ልጥፎች

ከኦገስት 29, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እንሆነት ... ዴሞክራሲ

ምስል
ወትሮም። „የእግዚአብሄር ባርያዎች እግዚአብሄርን ያመሰግኑታል። እርሱ የተመሰገነ ነው። ለዘለአለም የተመሰገነ ነው።“ ተረፈ ዳንኤል ቁጥር ፷፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ 29.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የመፍትሄው መንገድ ወትሮም አንድ ነው። ከግራ ዝንባሌ ጋር መፈታት። ራስን ማሸነፍ። ነገር ግን ግራ ሁልጊዜም ግራ ነው። የአላዛሯ ኢትዮጵያ የህልውናው ችግር ይሄው ነው። እራሱን ችሎ እኮ የአላዛሯ ኢትዮጵያ የህልውናዋ የማንነቷ ታጋድሎ ያስፈልግ ነበር እኮ።  የዚህ ዝንባሌ አለው ተብሎ ነው እኮ ነው የአማራ የህልውና የማንነት ታገድሎም የተፈራው፤ የተገለለው፤ ዕውቅና ሳያገኝ ተድብስብሶ እንዲቀር የተፈለገው። ምክንያቱም ጨቋኝ እና ተጨቋኝን ፈጥሮ ኢትዮጵያን ለማመስ ዋነኛው ፒላሩ ይሄው ነበር እና። ይልቅ ቀቀድሞው ጠ/ ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ዚንባቢዎ ሰሞኑን ለውጪ ሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአማራን ተጋድሎ አውስተው ነበር። ተመስገንም ብያለሁኝ።  የሆነ ሆኖ ወትሮም ቢሆን ይሄው ነው የ43 ዓመቱ ለፍትህ እና ለነፃነት፤ ለህግ የበላይነት እና ለሃሳብ ልዕልና ተጋድሎ መደረጉ አንዱን በዳይ ሌላውን ደግሞ በዳይ በማድረግ ነበር። ሊዘህም ነው የ አማራን የህልውና የማንነት ተጋድሎ ያን ህዝበ ጠቀም ለማድረግ ያለው ቀናነት ዘሞ እንዲቀር የተደረገውም ሥሩ ያ ነው።  አሁንም በግራ በቀኝ ያሉት ወጀቦች የዛ ቅሪት አካል ናቸው። ሥር ነቀል ለውጥ ከኢህአድግ መራሹ ይታለማል? ይገርም ነው ዘንድሮ፤ እራሱን ኢህአዴግ ያክስምልን በራሱ ሜዳ ተጫውቶ? እንዴት ይደንቃል ይሄ ጥንዝል ፍልስፍና።  ለውጡን የሚመራው ኢህአዴግ ሆኖ ማለት ነው። ኢህአዴግን አንይህ ብሎ ነገር አዋጪ አይደለም።  ...