በእውቀትም #ግዞተኛው አማራ ዬደንቢ ደሎ ትራጀዲ መቀጣጫ ነበር።
በእውቀትም #ግዞተኛው አማራ ዬደንቢ ደሎ ትራጀዲ መቀጣጫ ነበር።
#ውጤቱን አንቀበልም የሚል ሰላማዊ ንቅናቄ ይጠይቃል።
ይህ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የበቀል ዋንጫኛሞችን ተዋናይ ማድረግ የምጠብቀው ስለሆነ አይደንቀኝም።
የትምህርት ውጤት በረጅም ጊዜ ነው የሚታዬው። አራት ዓመት ሙሉ አማራ ከዕውቀት ውጪ በግዞት ላይ ይገኛል። ይቀጥላልም።
ይህን የገዳኦዳ ሥርዓት አናቱን በጥብጦ የሚንደው ካልተገኜ በስተቀር። ለዚህ ነው እኔ #HR 6600 ከውስጤ እምደግፈው። ናልኝ እምለው። ውስጤ ነህ የምለው።
~~~~~\\\~~~~~~
ከአቶ አዲሱ እንጎቻው።
"#የትምህርት ሚኒስቴር ጉድ በድንጋጤ ኩም ሊያደርገኝ ነው:!"
____+____
"በምስራቅ ጎጃም ዞን መርጦለማሪያም ከተማ የሚገኘው አብርሃዋፅብሃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደው አማኑኤል ፅሀይ ወንድም የተባለ የተፈጥሮ ሳይንሰ ተማሪ ከ700 አጠቃላይ ድምር ውጤት 164 አምጥተሃል ተባለ:ከዚያም ልጁ ጎበዝና በሀገርአቀፍ ደረጃም ሰቃይ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ በመሆኑ በውጤቱ ተደናግጦ online ቅሬታ አቀረበ:ቶሎ ሊሰተካከልለት ባለመቻሉ ፈተናዎች ኤጀንሲ በአካል ቀርቦ ሲያሰመረምር ትክክለኛ ውጤቱ *647*ሆኖ ልክ እንደተገመተው ከፍተኛውን ነጥብ ማሰመዝገቡን አረጋገጠ::"
___
"በምዕራብ ጎጃም ቲሊሊ ከተማ 140 አምጥተሃል ተብሎ የነበረ ተማሪ ቅሬታ አቅርቦ ሲመረመር 601:እንደዚሁም አዴት ከተማ 160 የነበረ ውጤት 618 ሆኖ ተገኝቷል:ሦሰቱ ጎበዝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በአካል በማቅረባቸው ውጤታቸው ተሰተካከለ:ምናልባት መምጣት ባይችሉ ኖሮ ግን ህይወታቸው ይበላሸ ነበር:በዚህ አይነት የሰንት ጎበዝ ተማሪዎች ውጤት ተበለሻሽቶ ይሆን??"
"ለማንኛውም ከዚህ መረዳት የሚቻለው ከወትሮው በተለየ መልኩ ለአማራ ክልል ተማሪዎች በብዛት መውደቅ ምክንያቱ ከጦርነቱ በተጨማሪ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ የውጤት ማሳሳት ሻጥር እንዳለ ነው:ስለዚህ የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች: መምህራን እና ሌሎች የሰራ ሃላፊዎች በአማራ ክልል መንግሰት ላይ ጫና ፈጥራችሁ ከትምህርት ሚኒሰቴር ጋር ተነጋግሮ መፍትሄ እንዲፈለግ ማድረግ ይጠበቅባችኋል::"
__+__
#ፍትህ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች!!
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/03/2022
አማራነትን የማያከብር ሰብዕና #ውራጅ ሰብዕና ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ