ቤተመንግሥቶች ምነው ተጣላችሁን? ወይንስ ኩርፊያ ነገር …… "የጎንደር ሸኒት" የኦዳገዳ ኢንፓዬር ቤተ - መንግሥትም ሆነ ይሆን?

ቤተመንግሥቶች ምነው ተጣላችሁን? ወይንስ ኩርፊያ ነገር …… "የጎንደር ሸኒት" የኦዳገዳ ኢንፓዬር ቤተ - መንግሥትም ሆነ ይሆን?
ሰሞኑን ቸል ቸል ማለት አዘወተሩሳ ጠቅላዩወፕሬዚዳንቱ? ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሆኑሳ ሁለመና? #ክብርተወት የት ገቡ? እሳቸውን አንጠልጥለው ሲጓጓዙ ነበር የባጁት የሚያምኑት ባልንጀራ አጥተው።
የገረመኝ በእኔያ ፃድቅ፣የተደሞ ልዕልና የብቃት ቀንዲል፣ የመቻል ሐዋርያ ብፁዑወቅዱስ ሊቀጳስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ አቡነ መርቀርዮስ #የአደባባይ ሽኝት፣ #የፍትኃት ሥርዓት፣ #የቀብር ሥርዓት ቀዳማዊ እመቤትወት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ትውር አላሉም። #የጤናን ነው? ወይንስ "ከጎንደር ሸኔ" ጋር ተቀላቀሉ? የቆለኛ ነገር?
ጄኔራልወት ብርኃኑ ጁላ ጎንደርን "ሽፍታ" ሲሉ እርስወ ደግሞ "የጎንደር ሸኔ" ሲሉ ታሪክን ገድለዋል። ተመፃድቀዋል። ይህን ወንዘኛወትን ልከው ባገኙት ምክር ነው የሆነው። ተረኛው ተገዳይ ማን እንደሚሆን እዬጠበቅን ነው።
"ልብ ያለውሸብ" ይላል የሚፈሩት ባለቅኔ ህዝብ ጎንደሬ። ይልቅ ለምርኮኛ ጫማወትን ጠራጊ ምን አሉ ይሆን? ማህበረ ምርኮኛው ወዘተረፈ ነውና። አራገፋልኝ።
በ2011 ከአክሱምትሪቲ መልስ በወሎው ጉባኤ "ጌታቸው አሰፋ ከዚህ አለ" ያሉት ምን እንዳስከተለ በውን አይተናል።
በዚህ አጋጣሚ የጀግኖች ቁንጮ ኮነሬል ደመቀ ዘውዱ ጠንቀቅ ቢሉ መልካም ነው። እና ወግ ደርሷቸው ወሮ ዝናሽ ታያቸው "አይ" አሉ ይሆን? ቀዝቀዝ እንዳሉ ቀሩን?
በዛ በኦዳገዳ የወረራ፣ የመስፋፋት፣ የአስምሌሽን፣ የዲስክርምኔሽን "ብልፅግናወት" የአስረሽ ምችው ዳንኪራም የውኃ ሽታ ሆነዋል ክብርተወት?
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/03/2022
መጨረሻወትን ያዬው ሰው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።