ልጥፎች

ከማርች 18, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።

ምስል
ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።   "የደጋግ ሰወች ልጆች ስሙኝ በረድኤት ታደሱ፤ አበባ በምድረ በዳ ጠል እንዲያብብ እንደሱ አብቡ። (በረድኤት ታደሱ) ዬሽቶ ማዕዛ ደስ እንደሚያሰኝ ማዓዛ ትምህርታችሁ እንደዚያ ደስ የሚያሰኝ ይሁን።"   አሜን ብዬ ልጀምር።   ፍቅር ተፈጥሮው ጥልቅ ነው። የዛሬ 7 ዓመት አንድ የጀርመን አውሮፕላን አብራሪ ፈቅዶ ከተራራ ጋር አውሮፕላን አጋጭቶ እሱን ጨምሮ ወደ 150 ሰወች አጠፋ። ፈጀ። 15 ቀን CNN ዘገበው። ሬሳው ከአውሮፕላን ላይ ሰው ተንጠልጥሎ ለቀመው። እጅግ አሰቃቂ ነበር። መተኛት መመገብ አቃተኝ። ከዛ የሰውልጅ ክፋነትን ከምን አመጣው የሚል ምርምር ቤቴን ዘግቼ ሰራሁኝ። ከማህፀን እና ከአብራክ አለመሆኑን ተረዳሁ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ንፁህ ሆኖ መፈጠሩን ለራሴ ሙግት መልስ አገኜሁ። ሁለተኛ ደረጃ አቅጣጫዬ ዬሰው ልጅ ከአብራክም ከማህፀንም ክፋትን ካልተማረ ከዬት ዬሚለው ሆነ ፍለጋዬ። መልሱ ከቤተሰብ፤ ከማህበረሰብ ዬሚል ሆነ። ለምን ዬሚለውን ሦስተኛው ጉዞዬ አንድ ጭብጥን ሸለመኝ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ሙሉ ሆኖ ሲኖር አንገቱ ተቆርጦ። ማዘዣ ጣቢያ አልባ። መኖር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተር ዓልባ። ፕላኔታችን አሳሰበችኝ። ነገ አስጨነቀኝ። ምክንያቱ ቀላል ግን ትኩረት ያላገኜ። ለክፋ ነገር ማርከሻ አልተሰራለትም። ክፋ ነገር ካለ ዬሚመክት ዬደግነት ትምህርት ቤት ሊኖር ይገባ ነበር። ያ ደግሞ ዬፍቅር ተፈጥር ካሪክለም ተሠርቶለት በመደበኛ ዬዓለም ዜጋ መማር አልቻለም። ዬፍቅር ተፈጥሮ ኮሌጅ፤ ዩንቨርስቲ፤ ኤክስፐርት፤ ሳይንቲስት፤ ፈላስፋ፤ ሙዚዬሣ።ም፤ ሚዲያ፤ መጋዚን፤ ግሎባል ቀን፤ ዬመንገድ ትርዒት ዬለውም። ዓለም በዘመኗ በፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት ላይ አጀንዳ ቀርፃ ተወ