ልጥፎች

ከኖቬምበር 22, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፈጣሪ፤ የእናት እና የልጅ ውለ ወግ -በቅኔ ዘጉባኤ ህዋዊ ጠረጴዛ።

ምስል
 የሰለሥቱ ጥምር ትምህርተ ተመክሮ። የፈጣሪ፤ የእናት እና የልጅ  የበሰለ፤ የበቀለ፤ ያሰበለ  ብልህ ውለ - ወግ።               „ልጄ ሆይ ቃሌን ብተቀበል፣ ትእዛዜን በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፣ ጆሮህን ጥበብን እንዲያድምጥ ታደርጋለህ፣ ልብህን ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፩ እስከ ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 21.11.2018 ከአገረ ደናግሏ ሲዊዝሻ። ·          እ ፍታ። እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? የነፃነት ታጋይ ወገን ሲታሰር የሚከፋችሁ፤ ሲፈታ ደስ የሚላችሁ፤ ሰው ሲቸገር የሚጨንቀችሁ ሲቃለልለት ፍስሃ የሚኖራችሁ፤ ሰው ሲሰቃይ የሚመራችሁ ከስቃይ ሲፈወስ የምትፈኩ፤ ልጆች ከወላጆቻው ተለይተው ካቴና ሲባላቸው የምታነቡ ነፃ ሲሆኑ ደግሞ በሐሤት የምትፍነከነኩ ቸሮቹ የአገሬ የልዕልት ኢትዮጵያ ልጆች ከቶ እንዴት አላችሁልኝ? ተስፋ ካለ ምን ያስፈልጋል ትሉኝ ይሆን? ተስፋን ስንቅ የሚያደርጉ ስለተፈጠሩበት ሚስጢር ጥበብ ያላቸው ስለመሆኑስ? ሄውዞን የተቃኙ እንደማለት። አጥቁሮ ያከሰለን፤ ተስፋን የዋጠውን ቀን አል ደ መጥ ብሎ እንጂ ተስፋን ሰንቆ ማን ጦም ውሎ ያድራል? ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተስፋ ባለቅኔ ናቸው።  ቅኔኛም ብቻ ሳይሆን ቃላት አዲስ የመፍጠርም፤ የማራባትም /የማግሰስ/፤ የማዘመንም እና ለህሊና ምቹ እና ጣፋጭ፤ ለጆሮም ድሎተኛ አድርጎ የማቅረብ አቅማቸው በመሪ ደረጃ በእኔ ዕድሜ የመጀመሪያው ናቸው። ጣዕሜ የሆኑትም ከዚህ አንጻር ይመስለኛል። ቅንነታቸው እና ርህርሀናቸው ደግሞ የህሊና ካሊም ነው። ·       ቅ ኝተ ተህሊና። የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ንግግሮች ሌላ ሰው እንደሚጽፍላቸው የሚገምቱ አሉ። ይህን የቀደመ ን