ልጥፎች

ከኦክቶበር 5, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ህመም።

ምስል
የተደከመበት እሾኽ በቀለበት። „እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፤--- በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም፤ ሬሳውም በቀን፤ ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይሰጣል።„ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ህመ ም። የጎንደር የአማራ የማንነት የህልውና አብዮት የወለደው የጣና ኬኛ አብዮት ሥጦታ የሰማይ ነበር። መክሊቱም የሰማይ ነበር። ሶሻሊዝም የዘራውን የሴራ የመከራ ምንጭ ከሥሩ ለመንቀል የሚያስችል እዮራዊ መልዕክት ነበር። ሶሻሊዝም ንደፈ ሃሳቡ ብቻ ሳይሆን በዚህ ፍልስፍና ውስጥ ያሉ ሰውን የሚፈትኑ የራስ በሽታዎች አገርን ህዝብን፤ ሰብዕናን የሚንዱ ረቂቅ የወረርሽኝ ጠንቅ አምራችነቱ የግራው ፍስፍና የማህበርስብ ሞራል ጠንቅንም ነው። ህመም! የጎንደሩ አብዮት መንፈስ የጠራው ያ የጣና ኬኛ አብዮት ይገላግለናል ብለን ብዙ ደከምን። ብዙ ለፋን። አሁን ሁሉም ታጥቦ ጭቃ ሆነ። ለውጡ ከሴራ፤ ከተንኮል፤ ተሰርጎ ገቦች  ጥቃት መዳን አልተቻለውም።  እንደ ገና አሁን እንደ ተለመደው በዬጎጆው ጉግስ አለ። ጦርነቱ ጦፏል። ዕንባም መጠጊያ አጥቷል። በዬቀኑ ቤት አልባው ህዝብ ቁጥር እያሻቀበ ነው። ዕንባም የትም ቦታ በዬትኛውም አድርሻ ማግኘት ይቻላል። ዕንባ አብቃይ መሬት መቼ ትዝታ ብቻ ሆኖ እንደሚቀር፤ "ነበር፡ የምንልበት ዘመን መጣ ሲባል ጥሎን ሄደ ….. ሄደ ሄደ ነጎደ ነጎደ ….ተስፋን እዬጎራረደ፤ የራይ ጥሪትን እያንጓዳጎደ። ህመም! ለችግሩ መንስኤ እኔ ነኝ የሚል አልተገኘም። የችግሩ መንስኤ ግን ቅናት ነው። ቅናት ደንበር ዘለልም ነው። ቅናት የፈጠረው ጦርነት ነው አሁን ይህ...