ልጥፎች

ከኤፕሪል 18, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአገር መከላከያ ሚ/ር ለማ መገርሳ ራሳቸውን ሾሙ ነው መባል ያለበት።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የአገር መከላከያ  ሚ/ር ለማ መገርሳ ራሳቸውን ሾሙ ነው  መባል ያለበት። „ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚአስፈልገኝን   እንጀራ ስጠኝ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፴ ከቁጥር ፰ እስከ ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18.04.2019 ከመነኩሲያዋ ሲወዘርላንድ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የኢህአዴግን ማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ እንዴት አዬሽው የሚል መልእክት ደርሶኛል። እንደተለመደው ነው እኔ ያዬሁት። እንዲያውም የሳጅን በረከት ዳግሚያ ተንሳኤ ብለው ይሻላል። ጠረኑ ሙሉ ለሙሉ ሳጅን በረከት በረከት ነው የሚለው። መድከም አያስፈልግም። በሌላ በኩል ደግሞ በመስከረሙ ጉባኤም መሰሉን አዳምጠናል፤ መሃል ላይ ደግሞ በህወሃት አሳሳቢነት አንድ ስብሰባ ነበራቸው፤ ያው መግለጫ ወጥቶ ነበር። እንዲህ ተገናኝተው መግለጫ ያወጣሉ። የሚተገበረው ግን በዶር ለማ መገርሳ ምህንድስና ብቻ ነው። ያ የግብር ይውጣ ነው። ወደፊትም በዚህው ይቀጥላል። ይልቅ አንድ ፖስተር ላይ „ዶር አብይ አህመድ አቶ ለማ መገርሳን ሾሙ“ የሚል ሚዲያ ላይ ተለጥፎ አይሁኝ። ይህ ግዙፍ ግድፈት ስለሆነ ይታረም ዘንድ ነው ይህችን ቆራጣ ጡሁፍ ያሰናዳሁት፤ እንጂ በዬሳምንቱ ለሚናድ ሹመት እና ሽረት ጉዳይ ማድረግ የተገባ አይመሰለኝም።   „ማን ፈቺ ማን አስፈቺ“ አሉ አቶ ዳውድ ኢብሳ እኔ ደግሞ እንዲህም እላለሁኝ። ማን ሿሚ ማን ተሾሚ ሆኖ ነው? ሾሚውም፤ ሻሪውም ዶር ለማ መገርሳ እራሳቸው ናቸው። እራሳቸውን ይፋዊ ነው የሾሙት፤ ራሳቸው ናቸው ፌድራል ላይ ደግሞ አሰኛቸውና በቋሚነት መቀመጥ አለብኝ ያሉት። ሁሉ በእጅ...