ይህቺ ቀን #የተናደች ዕለት እርስወን አያርገኝ።
#አሳቻው እና ሁለገብ ትትርናቸው።
#የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚር፣
#ፕሬዚዳንት,የኦዳገዳ የአስምሌሽን "ብልፅግና" #የጦርኃይሎችጠቅላይ አዛዥ፣
#የፓርክ አለቃ፣
#የደን ልማት ካፒቴን፣
#የአበባ ማምረቻ ድርጅት ተንከባካቢ ኤጀንሲ፣
#የኢቤንት ማናጀር፣
#የጓሮ አትክልት ሙያተኛ
#የሆሚኮኖሚክስ ተመራቂ ሰላጣ እና ባቄላ¡¡¿
#የመብራት ኃይል ዳንሰኛ ኃላፊ ምን ቀረ? እ #የኮትስትራክሽንኃላፊ፣
#የአማራ ክልል መስተዳድር ***ፕሬዚዳንት፣
#የስብከት ጠበብት፣
#የዕቃ ግምጃ ቤት ኃላፊ፣
ጫማ ጠረጋዋንም ተሻምተውታል፣ ዘይት ማከፋፈሉንም እንዲሁ። ያልሰነበተው #ጽዳተኝነትንም …… አንድ ሰሞን አስኮባ ተሸክመው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ነበር።
ዶር አብይ አህመድ አሊ እርስወ አቅደው፣ አደራጅተው፣ በመሩት የ90 ደቂቃ የባህርዳር እና የአዲስ አበባ ሰማዕታት የሽብር ናዳ እርስወ #በዕድሜ ልክ እስራት ሊቀጡ ሲገባ እነኝህን መከረኞች ፈረዱባቸው አይደል?
#በእዮር አደባባይ እርስወን ቅዱስ አምላክ ማን ብሎ ይጠራወት ይሆን?
#ከደቂቃኑ ከባከኑት፣ ከወደቁት መላዕክታን ዘር ይሆኑ? ቅጣተውት ከሰማዬ ሰማያት በላይ ሆነ?
በእርስወ ጥፋት ሌላው ይቀጣል፣ ይገደለላል፣ ይዋረዳል፣ ቤተሰቡ ፍዳውን ያያያል። ለእርስወ ስልጣን ሲባል። መኖር ከስሎ፣ መንኖ ይገኛል እስከ የት ይሆን ጉዞወት? መጨረሻወትን ያዬ ሰው?
እነኝህን መከረኞች በእርሰው የሽብር በጀት ተጠያቂ ሊሆኑ አይገባም። ዶር አንባቸውን የገደሉት ለሰሞኑ እራስወት እሩጠው እራሰወን ላስቀመጡበት ቦታ የሚበልጥ ሲነሪትም፣ ክህሎትም፣ ተቀባይነትም ሰልለው ስለደረሱበት ነው። ሌላ እንቆቅልሽ የለውም። በቃ ቀን ጥሩ ነው ታዩበት። ከሰነበተለወት።
አወኩን። ሰላማችን ቀሙን።ሐሴታችን ዘረፋን። ጥረታችንትቢያ አለበሱት። ሲያልቁ እንደሚያልቁ ለሰከንድ ይሰቡ። የሰው ደም የውሻ፣ የዶሮ አይምሰለወት።
ከ32 መኮንኖች አራት ፈቶ ቀልዱ ይቁም!
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/03/2022
ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ገዳይን ህዝብ ይዳኜዋል!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ