#ውስጤን በስሱ።
#ውስጤን በስሱ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት አደራችሁ ክብሮቼ። ውስጤን ብጥብጥ ያደረገው ግፋዊ እርምጃ ስከታተል አንድ ጹሁፍ አገኜሁኝ። ሰማዕቱ አልፏል። ነገስ ነው ጥያቄው። በስሱ ሁለት ዓመት ሊቃረበው ያለው ትግል እና ሂደቱን እስኪ እንቃኜው። ብዙ ቻልኩ፤ ብብዙም ታገስኩኝ። ዘጋቢው አቶ ይክበር ይመስገን በ6 ወር ብቻ 87 #ንጹኃን ተገድለዋል ባይ ናቸው። የገዳዮችን ግምታቸውንም አስቀምጠዋል። ጦርነት ውስጥ #በቀል #ቂም ምግቡ ነው። እናም የአማራ እናት ተሰቃዬች። ይህ ባህርዳር ብቻ ሳይሆን ከወሎ ደሴ ሃይቅ - ኮንበልቻ - ወልድያ ከተሞች ውጪ ያሉ የአማራ ከተሞች ማርቆስ፤ ዳንግላ፤ ፍኖተሰላም፤ ደብረታቦር፤ ጋይንት፤ አዲስ ዘመን፤ ዳባት፤ ደባርቅ፥ አዲስዘመን፤ ወረታ፤ አይከል፤ ጎንደር ከተማም በመሰሉ ከተሞችም ግፍ ይፈፀማል። ፌድራሉ ከህወሃት ጋር በደቡብ አፍሪካ ስምምነት ሲያደርግ ደስታዬ ወደር አልነበረውም። አፈሙዝ ፀጥ ሲል የከተማ ነዋሪወች እረፍት ታዬኝ። የሆነ ሆነኖ የፋኖ ንቅናቄው የተጀመረው #ከተማ ላይ ነበር። ግራ ነበር የተጋባሁት። ቀደም ብሎ ከዚህም ከዚያም እንድሳተፍ ያወያዩኝ ነበሩ። የማይታሰብ ነገር። በህይወቴ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የድርጅት አባል የሆንኩት። ድርጅቴ ሲፈርስ በቃ። መለካለክ ከሌላ ጋር ሰብዕናዬ አይፈቅድም። በምን ቋንቋስ ልንግባባ??? ወደፊትም የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባልም አካልም አልሆንም። ፈጽሞ። ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ የሽምቅ ውጊያ እኔ በታሪኬ ከተማ ውስጥ ከመደበኛ ሰራዊት ጋር ፊት ለፊት ሲገጥም ያዬሁት አሁን ነው። ከተማ ላይ ሽምቅ መሪወቹ እነ ሻለቃ ዳዊትየተገኜውን ድል ዘገባ ሲ...