ለመሆኑ የአማራ ህዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይታያልን? ትክክለኛ የፖለቲካ ዕውቅና እና ውክልናስ አለውን? ወላጅ አልባ ህፃናትንስ ሞግዚት ቀጥራችሁ ይሆን ወደ ወላጋዊ ሞት የምትሸኟቸውን??? ፍፁም ጨካኞች! ፍፁምም አረመኔወች ናችሁ።
ለመሆኑ የአማራ ህዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይታያልን? ትክክለኛ የፖለቲካ ዕውቅና እና ውክልናስ አለውን? ወላጅ አልባ ህፃናትንስ ሞግዚት ቀጥራችሁ ይሆን ወደ ወላጋዊ ሞት የምትሸኟቸውን??? ፍፁም ጨካኞች! ፍፁምም አረመኔወች ናችሁ። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ትናንት ከEMS ጋር አቶ አረጋ ከበደ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ለቃለ ምልልሱ ፈቅደው መቅረባቸው መልካም ነው። ነገር ግን ለቀረበላቸው ለስለስ ያለ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ በሲዊዝ ወይ በሲዊድን እንደሚኖር የአንድ አካል ተጠሪ ሆነው ነው የቀረቡት። ቤታቸው በበላያቸው እዬፈረሰ ለሳቸው ያሉበት ዶፍ አልታያቸው። የጦር ኃይሎች በሚመራው ክልል ሆነው፤ ከከተማ ከተማ በኢሊፍተር እና በብዙ አጃቢ በነፍስ ውጪ እና ግቢ ላይ እያሉ እሳቸው ልማት ጉብኝት ላይ ስለመሆናቸው ተርከዋል። የአማራ ህዝብ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፖለቲካዊ ዕድምታም አልገባቸውም። ስለሆነም በጭፍጫፊ ሳቢያወች ላይ ብቻ አተኩረው መልስ ለመስጠት ሞክረዋል። ጥያቄው እራሱ ሞጋች አልነበረም። ለዛም የበቃ ምላሽ ለመስጠት አልቻሉም። ለምሳሌ ወደ አዲስ አበባ አትገቡም የሚለው መከራ ዛሬ የለም፤ ስለቀደመው ተጠያቂ አይደለሁም ባይ ናቸው። የኦነግ ፖለቲካ ስትራቴጅ እና ታክቲክ ፈጽሞ አልገባቸውም ወይንም ለፖለቲካ ሴራው ሊጋባው ናቸው ማለት ነው። በአማራ ክልል ላይ ስለሚዘንበው የድሮን ጭፍጨፋም እኔ ማርስ ላይ ስለነበርኩ ልጠዬቅ አይገባም የሚል ዕድምታ ያለው ፍፁም የሆነ የጭካኔ ምላሽ ሰጥተዋል። ዬሚመሩትን ህዝብ መከራ እንዳላዩ፤ እንዳልሰሙ አልፈውታል። የጊዜ ጉዳይ እንጂ እሳቸውም ነገ ተረኛ መሆናቸውን ልብ አላሉትም። ደራጎንም ደራጎን፤ መቃብርም መቃብር፤ ሲኦልም ሲኦል ነው...