ወደ ቤቴ!
ማህሌቴ ወደ ቤቴ ስስቴ ወደ ቤቴ ወደ ቤቴ እኔነቴ። ሰገነቴ ወደ ቤቴ ወደ ቤቴ ማንነቴ። ናፍቆቴ ወደ ቤቴ ጥማቴ ሰዓታቴ። እረፍቴ። ልሂድ ወደ ቤቴ፤ አድባር - ቀለበቴ ዕርገተ-ህማማቴ፤ ቅድስተ - ትርስቴ። እባክሽ በሞቴ ! ጥሪኝ እመቤቴ ! የእኔ እሜቴ ! የደሜ እናቴ