ልጥፎች

ከዲሴምበር 22, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"በጀርመን የገና በዓል ገበያ ላይ ጥቃት ያደረሰው ማነው? ለምንስ ጥቃቱ ተፈጸመ?" BBC የእኔ ዕይታም። #ሩህሩሁ #አገረ #ጀርመን እግዚአብሄር ያጽናህ። አሜን።

      https://www.bbc.com/amharic/articles/c7vem6yjy23o   ከ 6 ሰአት በፊት "በጀርመን ማግደቡርግ ከተማ ሕዝብ በተሰበሰበት የገና ገበያ ላይ በተፈጸመ የመኪና ጥቃት የ9 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። አንድ ግለሰብ መኪናውን ሕዝብ በተሰበሰበት ገበያ ላይ እንደነዳ እና በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የጀርመን ፖሊስ አስታውቋል። ግለሰቡ ጥቃቱን ብቻውን ነው የፈጸመው ተብሏል። የመጀመሪያው ድንገተኛ ጥሪ ሲደረግ ግለሰቡ መኪናውን የገና በዓል ገበያተኞች ላይ መንዳቱ ተገልጿል። ድንገተኛ አደጋ ነው ተብሎ የታሰበ ቢሆንም ጥቃት መሆኑ ኋላ ላይ ታውቋል። የእግረኞች መንገድ ላይ ነድቶ ሰዎቹን እንደገደላቸው ተገልጿል። መንገዱ ለአደጋ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ነው። ቢቢሲ ያላረጋገጠው ቪዲዮ ግለሰቡ መኪናውን በቀፍጥነት እየነዳ ገበያውን ደረማምሶ ሕዝብ ወደተሰበሰበት ሥፍራ ሲያቀና በማኅበራዊ ሚዲያ ወጥቷል። የዐይን አማኖች ከእግረኛ መንገድ ሮጠው በማምለጥ ራሳቸውን እንዳዳኑ ተናግረዋል። ግለሰቡ ወደ እግረኛ መንገዱ በገባበት መንገድ መልሶ መውጣቱን ፖሊስ አክሏል። ግለሰቡ ጥቁር ቢኤምደብሊው አጠገብ በቁጥጥር ሥር ሲውል ታይቷል። አጠቃላይ ክስተቱ 3 ደቂቃ የሚወስድ ነው። በጀርመን የገና ገበያ ላይ በተፈጸመ የመኪና ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ቆሰሉ 21 ታህሳስ 2024   እነማን ተጎዱ? ተጠርጣሪውስ ማነው? በመኪና ጥቃቱ የ9 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ቢያንስ 41 የሚሆኑት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው። የሞቱት ሰዎች ማንነት ገና ይፋ አልሆነም። ጥቃቱን የፈጸመው የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት ያለው የ50 ዓመት የሥነ ልቦና ...