#ዛሬን #ለመስኪ! #ብዙዬ #የብዕር "አንጋቿ" ውዴ ክብርት መስከረም አበራ እናትም ነሽ። #ታድለሽ!

 

#ብዙዬ #የብዕር "አንጋቿ" ውዴ ክብርት መስከረም አበራ እናትም ነሽ። #ታድለሽ!
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
እናት መሆን የቻልሽው መስኪ እንኳን ለድንቁ፤ ለውቡ፤ ለበረከት ቀኑ የዓለም ዓቀፍ እናቶች ቀን ደረስሽልኝ። አንቺ ብዙ ነሽ። በቋሚነት በትንታጓ ብዕርሽ እደነቅም ነበር። የዘሐበሻ እና የሳተናው #ቋሚ #አምደኛ ሁለታችንም በነበርንበት ጊዜ ሁሉ ጽናትሽ ይደንቀኝ ነበር።
አገር ቤት ሆኖ ያን መሰል የሃሳብ ሙግት አቅምሽ ይደንቀኝ ስለነበር አንድ ቀን ኢሜል ፃፍኩልሽ። ፈጣሪ አምላክ #ቸርሽን ያሰማኝ ዘንድ እለምነዋለሁኝ። የማይገኜው ዕፁብ የእናትነት ጸጋ ፈጣሪ ስለሰጠሽ ይመስገን። አሜን።
 
የማከብራችሁ የአገሬ፤ የዓለም እናቶች ሆይ!
 
እንኳን ለብርኃነ - ለዓለም ዓቀፋ ክቡር ቀን ለእናቶች በዓል #ደረሳችሁልን። እናንተ ኃላፊነት እና ግዴታችሁን ባትወጡ እኮ ምድር ወና ትሆን ነበር። ስለሆነም ለሰጣችሁን የትውልድ #በረከት ልዩ ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረስ።
 
#እናታዊነት የደግነት መንክርነት ነው።
 
እናትነት የእናትን ተግባር መወጣት ስለሆነ፤ በልጆች ጉዳይ ኃላፊነት የወሰዳችሁ የረባ ዕውቅና ተሰጥቷችሁ የማያውቀው #አባቶች#ታላቅ እህት እና ወንድሞች፤ #የበጎ አድራጎት ያቋቋቋማችሁ #ደጋጎች#በማደጎ - በማር ልጅ ኃላፊነትን ፈቅዳችሁ የወሰዳችሁ ሁሉ እናትነት ተግባር እና ምግባር ነውና እና እንኳን ለዚህ #ቅዱስ ቀን በሰላም ደረሳችሁ።
 
ዕለቱ የደግነት፤ የርህርህና፤ የዕውነተኛ ሰውኛ ቀን ነውና ስናስበው በውስጣችን ሰፊውን ቦታ ይዞ የሚገኜውን #ክፋ ሃሳብን በማጽዳት ቢሆን ምርጫዬ ነው። የቻላችሁ ደብረብርኃን ቅርባችሁ ስለሆነ እዛ የሚገኙትን #ተፈናቃይ እናቶች #ሰላምታ ብትመግቧቸው ምኞቴ ነው።
 
ሌላው እንዲህ በልቅናቻው ለካቴና የተዳረጉትን ሄዳችሁ ብትጎበኙም የጽድቅ ጎዳና ነው። ጊዜው ብቻ ሳይሆን ሽልንጉም ይከብዳልና የምትችሉ ለማለት ነው። በተለይ ደጉ ሎዛ ሚዲያ ይህን ቢያደርግ ምኞቴ ነው። ለእስረኛ የተዋህዶ ልጆች #ተስፋነቱ ሁልጊዜ ይደንቀኛል። እማርበታለሁም። 
 
የእኔ ክብረቶች እንዴት አደራችሁ፤ እንደምን አረፈዳችሁ፤ እንዴትስ ዋላችሁ? #ዛሬን ለመስካሻ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን፤ አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
10/05/026

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።