ልጥፎች

ከኦክቶበር 7, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች የትኞቹ ናቸው? Etv | Ethiopia | News zena

ምስል

እኛ ይሆን #የተወሳሰብነው ወይንስ #ኢትዮጵያ? ኢትዮጵያ ይሆን #የተተበተበችው ወይንስ እኛ?

  እኛ ይሆን #የተወሳሰብነው ወይንስ #ኢትዮጵያ ? ኢትዮጵያ ይሆን #የተተበተበችው ወይንስ እኛ? ምዕራፍ ፲፬ ዛሬ አህዱ ልበለው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁ ወይ እኛ ይሆን #የተወሳሰብነው ወይንስ #ኢትዮጵያ ? ብዙ ሳደምጥ ሰነባበትኩኝ። እኛነታችን በዬትኛውም ፈርጅ ይሁን ማዕዘን ተጥመለመለብኝ ልበል ተፈተለተለብኝ? አለመረዳት? አለመግባት? አለመግባባት? ይሁን አለመፈጣጠር ትብትብ አለብኝ። እኔ ብቻ ይሆን ብዬ ራሴን እጠይቃለሁኝ። ዛሬም ይጨንቀኛል። ዛሬም ያሳስበኛል። ዛሬም ያስለቅሰኛል። ዛሬም ያሰጋኛል። ለነገም ይጨንቀኛል። ነገም ያሳስበኛል። መዳረሻው ዳርቻው ምን ሊሆን እንደሚችል ነብይ ሽው ይለኛል። ለምን? ዘመን ይጠዬቃል? ስለምን? ፖለቲካውም ይጠዬቅ? እንደምን የፖለቲካው ሹማምንቶች ከጫፍ እስከ ጫፍ ይጠዬቁ። ተጠያቂነት ይጠዬቅ። ኃላፊነትም ይጠዬቅ። እኛም እንጠያዬቅ። ትርፍ እና ኪሳራው የብትልናችንም ይመዘን። የትናንቱ መና ሲሆን የዛሬውስ የት ያደርስ ይሆን? ዝምታ ይሻል መናገር? መናገር ይሻል መራመድ? ወጥተው የቀሩት ልጆች ጉዳይ መጨረሻው የት ይሆን ፌርማታው? ለምን ቁርጥ ያለ ነገር አይገለጽም? ስለምን ተድቦልቡሎ፤ ተጠፍጥፎ ይቀርባል። የዕውነት አምላክ ዕውነቱን አስበራልን እና ቁርጣችን እንወቅ። መተከልም ከሞት የተረፋ ታገቱ ሰማን። ድብዛው ጠፋ። በዬጊዜው በገብሬ ጉሬቻም እገታ አለ። በአማራ ክልልም ወረርሽኙ እንደ መልካም ውርስ ከኦሮምያ ክልል ተቀድቶ የሰርክ ዜና ሆኗል። ምን ነካን? ማንስ አስነካን? እንደምንስ ይዳን? ከመካሰ ፖለቲካ እንዴት ይወጣ? ከመበቃቀል ፖለቲካ እንዴት ይዳን? ከትውልድ መማገድ ፖለቲካ እንደምን ይወጣ? ምናችን ይሆን የታመምነው? ከህሊናችን ውስጥ የትኛው...