ልጥፎች

ከጁን 15, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አማራ ከእንግዲህ ማረጃ ልኳንዳ ቤት አይደለም።

ምስል
         ጊዜ ምስክር ነው።                                                  ከሥርጉተ ሥላሴ 15.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) „እግዚአብሄር ዓለቴ፤ አምባዬ መድሃኒቴ ነው። እግዚአብሄር ጠባቂዬ ነው በእርሱም እታመናለሁኝ። ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ መጠጊዬና መሸሸጊያዬ መድሃኒቴ ሆይ ከግፍ ሥራ ታድንኛለህ።“  (መጽሐፈ ሳሙኤል ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫) የዕውነት ማህደር። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92069#comments “ በእስር ላይ ብሆንም ግንቦት 7 አንድም ጥይት በኢትዮጵያ ምድር እንዳላጮኸ ነው የማውቀው። ” አንዳርጋቸው ጽጌ ለቢቢሲ June 14, 2018 መነሻዬ ይሄ ነው። የሰማዕቱ ጎቤ እና ጓዶቹ ገድል በዓለም አደባባይ ስለተናኜ ደስ ይለኛል፤ ግን የተከበሩ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ተከትለው የሄዱ የውጪ ኑሯቸውን የተዉ አርበኞች ሜዳ ላይ ተሰዉ ዜናንም ሰምተናል። አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ሊገድል ነው ሲባል ጎንደር፤ ፊት ለፊት ውጊያ አድርገን ሞቱ ሲባል የጎንደር አርበኞች፤ ተጋድሎው ህዝባዊ ሲሆን የግንቦት 7 ነው፤ ይህ ውስብስብ የፖለቲካ ትርምስ እንዴት ነው የሚፈታው? ግንቦት 7 እንዲታመን ነው ወይንስ ግማሽ ውሸታም ነው ለማለት ነው? ወይንስ ቅይጥ መንፈስ ለመፍጠር ነው አልገባኝም። እርግጥ ነው በአንዲት የውጊያ ግንባር ፊት ለፊት ገጥሞ ውልቅልቁ ወጥቶ...