አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም። ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው።
አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም። #ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው። ስስት ሰፊ ትርጉም አለው። እኔ አሉታዊ ስስት ላይ ነው ማተኮር እምሻው። "ለመብል ሁሉ አትሰስት ላዬኽውም እህል ሁሉ አትሰስት፤ ብዙ መብላት ደዌ ይሆናልና ስስትም ጓታን ያበዛዋል እና አትሰስት፤ ስስት የገደላቸው ሰወች ብዙ ናቸው፤ መጥኖ ዬሚበላ ግንሰውነቱ ጤና ነው።" ስስታም ዓይኑ ጠባብ ነው። ይቅበዘበዛል። ጎላ ብሎ በወጣው ላይ አንቴናውን ይዘረጋል። የእህል ስስት ለቁንጣን ይዳርጋል። የሥልጣን ስስት ደግሞ ለፋሺዝም። ስስት የህሊና ቀውስም ያስከትላል። ቀውሱ #ማናንሼ እለዋለሁኝ እኔው። የማንነት ቀውስ ያለበት ሰብዕና ውስጡ ሰላም የለውም። ይናደፋል። ይቦጭራል። ሁልጊዜ ግስላ፤ አራስ ነበር ነው። ሥልጣን ኖረውም አልኖረው ቅምጥ ፍላጎቱን ለማስቀጥል ሩጫው አጋጣሚውን በመጠቀም ይሆናል። አድብቶ ይጠብቃል። ብቅ ብሎ ይሰወራል። አረሳስቶም ጠቀራውን ያንዶለዱለዋል። እሳቱን ጫጭሮም ዞር ይላል። ገባ ወጣ ነው። ለምዱ እስቲገለጥ። አክ እስኪባል። መነገጃው ግን ያው የፈረደበት ኢትዮጵያዊነት ነው። እያከሰለ በምራቁ ቀለም ቀቢነት ያጎሳቁለዋል። እርግጥ ጠንቀኛውን ዬአንድ ለአንድ አጋበስባሽ ስስቱን አምቀው የያዙ ጊዜ ራዲዮሎጂ ሆኖ እስኪያጋልጣቸው ብዙ ማገዶ ይጠይቃል። ሰብዕናቸው #ግራጫ #በሲቃ ነው። አካሄዳቸው #ተርገብጋቢ እና #ገርበብ ያለ ነው። አልፎ አልፎ ፍንጭ ቢሰጡም ለሰከኑ ዬሰብዕና አጥኝወች ካልሆነ በስተቀር ተሎ ለማዬት ያስቸግራሉ። የሆነ ሆኖ አቅም፤ አቅል፤ ብቃት፤ ታሪክ ላለው ማህበረሰብ ስስታም ግለሰቦችም፤ ስስታም ተቋማትም የትውልድ ጠንቅ ናቸው። ካንፓቸው እና ካንፓሳቸው #ጥላቻ ነው። ምርታቸው ዲዲቲ ነው። ከሚጠሉት ዘለግ ...