃላፊነትን ፈቅዳችሁ የወሰዳችሁ ሁሉ እናትነት ተግባር እና ምግባር ነውና እና እንኳን ለዚህ #ቅዱስ ቀን በሰላም ደረሳችሁ።   ዕለቱ የደግነት፤ የርህርህና፤ የዕውነተኛ ሰውኛ ቀን ነውና ስናስበው በውስጣችን ሰፊውን ቦታ ይዞ የሚገኜውን #ክፋ ሃሳብን በማጽዳት ቢሆን ምርጫዬ ነው። የቻላችሁ ደብረብርኃን ቅር...