ትውልድ የማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ወልዴ ቃላቸውን አተሙ!
ትውልድ ማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ወልዴ ዛሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዓለም አቀፋዊ ጥሪ አቀሩቡ። ቃላቸውንም በኢትዮጵያዊነት አተሙ! ከሥርጉተ ሥላሴ 20.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) "በመከራዬ ሳሉ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሄር ጮኽሁ፤ እርሱም ሰማኝ፤" (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፫) ትወልድ የማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ውልዴ ዛሬ በውጬ እና በአገር ውስጥ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያወያነ ሁሉ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሙሉ እግዛ እና ለቀናዊ ጉዟቸው ጥንካሬና ብርታት እንዲሆናቿው ለኢትዮጵውያን በሙሉ ታላቅ ዓለም ዓቀፋዊ ታሪካዊ ጥሪ አስተለላፉ። እኒህ ታላቅ ሙሁር እና የፖለቲካ ሊሂቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ናቸውም ማለት እችላለሁኝ። ከአገር ከወጡ በኋዋላ መድህን የሚባል የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው ካደራጁ በኋዋላ በራሳቸው ፈቃድ ለተተኪ ወጣቶች ያደራጁትን መድህን ፓርቲ ያሰረከቡ የመጀመሪያው የፖለቲካ ሊሂቅ ናቸው። ውስጣቸው ብቃታቸው ዕንቁ ነው። እኔ በልጅነት ኮ/ አሳፋ ሞሲሳ የሚባሉ ከፍተኛ መኮነን ይሆልታ ግንተ ዋና አሰትዳዳሪ ስለክቡርነታቸው እያስጠኑኝ ነበር ያደኩት። ስለሆነም በውስጤ የበቀሉ የፖለቲካ ሊሂቀ ሊሂቃን ናቸው ማለት እላለሁኝ። እንደ ዕድል ሆኖም ክቡርነታቸውን የተኳቸውን ወጣት ሁልት ረ/ ፕሮፌሰሮችንም በአካል ተገናኝቼ ተወያይቼም ነበር። ሁልጊዜ ስለ ብቁ የአገር መሪ ሲታሰብ አስባቸዋለሁኝ። በደርግ ዘመን ዓራት ዓይናማ ቁልፍ አካል ነበሩ። ሳይመቻቸው ሲቀር ወደ አሜሪካ