ልጥፎች

ከፌብሩወሪ 17, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሀውልት ለኑክሩማ ወይስ ለሥላሴ? ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ።

ምስል
 እንኳን   ደህና   መጡልኝ።  ሀውልት ለኑክሩማ ወይስ ለሥላሴ? “ለሁሉ ዘመን አለው፤ ከሰማይ በታችም ለሆነው ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።” መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ እስከ ፪ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! {ማስታወሻ፤ ውድ አንባቢ! ቀጣዩ ፅሁፍ የተነቀሰው <ሞትና የኢትዮጵያ መሪዎች> በሚል ርዕስ በ381 ገጾች ህዳር 2006 ዓ/ም - 2013 - በአነስተኛ ቁጥር በሲድኒ ካሳተምኩት መፅሀፍ ነው። በዚህ መፅሀፍ የግርማዊነታቸውን ዘመን በሚተነትነው ምዕራፍ ዛሬ በሰፊው መነጋገሪያ የሆነው <የኢትዮጵያ ፓን አፍሪካውያን> በሚል የተደራጀው ማፍያ የህወሃት መንግሥታዊ ቡድን የግርማዊነታቸው ሀውልት በአፍሪካ ህብረት ግቢ እንዳይቆም በታሪክና በትውልድ ላይ የሰራው ሸፍጥ በዝርዝር ቀርቧል። ከአምስት ዓመት በፊት በታተመው መፅሀፍ የሚከተለው ትንተና ቀርቦ ነበር፤ መልካም ንባብ ይሁንልዎ!}        አቶ መለስና መንግሥታቸው ቀዳማዊ ሃይሥላሴ ለአፍሪካ ያበረከቱት አስተዋፅዖ እንዳይዘከርም ሆነ ቋሚ ሀውልት እንዳይተከልላቸው በፅኑ የጣሩና ጥረታቸውም ፍሬያማ እንዲሆን ያደረጉ ናቸው።  “የኢትዮጵያ እንቆቅልሽ፤ ሀውልት ለኑክሩማ ወይስ ለስላሴ?” Ethiopia’s conundrum: A statue for Nkrumah or Selassie?  በሚል ርዕስ የአፍሪካ ሪፖርተር ጃኔት ሾኮ / Janet Shoko/ ፌብሩዋሪ 8፤ 2012  ካቀረበችው ዘገባ የሚከተለውን ልብ ይሏል፤  የቀድሞውን የጋና መሪ ኳሚ ኑክሩማን ለመዘከር ሐውልታቸው በአፍሪካ አዳራሽ መተከሉ አግባብ ነው ሲሉ አቶ መለስ ጥብቅና ቆመውላቸዋል። የሃይለ ሥላሴ ሐውልት እንዳይተከልም ዐይነተኛ መከራከሪያቸው ያደረጉት፤ ኑክሩማ ፓን